2010-09-24 16:13:29

የታልቅዋ ብሪታንያ ጳጳሳት መግለጫ


የታልቅዋ ብሪታንያ ጳጳሳት ባለፈው ሳምንት ቅዱስ ኣባታችን ያደረጉት የ4ቀናት ሓዋርያዊ ጉብኝት ስኬታም እንደነበረ መግለጫ ኣውጥተዋል፤ መግለጫው በእንግሊዝ ኣገርና ወይልስ ጳጳሳት በኣንድ በኩል በእስኮትላንድ ጳጳሳት ደግሞ በሌላ በኩል ቢወጣም ይዘቱ ኣንድ እንደሆነ ከትልቅ ብሪተይን የመጣ ዜና ያመለክታል።

ጳጳሳቱ የትልቅ ብሪታንያ ንግሥትንና መንግሥት እንዲሁም በኣጠቅላይ ኣገሩን ሙሉ ር.ሊ.ጳጳሳትን በመቀበል ያሳዩትን ትልቅ ኣክብሮት በመጥቀስ ኣመስግነዋል። በእንግሊዝ ኣገርና በወይልስ ጳጳሳት መል እክት ሌላ ትኩረት የተሰጠው ጉዞው ስኬታም እንዲሆን ያዘጋጁትን ሲያመሰግኑ የእስኮትላንድ ጳጳሳት ደግሞ የኣገሩ መገናኛ ብዙኃንን ባደረጉት ትብብር ኣመስግነዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.