2010-09-24 16:11:40

ከክርስቶስ ጋር ከሚፈጠረው ቅርብ ግኑኝነት የጓደኛ ርኅራኄ ይወለዳል


ቅዱስ ኣባታችን ባለፈው ሮብ የትልቅዋ ብሪተይን ሓዋርያዊ ጉብኝት ኣመልክተው ባቀረቡት ትምህርታቸው የጉብኝቱ መል እክት ር.ሊ.ጳ መልእክት ‘ከክርስቶስ ጋር ከሚፈጠረው ቅርብ ግኑኝነት የጓደኛ ርኅራኄ እንደሚወለድ’ የሚያመለክት መሆኑን ገልጠዋል።

ሕወታችንና ሁኔታችን ሁሉ እግዚአብሔር ለኛ ካለው ፍቅር ይነሳል፤ ኣስቀድሞ የሚወደን እግዚአብሔር ነው፤ ሁላችን እንደ እርሱ ቅዱሳን እንድሆንም ይፈልጋል፤ እንደ እርሱ ቅዱሳን መሆን ማለት ፍቅሩን ተቀብሎ ዘለዓለማዊ ደስታ ማግኘት ነው። የክርስትና ሕይወት ለቅድስና ጥሪ እንደመሆኑ መጠን ቅድስና የሰው ልጅ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው መልስ ነው፤ ማለትም የሰው ልጅ ልቡን ከእግዚአብሔር ልብ ጋር ኣንድ ለማድረግ ያለው የጋለ ፍላጎት ነው። ይህም በየዕለቱ መለኮታዊ ፈቃድን ለመፈጸም ይገፋፈናል፡ ዓላማችን ለፍቅርና በፍቅር ስለሆነም በእግዚአብሔር መልክና ኣምሳል ተፈጥረናል፡ ብለው ነበር።

ቀጥለውም ማፍቀር ከባድ መሆኑን ገልጠዋል፤ ስስት ቅናት ለእኔ ይመቸኝ ማለትና ለሥልጣን ያለን ጥማት ማፍቀርን ኣስቸጋሪ ያደርጉታል፤ ስለዚህም ፍቅር በእያንዳንዱ ቀን በምናደርገው ምርጫ ይወሰናል፤ ጌታ በምሥጢራቱ በሚሰጠን ጸጋና ከቅዱስ ቃሉ ከምናገኘው ጥበብ እንዲሁም በጸሎት የጌታ ኢየሱስ እርዳታ እየጠየቅን ፍቅርን መምረጥ ኣለብን፤ ይህ ሁሉ በሕይወታችን ውስጥ ኣንድ መንፈሳዊ ደንብ እንድንሰራና ለጸጥታ የሚሆን ግዜ በመምደብ በዚህም ጸጥታ ጌታ እንዲናገረን መጠባበቅ ያስፈልጋል፡ ጸሎት የሌለበት ሕይወት የተከተልን እንደሆነ እንደሚጮህ ብረት እንሆናለን፤ ሁሉ ይደባለቃል፤ የተሳሳተ ውሳኔ በማድረግ ስሕተተኛ መንገድ መከተል እንችላለን፤ እምነት የኣ እምሮ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከልብ የሚነሳና እስከ ውስጣችን በመግባት ሁኔታችን መለወጥ ኣለበት፤ እንዲሁ ካደረግን ኣስተሳሰባችን ይሰፋል፤ ከእግዚአብሔር ያለን ጓደኝነት እያደገ ይመጣል፤ በችግር ላሉ ወንድሞቻችን በችግራቸው እንድረዳቸው ይገፋፋናል፤ ጌታ በወንጌሉ እንዳለው ለሁለት ጌቶች ሊታዘዝ የሚችል የለም፤ የችግራችን መፍትሔ እግዚአብሔር ብቻ ስለሆኑ እሱን በማመን ተስፋችን በጠቅላላ በእርሱ ላይ መጣል እንድሚያስፈልግ በዚህም ከክርስቶስ ጋር ከሚፈጠረው ቅርብ ግኑኝነት የጓደኛ ርኅራኄ እንደሚወለድ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.