2010-09-22 14:17:32

ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት


በአፍሪቃ እድገትን ለማነቃቃት በሚል ዓላማ ላይ ያነጣጠረ ጉባኤ ጳጳሳዊ የባህል ምክር ቤት እና የአስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅባር ጋር በመተባበር የአቢያተ ክርስትያን እና የተለያዩ መንግሥታውያን እና RealAudioMP3 መንግሥታውያን ያልሆኑት ብሔራዊ አቀፍ እና ዓለም አቀፍ የተራድኦ ማኅበራትን በማስተባበር፣ በአፍሪቃ እድገትን ለመነቃቃት የሚይስችሉትን መንገዶችን እና የልማት እቅዶችን እግብር ላይ ለማዋል የሚያገለግሉ ሰብአዊ ሙያዊ ኤኮኖሚያዊ ብቃት ለማስጨበጥ የሚያስችሉትን ጉዳዮች በጋራ ለመሻት ያለመ፣ ሰው የእግዚአብሄር አርአያ እና አምሳያ ነው የሚለው መሆናዊው ሐቅ መሠረት በማድረግ የሚወያይ ዓለም አቀፍ የባህል ጉባኤ እንዲካሄድ ያቀረበው ሐሳብ እ.ኤ.አ. በ 2011 ዓ.ም. መጋቢት ወር ላይ እንደሚካሄድ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

በአፍሪቃ እና በስደት ላይ የሚገኙት አፍሪቃውያን ባህል፣ ማንነት፣ ልማት በሚል ሰፊ እና ጥልቅ ርእስ የተመራ እንደሚሆን ከወዲሁ ሲታወቅ፣ በአፍሪቃ እድገት እንዲረጋገጥ የሚደግፍ ብቻ ሳይሆን የእድገቱ ሂደት ፈጣን እንደሚያደርግ ከወዲሁ አቢይ ተስፋ የተጣለበት ጉባኤም ጭምር ነው። ይኽ በሚቀጥለው ዓመት ሊካሄድ ተወስኖ ላለው ዓለም አቀፍ ጉባኤ የሚሸኙ ጳጳሳዊ የባህል ምክር ቤት እና የአስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር በጋራ የአፍሪቃ መጋብያን ወይንም ልኡካነ ወንጌል እና በአፍሪቃ እና ከአፍሪቃ ውጭ የሚገኙት አፍሪቃውያን የቲዮሎጊያ ሊቃውንትን ለመደገፍ ያለመ መርሃ ግብሮች እንደሚያከናውንም ተገልጠዋል።

ቤተ ክርስትያን ማንኛውም እድግት የሚጀመረው እና የሚረጋገጠው በወንጌል ቃል ሲመራ ብቻ ነው የሚል እምነት እንዳላት የሚያጎላ፣ እ.ኤ.አ. መስከረም 27 ቀን 2010 ዓ.ም. እንዲሁም ጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. በአቡጃ በሚገኘው የምዕራብ አፍሪቃ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እና የተልእኮ ማእከል ሁለት የግኑኝነት ጉባኤዎች እንደሚካሄዱም የቅድስት መንበር መግለጫ በመጥቀስ እንዲህ በመቀጠልም እ.ኤ.አ. በዚህ በሚቀጥለው ዓመት ሊካሄድ ተወስኖ ባለው ጉባኤ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የሚወክሉትን የሚያዘጋጅ የተለያዩ ግኑኝነቶች እንደሚከናወኑ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.