2010-09-22 16:33:43

የር.ሊ.ጳጳሳት ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (22.09.2010)


ቅዱስ ኣባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ለተሰበሰቡት ምእመናንና ከተለያዩ ክፍላተ ዓለማት ለመጡ ነጋድያን በተለመደው ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ይህንን ኣስተምህሮ ኣቅርበዋል። “ውድ በክርስቶስ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ እንደምታውቁት በታላቅዋ ብሪጣንያ ካደረግሁት ሓዋርያዊ ጉዞ መመለሴ ነው፤ ለረጅም ግዜ ቀዝቅዞ በነበረው የቅድስት መንበርና ታላቅዋ ብሪጣንያ ግኑኝነት ኣዲስና ኣስፈላጊ እርምጃ በሰጠው በዚሁ የኣራት ቀን ሓዋርያዊ ጉብኝት በኣካል ለተገኛኙንና በብዙኅን መገናኛ ብዙ ላበረከቱት ሁሉ የጋለ ሰላምታየን ለመላክ እወዳለሁ።
ባለፈው ሓሙስ በታላቅ ብሪጣንያ ንግሥትና የአደንበራ ልዑል መስፍን በእስኮትላንድ ታሪካዊ ዋና ከተማ አደንበራ ባደረጉልኝ ደማቅ ኣቀባበል ታላቅ ክብረት ተሰማኝ። በዛኛው ቀን ማምሻውን በግላስገው ከተማ ብዙ ጳጳሳት ካህናት ገዳማውያትና ገዳማውያን እንድዲሁም ብዙ ም እመናን በተገኙበት በጥለቅ ላይ የነበረች ጸሓይም ልዩ ድምቀት በሰጠችበት በላዩስቶን ፓርክ ከኔ በፊት የነበሩ ፍቁር ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ከ28 ዓመታት በፊት የቀደሱበትን ቦታ እያየሁ መሥዋዕተ ቅዳሴ ኣሳረግሁ።

ለንደን በደረስኩበት ጊዜም በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ካቶሊካውያን ተማሪዎችን ሕጻናት ሓዋርያዊ ጉብኝቴን በታላቅ ደስታ ሲያከብሩ ኣገኘህዋቸው፤ ይህም በታላቅዋ ብሪጣንያ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ኣብያተ ትምህርትና ኣስተማሪዎች የሚደረገውን ታላቅና መሠረታዊ ሥራ ያመለክታል፡ ከዚያ በመቀጠል የተለያዩ ሃይማኖቶች መሪዎች ካህናትና ምእመናን ጋር በመገናኘት ስለ ሃይማኖት ልዩነቶች ተወያይተን ለሁላችን የሚሆን የጋራ ቅዱስ ውህደት የምናገኝበትን መንገድ ተወያይተናል።

ከዛ በመቀጠል እስከ ሮም በመመላለስ ብዙ ጊዜ ያገኘን የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ ጋር በመገናኘቴ ታላቅ ክብር ተሰማኝ፤ ከሊቀ ጳጳሱና ከጠቅላላ የእንግሊዝ ኣንግሊካውያን ጳጳሳት በላምበዝ ፓላስ ያደረግነው ውይይት ልብ ለልብ የሚያገኛኝባ ወንድማማችነት የሞላበት ነበር፤ ከዛ በመቀጠል ወንዝን ተሻግሬ በወስትሚኒስተል ኣደራሽ ተሰብስበው ከነበሩ ከታላቅዋ ብሪጣንያ ፓርላማ ሁለቱ ምክርቤቶች ጋር ለመወያየት ታላቅ ዕድል ኣገኘሁ፤ በዚሁ ውይይት ብታላቁ የሃገሩ ተወላጅ ቅዱስ ቶማስ ሙር ጊዜ የነበረ ኣስተሳሰብ ዛሬም በእኛው ዘመን ተገቢ የሆነው በእምነትና ኣእምሮ *ሳይንስ* መህከል ስላለው ግኑኝነት ተናግረናል። በመጨረሻም በዛው ቀን ላይ ከካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ ጋር ኣብረን በቅዱስ አድዋርድ መቃብር ፊት ተንበርክከን ለመጸለይና የእስኮትላንድና የሌሎች የታላቅዋ ብሪጣንያ ኣብያተ ክርስትያን መሪዎች ኣስተባባሪ ከሆኑ ሊቀ ጳጳሱ ኣብረን እግዚአብሔርን ክርስትያናዊ ኣንድነታችንን እንደገና ለማነቃቃት ስለሰጠን የተለያዩ ጸጋዎች ኣመስግነናል።

በቀጠለው ቀን ጥዋት ላይ ከጠቅላይ ሚኒስተር ደይቪድ ካመሮን እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ኒክ ክለግ እና የተቋዋሚው ፓርቲ መሪ ሃሬት ሃርማን ጋር ተገናኘሁ፤ ከዛም በኋላ በወስትሚኒስተር ካተድራል በበለጠው የእንግሊዝ ሙዙቃ የተሰኘ ሮማዊ ሥር ዓተ ኣምልኮ ቅዳሴ ኣሳረግሁ፤ ከቀትር በኋላም በን ኡሳን የድሆኖች ደናግል ማኅበር እርሳቸው ከሚረድዋቸው ሽማግሌዎች ጋር ተግናኘሁ፤ በዛው ኣጋጣሚ ለታላቅ ብሪጣንያ ሕጻናት ደህንነት ለሚሰሩ ድርጅቶች ለማመስገንና ለማበረታታት ዕድል ኣገኘሁ። ማምሻውን ጸጥታና የጸሎት መንፈስ በሰፈነበት በሃይድ ፓርክ በብዙ ሺ ከሚቆጠሩ ምእመናን እጅግ ደማቅ የሆነ የኒውማን ብጽዕና ማዘጋጃ ጸሎተ ዋዜማ ተሳተፍኩኝ፡

እሁድ ጥዋት የካርዲናል ጆን ሄንሪ ኒው ማን ሥር ዓተ ብጽ ዕና ለመፈጸም ወደ በርሚንግሃም ተጓዝኩኝ፤ የብጽ ዕና ሥር ዓት የተፈጸመበትን መሥዋዕተ ቅዳሴ ከፈጸምኩ በኋል ከታላቅዋ ብሪጣንያ ጳጳሳት ጋር የጋለና ወንድማማችነት የሞላበት ግኑኝነት ኣካሄድኩኝ፤

ማምሻውን በበርሚንግሃም ዓለም ኣቀፍ የኣየር ማረፍያ ጠቅላይ ሚኒስተር ደይቪድ ካመሮን በቀረበልኝ ልባዊ የሽንት ንግግር የታላቅ ብሪጣንያ መንግሥት ለሁሉም ብልጽግና ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያንና ከሌሎች ጋር ትብብር እንደሚያደርግ ቃል ገብቶልኝ ከታላቅ ብሪጣንያ ተሸኘሁኝ።

ስለዚህ እሁድ ዕለት ቤተ ክርስያን ሕይወቱና ጽሑፉ ለረዥም ዓመታት ትልቅ ኣድናቆት ላተረፈና ከኣገሩ ድንበር ባሻገር ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች ለመረጡት ኒውማን ብጽዕና ባወጀችበት ጊዜ ጥልቅ እርካታ ተሰማኝ። የብጹዕ ጆን ሄንሪ ኒውማን ብሩህ ኣ እምሮ እውነትን ለማወቅና ብፍቅር ለመግለጥ ያካሄደው ኣሰሳ የግሉ ምቾት ሁኔታ ጓደኝነትን ሳይቀር ቢፈታተነውም ከቤተ ክርስትያን ጋር ኣንድ በመሆን እግዚአብሔርን የማወቅና የማፍቀር ኣስደናቂ ምስክርነት ነው፤ ይህ ኣብነት ሁላችንን በማንቃት መሪ ኣብነት እንደሚሆን እርግጠኛ ነኛ። በማለት በታላቅዋ ብሪጣንያ በቅርቡ ስላካሄዱት ሕዋርያዊ ጉብኝት በተለያዩ ቋንቋዎች ከገለጡና ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ ሶሙንን በቭየና ስለሚካሄደው በካቶሊክካዊት ቤተክርስትያንና በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ዓለም ኣቀፍ ንባበ መለኮታዊ ውይይት ይህንን የአደራ መልእክት ኣስተላልፈዋል፤ ‘በዚህ ሳምንት በቪየና በካቶሊክካዊት ቤተክርስትያንና በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ዓለም ኣቀፍ ንባበ መለኮታዊ ውይይት የሁለቱ ኣብያተክርስትያናት የጋራ ኮሚሽን አጠቃላይ ጉባኤ እየትካሄደ ነው፤ በዚሁ የውውይት ደረጃ በኣንደኛው የሺ ዓመት ዘመን የሮማ ጳጳስ በዓለም ኣቀፍ ቤተ ክርስትያን ስለነበረው ሚና የሚያጠና ነው። ለጌታ ኢየሱስ ፍቃድ መታዘዝና የዘመናችን ትልላቅ የክርስትና ፍልምያዎች እግምት ውስጥ ማግባት የቤተ ክርስትያን ሙሉ ውህደትን እግምት ውስጥ እንድናገባ ያስተገድደናል። ሁላችሁ የኮሚሽኑ ሥራዎች በድል እንዲወጡና የተጠመቁ ሰዎች ለመላው ዓለም የላቀ የወንጌል ምስክርነት ለመስጠት እንዲችሉ በመሃከላቸው ቀጣይ የሰላምና የይቅር መባባል መንፈስ እንዲሰፍን እንድትጸልዩ ኣደራ እላለሁ’ በማለት የዛሬውን ትምህርት ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.