2010-09-22 14:18:40

ባን ኪ ሙን፣ ሰላም የተካነው ዓለም


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን ትላትና ታስቦ የዋለው ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ምክንያት፣ መንግሥታት ለአክራሪያን ኃይሎች ቅስቀሳ እና ዓላማ በቀላሉ ሊማረክ ለሚችለው ለወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል፣ መቀባበል RealAudioMP3 መቻቻል መከባበር የሚያስቀድም ሰላም የተካነው ዓለም የማስረክቡ ሃላፊነት አለባቸው በማለት ትእዛዛዊ ጥሪ አዘል መልእክት ማስተላለፋቸው ተገልጠዋል።

ቀኑን ምክንያት በማድረግ በኢጣሊያ የሰላም ጠረጴዛ ማኅበር እ.ኤ.አ. መሰከረም 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ሁሌ በየዓመቱ ከፐሩጃ እስከ አሲዚ የሚካሄደው የሰላም የእግር ጉዞ፣ የሰላም ባህል፣ አበይት ክንዋኔዎች በማረጋገጥ የሚሰርጽ ሳይሆን ዕለት በዕለት በሚረጋገጡት ሰላምን የሚያነቃቁ እርምጃዎች አማካኝነት መሆኑ እና የመገናኛ ብዙሃን ሳይቀር ይኸንን ሓሳብ እንዲቀበሉት የሚገፋፋ እና የሚያሳምን ወይንም እንዲያስተነትኑበት የሚቀሰቅስ በማድረግ እዳዘጋጀው ለማውቅ ሲቻል፣ እ.ኤ.አ. ከ መስከስረም 6 ቀን እስከ መስከረም 17 ቀን 2010 ዓ.ም. የመገናኛ ብዙሃን ለሰላም ግንባታ እና ዜጎች ለሰላም ሕንጸት የሚስጡት አስተዋጽኦ የሚገመግም የመገናኛ ብዙሃን መርሃ ግብሮች ላይ ለየት ባለ መልኩ ክትትል እንዲደረግ ሀሳብ ያቀረቡት የሰላም ጠረጴዛ የተሰኘው ማኅበር አባል አልበርቶ ባልዳዚ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የመገኛ ብዙሃንን ለ11 ቀን በመከታተል ያቀረቡት መርሃ ግብር እና ያቀረቡት የሥርጭት መርሃ ግብሮቻቸው እንዲሁም ያስተላለፉዋቸው የፖለቲካ የውይይት መድረኮች ጭምር ሰላም የሚል ቃል ያልተሰመረበት እና ያልተሰማበትም መሆኑ ጠቅሰው፣ የበለጠ ዓለም ብሎም የሰውል ልክ ያለው ዓለም ለመገንባት እና ለማረጋገጥ ሰላም ወሳኝ ሆኖ እያለ በፖለቲካው መድረክም ይሁን በመገናኛ ብዙሃን ጭምር ስለዚሁ ጉዳይ ምንም ሳይባል መቅረቱ እጅግ የሚያሳዝን ነው።

ከሕይወት መድረክ እሴቶች እና የእሴቶች ቅደም ተከል መደለዙ ጸረ ሰላም ድርጊት ነው። ስለዚህ እሴቶችን ማነቃቃት በሁሉም ዘንድ እንዲከበሩ እና እንዲስተነተኑ ማድረግ ለሰላም መንገድ ማቅናት ማለት ነው። ስለዚህ ኅብረተሰብ በተለይ ደግሞ ወጣቱ ትውልድ በሰላም እንዲታነጽ እና ሰላም ለማረጋገጥ ተቀዳሚ ተወናያን ማድረግ የሚያስችሉ መርሃ ግብሮች ማፋጠን ይጠበቅብናል። ስለዚህ ግጭት በሚታይባቸው ክልሎች የሰላም አስከባሪ ኃይሎች መላክ ብቻ ሳይሆን በሰላም ባህል የታነጸ ህብረተሰብ በማቆም የሰላም አስከባሪዎ ኃይል በዚህ ባህል የታነጸ መሆን ይኖርበታል። የሰላም ሕንጸት መርሃ ግብር በህሉም የመገናኛ ብዙሃን ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ዓላማ መሆን አለበት።

አበይት እና አንገብጋቢ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ሆነው እያሉ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን በኵል ቅድሚያ ሳይሰጣቸው ባንጻሩ ብዙውን ጊዜ የመገናኛ ብዙሃን ትኵረት የሚሰጡበት ፖለቲካዊ አሉ ባልታ ተቀዳሚ ሆነው ይታያሉ። እነዚህ መሠረታውያን ናቸው የሚባሉት የመገናኛ ብዙሃን ጉዳይ ትኩረት የሚሰጥባቸው ጉዳዮች፣ መሠረታውያን ጉዳዮች እንዳልሆኑ የመገናኛ ብዙሃን ጠንቅቀው የሚያውቁት እየሆነ ነገር ግን ማእከላዊ ሥፍራ እንደሚሰጡበት ሥርጭቶቻቸውን በመከታተል ለማረገገጥ የተቻለ እውነት ነው። ስለዚህ በሁሉም መድረክ ቅድሚያ ማግኘት ያለበት የሰላም ሕንጸት እና የሰላም ባህል ማስፋፋት የሚለው እቅድ ላይ ያተኮረ መርሃ ግብር መሆን ይገባዋል በማለት የሰጡን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.