2010-09-21 15:48:49

የካንተርበሪይ ሊቀ ጳጳስ ሮዋን ዊልያምስ አስተያየት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በታላቅዋ ብሪታንያ ያካሂዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት ከሁሉም አቢያተ ክርስትያን መሪዎች ጋር ያከናወኑት ግኑኝነት እና የተፈጸመው የጋራው ጸሎት መርሃ ግብር በማስመልከት የውህደት አንግሊካዊት RealAudioMP3 ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳሳት ሮዋን ዊሊያምስ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ያከናወኑት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተዋጣለት የደስታ አጋጣሚ እና ከአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን፣ እንዲሁም ከሕዝብ የቀረበላቸው አቀባበል እና መስተንግዶ አወንታዊ እና በተለይ ደግሞ በዌስትሚኒስትር አዳራሽ በመጨረሻም በጋራ በዌስትሚኒስትር ርእሰ አድባራት በህብረት በተደገመው ጸሎተ ሰርክ የታየው መንፈሳዊነት ደስ የሚያሰኝ ነው ብለዋል።

ሐዋርያዊ ጉብኝቱ ከመፈጸሙ በፊት የነበረው አሉታዊ ቅድመ ግምት ውድቅ ብቻ ሳይሆን የተሳሳተ ግምት እንደነበርም ሁሉም ያየው እና ያረጋገጠው ጉዳይ ነው። ስለዚህ የተባረከ እና ሕዝብ ቅዱስነታቸውን ለመቀበል ወደ አደባባይ እና በመንገድ ዳር ወጥቶ የሰጠው የእምነት ምስክርነት የሚደነቅ ነው፣ ስለዚሁ አሉታዊው ቅድመ ግምቱ በታየው የእምነት ምስክርነት አማካኝነት መሻሩ ሁሉም ያየው እውነት ነው ብለዋል።

ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጋር ባካሄዱት የግል ግኑኝነት የተከናወነው ውይይት በካቶሊክ እና በአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን መካከል ያለው ግኑኝነት ላይ ያተኮረ ነበር። ሆኖም ይህ ዓይነቱ ግኑኝነት በይፋ በተለያዩ የግኑኝነት መርሃ ግብሮች የሚከናወን መሆኑም አስታውሰው፣ የበሁለቱ አቢያተ ክርስያን መካከል ያለው ግኑኝነት ላይ ያተኮረ ብቻ አልነበረም ካሉ በኋላ የመካከለኛው ምስራቅ ማኅበረ ክርስትያን ወቅታዊ ሁኔታ፣ የዚህ ክልል ብፁዓን ጳጳሳት እንዲያካሂዱት ተወስኖ ያለው ሲኖዶስ፣ ሁለቱ አቢያተ ክርስያን በሱዳን ጉዳይ፣ የሰላም ቀዳሚነት፣ ከዓለማውያን ጋር የሚደረገው ግኑኝነት እና ውይይት በተሰኙት ርእሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ገልጠዋል።

ብዙውን ጊዜ የመገናኛ ብዙሃን በሁለቱ አቢያተ ክርስትያን ያለው የጋራው ግኑኝነት እያስገኘው ያለው አወንታዊ ውጤት በማስደገፍ ከመናገር ይልቅ፣ ግጭት ሌላው የሚስብ ርእስ በመሆኑ በዚሁ ላይ በማተኮር ዜና ሲያቀርቡ ቢታይም ቅሉ፣ የዛሬ 40 እና 50 ዓመት በፊት የማይታሰብ ውጤት እንዲሁ ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ወዲሁ የታየው መቀራረብ፣ የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን የቲዮሎጊያው ሃብት እና ከቤተ ክርስትያን አበው የተወረሰው የጋራው መንፈሳዊ ባህላዊ እና ቲዮሎጊያዊ ሃብት፣ የሚያገናኝ ትልቅ ሃብት ነው። ይህ ደግሞ በተፈጸመው የጋራው የጸሎት መርሃ ግብር አማካኝነት በተጨባጭ ተመስክረዋል፣ ስለዚህ በመገናኛ ብዙሃን የሚዘነጋው በሁለቱ አቢያተ ክርስያን መካከል ያለው ፍቅር ወዳጅነት የተመሰከረበት ግኑኝነት ነው በማለት፣ የዛሬ 28 ዓመት በፊት ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እና ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. ያካሄዱት ጉብኘት በታላቅዋ ብሪጣኒያ እምነት የሚያነቃቃ እንዲሆን በመመኘት ሐዋርያዊ ጉብኝቶቹ ይፈጸሙ ዘንድ አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን በመጸለይ እንደተባበረች እና ጸሎቱም ከእግዚአብሄር መልስ እንዳገኘ ያረጋገጠ ግኑኝነት ነበር በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.