2010-09-20 16:32:22

የቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ የትልቅዋ ብሪጣንያ ሓዋርያዊ ጉብኝት በሰላም ተፈጸመ


ቅዱስነታቸው በታላቅዋ ብሪጣንያ ያደረጉት የ4 ቀን ሓዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው ትናንትና እንደ ኢጣልያ ሰዓት ኣቆጣጠር ከምሽቱ 10.30 በሰላም ቻምፒኖ ዓለም ኣቀፍ የኣየር ማረፍያ ደርሰዋል።

ሓዋርያዊ ጉብኝቱ እጅግ ማራኪ እንደነበረ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠር ሕዝብ በቀጥታ እንደተከታተለው እንዲሁም በተለቪዥን በኢንተርነትና በረድዮ በብዙ ሚልዮን የሚቈጠር ሕዝብ እንደተከታተለው ብዙ የብዙኃን መገናኛ ተገልጠዋል።

ቅዱስነታቸው ትናንትና ለጉብኝቱ ዋና ምክንያት ከሆኑ ኣንዱ ግብረ ተልእኮ ለመፈጸም እንዲዘጋጁ፤ ቅዳሜ በሃይድ ፓርክ ለንደን ከተማ ከ200 ሺ በላይ ከሚሆኑ ምእመናር ኣብረው፤ ለካርዲናል ኒውማን የብጽዕና ሥርዓት ጸሎተ ዋዜማ ጥልቅ በሆነ መንፈስ ኣሳርገዋል።

ትናንትና ጥዋት ካደሩበት የሓዋርያዊ እንደራሴ መኖርያ ቤት ተነስተው ወደ ዊምብለዶን ፓርክ ተጉዘው ከዛ በሄሊኮፕተር ወደ በርሚንግሃም በመሄድ የካርዲናል ሄንሪ ጆን ኒውማን ሥርዓተ ብጽዕና ፈጽመዋል።

ይህንን ሥርዓት የፈጸሙበትን መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳረጉበት ቦታ ረንዳል በሚባለው የበርሚግሃም ቀበሌ የሚገኝ ኮፍቶን ፓርክ ይባላል፤ ይህ ሕዝባዊ መንፈሻ የኣትክልት ሥፍራ እስከ ሰባ ሺ ሰው ሊይዝ ይችላል።

ብሥርዓቱ ላይ ከ60 ሺ በላይ ምእመናን ተገኝተው ነበር፤ ሥርዓቱ ከመጀመሩ በፊት የበርኒንግሃም ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ኣቡነ በርናርድ ሎንግሊ የእንኳን ደህና መጡ ሰላምታ ኣቅርበዋል።

ቅዱስነታቸው የካርዲናል ኒውማን ብጽዕና ባወጁበት ጊዜ ከትልቅዋ ብሪታንያና ከኣየርላንድ ለተሰበሰቡ 60 ሺ ምእመናን “ክቡር የእግዚአብሔር ኣገልጋይ ጆን ሄንሪ ካርዲናል ኒውማን ብጽ ዕና እናውጃለን” በማለት የሚከተለውን የብጽዕና ኣውጅ ኣንብበዋል።

“የበርሚንግሃም ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ኣቡነ በርናርድ፤ የሌሎች በጵጵስና ውንድሞቻችን የሆኑ ጳጳሳት እና የብዙ ምእመናን ልመና በመቀበል እንዲሁም የቅዱሳንን ጉዳይ ከሚከታተል ማኅበር ጋር በመወያየት በሓዋርያዊ ሥልጣናችን ክቡር የእግዚአብሔር ኣገልጋይ የሰባክያን ማኅበር ካህን ጆን ሄንሪ ካርዲናል ኒውማን ብጽዕና እናውጃለን። ካሁን ወዲህ እንደ ብጹዕ ለኣማላጅነት ይቀርባል ዝክረ በዓሉም በየዓመቱ ጥቅምት 19 ቀን በቤተ ክርስትያን ሕግ መሠረት በተቋቋሙ ቦታዎች ይከበራል።” ብለዋል። ሕዝቡም በሆሆታና ብጭብጨባ ደስታውን ገልጠዋል።

ቅዱስነታቸው በቅዳሴ መሃከል በሰበኩት ስብከት ‘በብጹዕ ኒውማን ሕይወት ሕያው ምስክር የሆነ የኣበ ነፍስ ቅድስና እናገኛለን፤ በስክተ ወንጌል ግብረ ተል እኮው በትምህርቱ እና በደረሳቸው ጽሑፎች ይህንን ኣጉልቶ ኣሳይተዋል፡ በዚሁ ኣዲስ ብጹዕ የቅድስና ምንጭ የሆነውን የታላቅዋ ብሪተይን የማስተማርና የጥልቅ ሰብኣዊ ጥበብ ባህል እንዲሁም ለጌታ ያለውን የጋለ ፍቅር ለማግኘት እንደሚቻል’ ግለጠዋል።

የሓዋርያዊ ጉብኝታቸው መሪ ቃል ያደረጉትን ‘ልብ ለልብ ይናገራል’ የሚለው የካርዲናል ኒውማን መፈክር ምን እንደሚያስተምረን ሲገልጡ፤ ይህ መሪ ቃል የክርስትና ሕይወት የቅድስና ጥሪ መሆኑን ለመረዳት ያስችለናል እንዲሁም የሰው ልጅ ልብ ምንኛ ያህል ከእግዚአብሔር ልብ ጋር ሊገኛኝ እንደሚፈልግ ያብራራልናል፤ ብጹዕ ኒውማን ለጸሎት ታማኝ መሆን ቀስ በቀስ ወደ መለኮታዊ ሕይወት እንደሚያሻግረን ያስተምራል፤ ስለዚህ የኒውማን ትምህርት ክርስትያን ም እመን ለእያንዳንዳችን የሚሆን ዕቅድ ለሰጠን ጌታ እንዴት በወሳኔና በቊርጠኝነ ማገልግል እንድምንችል ያስተምራል”ብለዋል።

የኒውማን ትምህርት በመል እልተ ባህርያዊ ነገሮች ብቻ ሳይወሰን፤ ኣእምሮና እምነትም እንደሚግናኙና እንድሚረዳዱ ያብራራል፤ ቅዱስነታቸው ይህንን ሲገልጡ ‘ኒውማን መልእልተ ባህርያዊ ግልጸት በሰለጠነው ኅብረተሰብ ስላለው የእምነትና የኣእምሮ ግኑኝነት ያስተማረው በጊዜው ለንበረችው ታላቅ ብሪጣንያ ብቻ ሳይሆን ገና ዛሬም በመላው ዓለም ላሉ ሰዎች እያተማረና እያብራራ ነው፤’ በማለት ካብራሩ በኋላ ስለትምህርትም ቢሆን የኒውማን ሥነ ሓሳብ ለካቶሊካውያን ትምህርት ቤቶች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች የሚሆን መሠረታዊ የኣእምሮ ግንባታ እንዳቋቋሙ ገልጠዋል።

በመጨረሻም ስለ ክህነታዊ ኣገልግሎቱ በተለይም ትናንትና ተዘክሮ በዋለው 70ኛ የእንግሊዝ ውጊያ ኒውማን ያበረከተውን በማስታወስ እሳቸውም የውግያውን ጊዜ እንደሚዘክሩት በመጥቀስ ለሕመምተኞች ለድሆች እንዲሆም ለእስረኞች ያበረከተው ኣገልግሎት የማይረሳ መሆኑን ገልጠዋል።

የሥርዓተ ብጽዕና ቅዳሴ ከተፈጸመ በኋላ የመል ኣከ እግዚአብሔር ትምህርት ሲያቀርቡም ይህንን ከ70 ዓመታት በፊት በናዚ ጀርመንና በታላቋ ብሪጣንያ መካከል የተደረገውን ኣሰቃቂና ኣሳፋሪ ውግያ በማስታወስ ሁላችን ለሰላም መሥራት እንዳለብን ኣደራ በማለት ሁሉንም ፈጽመዋል።

የሥርዓተ ብጽዕና ቅዳሴ ከተፈጸመ በኋላ ቅዱስነታቸው የቅዱስ ፊሊፖ ነሪ የግብረ ሠናይ ማእከል ጐበኙ። ይህ ማእከል እላይ እንደተጠቀሰው ብጹዕ ኒውማን የተመሠረት ሆኖ ብዙ የእርዳታ ሥራ ያበረከቱበት ቦታ ነው፤ መሥ ብጹዕ ኒውማን ወደ ካቶሊክ ሃይማኖት ከተመለሱ እስከ ዕለተሞታቸውም እዚህ ቦታ ነው የተቀመጡት፤ ቅዱስነታቸው እማእከሉ በደረሱበት ወቅት የማእከሉ ኃላፊ ተቀብለዋቸውል፤ በቤተ ጸሎት የግል ጸሎት ካሳረጉ በኋላ የብጹዕ ኒውማን መኖርያ ቤት የነበረው ኣሁን ግን ቤተ መዘከር ሆኖ ላለው ታዝበዋል።

ቅዱስነታቸው እንደገና ጉዞኣቸውን በመቀጠል ወደ ቅድስት ማርያም ኮለጅ ኦስኮት በመሄድ 50 ከሚሆኑ የኢንግላድ የወይልስና የእስኮትላንድ ጳጳሳት ተመግበዋል፤ ከምግብ በኋላ ከጳጳሳቱ ጋር በመገናኘት ስለ ልዩ ልዩ የግብረ ተልእኮ ጉዳዮች ተናግረዋል።

ማምሻውን በበሚንግሃም ኣለም ኣቀፍ የኣየር ማረፍያ የታላቅዋ ብሪተን ጠቅላይ ሚኒስተር ስለጉብኝታቸው ኣመስግነው እሳቸውም በብኩላቸው ስለተደረገላቸው ኣቀባበል በማመስገን ተለያዩ፤ በሮም ሰዓት ኣቆጣጠር ከምሽቱ 10.30 ቻምፒኖ ኣለም ኣቀፍ የኣየር ማረፍያ በሰላም ገብተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.