2010-09-17 14:23:20

ካናዳ፣ ዓለም አቀፍ የኃይል ምንጭ ጉባኤ


በካናዳ ሞንትሪያል ከተም ዓለም አቀፍ የኃይል ምንጭ ጉዳይ ርእስ በማድረግ በመካሄድ ላይ ባለው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ተገኝተው ንግግር ያሰሙት የአፍሪካ ኅበረት የልማት ባንክ ቤት ሊቀ መንበር ዶናልድ ካበሩካ፣ በአፍሪቃ ያለው የኃይል ምንጭ ድኽነት 80% የክፍለ ዓለሙን ሕዝብ አለ መብራት እንዲኖር ማስገደዱ አብራርተው፣ የከሰል እና የውኃ ኃይል ምንጭ ከፀሐይ ብርሃን እና ከውኃ የሚገኘው ኃይል ምንጭ የመጠቀሙ ሥልት እየተስፋፋ ቢሆንም ቅሉ፣ የዚህ ሃብት ምንጭ ተጠቃሚው ግን በአፍሪቃ የሚገኙት የውጭ ኅብረ ኢንዳስትሪዎች ናቸው እንዳሉም ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የኃይል ምንጭ አጠቃቀም ድኽነት ለልማት እና ለኤኮኖሚ እድገት አቢይ እንቅፋት መሆኑ ካበሩካ አብራርተው፣ ይህ ደግሞ በአፍሪቃ የጤና ጥበቃው አሠራር ለአደጋ ከማጋለጡም አልፎ እንዳይስፋፋም እያደረገ ነው። ስለዚህ የኃይል ምንጭ ድኽነት፣ በህሉም ዘርፍ ልማት እና እድገት እንዳይኖር የሚያደርግ አቢይ እንቅፋት መሆኑ ማብራራታቸው ሚስና የዜና አገልግሎት ካሰርጫው የዜና ምንጭ ለመረዳት ተችለዋል።

አፍሪቃ ያለባት የኃይል ምንጭ የመጠቀሙ ፍላጎት ለማርካት የኃይል ምንጭ ናቸው የሚባሉትን ሁሉንም መንገዶች በሚገባ በማጤን ተጠቃሚ ለሆን የሚያስችላት መንገድ መቀየስ ይኖርባታል፣ ስለዚህ የኃይል ምንጭ አገልግሎት ፖለቲካ፣ ስነ ምኅዳር የሚከተል አካባቢን የማይበክል ሕይወት ለአደጋ የማያጋልጥ መሆን አለበት እንዳሉ ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.