2010-09-17 14:18:30

ተዛማጅ ባህል እና የእግዚአብሔር ጥማት


በታላቅዋ ብሪጣኒያ ኅብረሰብ ዘንድ የሚታየው ሃይማኖታዊ እና የተዛማጅ ባህል የተካነው ሕይወት ኑሮ በማስመልከት አንድ የእስየሱሳውያን ማኅበር ተማሪ አባል ሳሙኤል ኦቨርሉፕ፣ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ RealAudioMP3 በትክክል የታላቅዋ ብሪጣንያ ኅብረተሰብ በደፈናው ማመን አለ ማመን ሁሉም ያው ነው በሚለው ተዛማጅ ባህል የተጠቃ ነው ብሎ መናገር ትክክል አይደለም፣ ይኽ ደግሞ በቅርብ የሚያውቁት ብቻ ሳይሆን ከግል ተመኵሮ በመንደርደር የሚያረጋገጡት ሐሳብ መሆኑ ገልጠው፣ ስለዚህ ብዙሃኑ የአገሪቱ ሕዝብ እግዚአብሔር እንደሚያስፈልገው የሚገልጥ ሕይወት የሚያስተጋባ እየሆነ መምጣቱ የወቅቱ ተጨባጭ ገጠመኝ ቢሆንም፣ በአግሪቱ ኅብርሰብ ዘንድ እምነት የተነጠለ እጠርዝ ላይ የተተወ እንዳልሆነ ለመረዳት የሚያግዙ ብዙ ምክንይቶች እንዳሉ ነው ብለዋል። ሆኖም ማመን አለ ማመን ሁሉም ያው ነው የሚለው እሴቶች እና የእሴቶች ደረጃ ብሎ የለም የሚለው ተዛማጅ ባህል እየተስፋፋ ነው። ይህ ደግሞ በአገሪቱ የተጋረጠ ችግር መሆኑ ገልጠው፣ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንደሚሉት እምነት እና ምርምር አገናኝቶ ማወያየት አስፈላጊ ነው። ስለዚህ በታላቅዋ ብሪጣኒያ ያለው ካቶሊክ ማኅበርሰብ አናሳ ቢሆም ቅሉ፣ ትሁት በሳል በእምነቱ የጸና በቃል እና በሕይወት የሚመሰክር ገንቢ እና ንቁ የኅብርሰብ አባል ሆኖ መገኘት ይኖርበታል በማለት ቅዱስነታቸው የሰጡት ምክር ገቢራዊ ማድረግ ያስፈልጋል።

ስለዚህ ቤተ ክርስትያን፣ ገዳማውያን ካህናት ደናግል፣ የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች በጠቅላላ በአገሪቱ የሚገኙት ልኡካነ ወንጌል ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ላይ መሠረታቸውን ያኖሩ በእርሱ ላይ የተገነቡ በተመሳሳይ መልኩም ባላቸው ሙያ እና ጥሪ ከሚኖሩበት ኅብረተሰብ ጋር በሚገባ ተዋህደው የሚኖሩ፣ ዜጎች የማነጹ ኃላፊነት ይጠበቅባታል። ደስታ የተካነው ማኅበርሰብ በመገንባት ወጣቱን ወደ ቤተ ክርስትያን መሳብ አስፈላጊ ነው። ሌላው ችግር ማህበራዊ ፍትህ የሚለው መሆኑ በመጥቀስ፣ ብዙ የፖለቲካ አካላት እና መንግሥታት የቤተ ክርስትያን የማህበራዊ ጉድይ ትምህርት መሠረት በማድረግ ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚጥሩ በማብራራት፣ ይህ እውነት መደበቅ ሳይሆን ድምጻችምም ከፍ በማድረግ በማስተጋባት ይኖርብናል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.