2010-09-15 15:16:54

ዓለም አቀፍ የነጋድያ እና የቅዱሳት ሥፍራ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ


የቤተ ክርስትያን ኵላዊነት ገጽታ በመጠበቅ የቅርብ ተጨባጭ ተመኵሮ በተመለከተ ያለው ግንዛቤ አማካኝነት እያንዳንዱ ይኸንን ተመኵሮውን ለማገናኘት እና ለማነጻጸር የሚያነቃቃ ጳጳሳዊ የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ከሳንቲያጎ ርእሰ ሰበካ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ዓለም አቀፍ የነጋድያን እና የቅዱሳት ሥፍራ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጉዳይ የሚወያይ እ.ኤ.አ. እስከ መስከረም 30 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚዘልቅ ሶስተኛ ጉባኤ እፊታችን መስከረም 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በሳንትያጎ ደ ካምፖስተላ እንደሚከፈት የስደተኞች እና የተጋጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ከሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።

ይኽ ዓይነቱ ቀዳሜ ጉባኤ እ.ኤ.አ. በ 1992 ዓ.ም. በሮማ መካሄዱ የሚዘከር ሲሆን፣ በዚህ ዘንድሮ የካምፖስተላ የኢዮቤል ዓመት በሚዘከርበት ወቅት የሚካሄድ ጉባኤ በመሆኑም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዚያኑ ቅዱስ ሥፍራ ሐዋርያዊ ጉብኝት በሚያካሂዱት ወቅት የሚጠናቀቅ መሆኑ የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ አባ ጋብርኤለ ቤንቶሊዮ የጉባኤው መርሃ ግብር በማስደገፍ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በመጥቀስ፣ ጉባኤው ከተለያዩ 75 አገሮች የተወጣጡ ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት እና ዓለማውያን ምእመናን የሚገኙበት በጠቅላላ 250 ተጋባእያን እንደሚያስተናግድ ገልጠው፣ ተጋባእያኑ የሳንዲያጎ ደ ካምፖስቴላ ታሪካዊ እና በቅዱሳት ሥፍራ መንፈሳዊ ንግደት ፈጽመው በርእሰ ሰበካው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዅሊያ ባሪዮ በሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚሳተፉም ለማወቅ ሲቻል፣ የስደተኞች እና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ በቅዱስ ሐዋርያ ያዕቆብ አማልጅነት የሚቀርበው የምህለላ ጸሎት ከተጋባእያኑ ጋር በመሆን እንደሚያቀርቡ ተገልጠዋል።

ጉባኤው ኢየሱስ በኤማሁስ ለሁለት ደቀ መዛሙርት መገለጡ በሚያወሳው በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ከቁጥር 13 እስከ 35 ባለው ቃለ ወንጌል ላይ በማተኮር በቁጥር 29 እነርሱ ግን ቀኑ መሽቶኣል ፀሐይም መጥለቅዋ ነው፣ ስለዚህ ከእኛ ጋር እዚህ እደር ብለው አጥብቀው ለመኑት፣ በዚህ ምክንያት ከእነርሱ ጋር ሊያድር ወደ ቤት ገባ በሚለው ቃል ላይ ያተኮረ አስተንትኖ እና ጸሎት እንደሚከናወንም ለማወቅ ሲቻል፣ በዚህ አጋጣሚም በኢራቅ የባግዳድ ተባባሪ ጳጳስ የብሩንዲ የኪጉንጎ ቅዱስ ሥፍራ አስተዳዳሪ ጳጳስ፣ የኵባ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር በእየሩሳሌም የቅዱስ መቃብር ባዚሊካ ምክትል አለቃ ምስክርነት እንደሚያቀርቡ አባ ቤንቶሊዮ ገልጠው፣ አቢያተ ክርስያናት እርስ በእርሳቸው በመቀራረብ የሚሰቃየው በሃይማኖት ነጻነት ረጋጣ ሳቢያ በችግር ላይ ለሚገኘው ቅርብ በመሆን ትብብር እና ድጋፍ የሚገለጠበት ጉባኤ እንድሚሆንም አስታውቀው፣ ተጋባእያኑ በዚህ ሳንቲያጎ ደ ካምፖስተላ ቅዱስ ሥፍራ የኢዮቤል ዓመት ምክንያት ቅዱስ አባታችን በሥፍራው ተገኝተው የሚያሰሙት መልእክት በማዳመጥ መሪ ቃል እንደሚቀበሉ ገልጠው የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.