2010-09-15 15:46:49

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በብሪታንያ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ታላቅ ብሪታንያን ይፋ ለመጐብኘት ነገ ሐሙስ ከሐዋርያዊ መንበራቸው እንደሚነሱ ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።

አንድ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብሪታንያን ይፋዊ ጉብኝት ሲያደርጉ በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ የመጀመርያ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መሆናቸ መግለጫው አመልክተዋል።

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሐዋርያዊ እና ይፋዊ ጉብኝት ልብ ለልብ ይናገራል የተሰየመ መሪ ቃል አንግቦ እነሚከናወን ያመለከተ የቫቲካን መግለጫ ጉብኝቱ እኤአ ከነገ ሐሙስ መስከረም ወር አስራ ስድስት እስከ ፊታችን እሁድ የሚዘልቅ መሆኑ መግለጫው አብራርተዋል።

ቅድስነታቸ በታላቅ ብሪታንያ በሚቆዩበት ግዜ ኤዲምበርግ ግላጎው ላንደን እና በርሚንግሃም ይጐበኛሉ

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ብሪታንያን የሚጐበኙ የሃገሪቱ ካቶሊካዊ ረኪበ ጳጳሳት ንግስት ኤልሳቤጥ ዳግማዊት እና መንግስት ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት እንደሆነ የማይዘነጋ ነው።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ በአስራ ዘጠነኛ ሚእተ ዓመት ንግስት ኤልሳቤት ዳግማዊት አባታቸው ንጉስ ጆርጅ ስድስተኛ ከዚህ ዓለም እንደተለዩ በሃያ ስድስት ዕድምያቸው ሰነ ሁለት በ1952 እኤአ የሃገሪቱ ንጉሳዊ ዘውድ እንደተረከቡት የሚታወስ ነው።

ንግስት ኤልሳቤት ዳግማዊት ከቀደምት አርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ አስራ ሁለተኛ ዮሐንስ ሃያ ሶስተኛ ከጳውሎስ ስደተኛ ጋር ቫቲካን ውስጥ መገናኘታቸው የሚታወስ ነው።

ይሁን እና ነገ ሐሙስ መስከረም አስራ ስድስት ቀን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ብሪታንያ እንደገቡ ንግስት ኤልሳቤጥ ዳግማዊት ኤዲምበርግ ከተማ ላይ በሚገኘው ሆሊሩድ ሃውስ መንግስታዊ አዳራሽ አቀባበል እንደሚያደርጉላቸው ቫቲኣክን አስታውቀዋል።

ቅድስት መንበር እና ታላቅዋ ብሪታንያ ከአንድ መቶ ሶውስት ዓመታት በፊት የጀመሩትን ግንኙነት በነዲክቶ ሀገሪቱ ውስጥ በሚያካሄዱት ይፋዊ ጉብኝት ይጠናከራል ተብሎ ተገምተዋል።

ንግስት ኤልሳቤጥ ዳግማዊት ከመጀመርያ ግዜ ከአንድ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተገናኙት እኤአ በ1953 ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ አስራ ሁለተኛ ሲሆን ከስምንት ዓመታት በኃላም ቫቲካን ውስጥ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ሃያ ሶውስተኛ ጋር መገናኘታቸው ተዘገብዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ በ1903 ንጉስ ኤድዋርድ ስድስተኛ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለኦን አስራ ሶውስተኛ በ1923 እኤአ የንግስት ኤልሳቤጥ ዳግማዊት አያት ንጉስ ጆርጅ አምስተኛ ቫቲካን ላይ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ አስራ ሀንደኛ መገናኘታቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውሰዋል።

ቅድስት መንበር እና ብሪታንያ የዲፕሎማቲክ ግንንኙነት የጀመሩት እኤአ በ1914 እንደሆነም መግለጫ አክሎ አስታውሰዋል።

ይሁን እና የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ብሪታንያ ይፋዊ ጉብኝት ምክንያት በማድረግ ላንደን ላይ የሚገኘው የእንግሊዝ እና ወይልስ ረኪበ ጳጳሳት የካቶሊክ ጥናት ቢሮ የካቶሊክ እምነት በተመለከተ መረጃ የሚሰጡ ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች አዘጋጅቶ ማሰማራቱ ከቦታው የደረሰ ዜና ገልጸዋል።

የእንግሊዝ እና ወይልስ ረኪበ ጳጳሳት ህዝብ ካቶሊካውነት በተመለከተ በሚገባ ለማስረዳት ከበርካታ ዓመታት ጀምሮ እንደሚንቀሳቀስ አብሮ የደረሰ ዜና አመልክተዋል።

የረሳም ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤድዊን ረገን እንዳመልከቱት የካቶሊካዊ እምነት ለመረዳት በብዙ ሺ ሚቆጠሩ ጠያቂዎች ደብዳቤዎች ልከዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤድዊን ረገን እንዳመለከቱት በአጠቃላይ እምነትን ለማወቅ የሚፈልጉ በርካታ ናቸው እና እነዚህን ለመርዳት ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች መሰማራታቸው እና እገዛ እየሰጡ ይገኛሉ ።

በየእንግላንድ እና ወይልስ ረኪበ ጳጳሳት የቆመ /a> , ድረ ገጽ ለዚሁ ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጠ መሆኑ ጳጳሱ አስገንዝበዋል።\

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በ1982 እንግሊዝ ላይ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንዳደረጉ ካቶሊካዊ እምነት የተቀበሉ በርካታ መሆንቸውም ብፁዕ አቡነ ኤድዊን ረገን አመልክተዋል።

እምነትንህን ለሌሎች ማጋራት ተገቢ ነው ያሉት አቡኑ የበነዲክቶስ ይፋዊ እና ሐዋርያዊ ጉንብኝት በመልካም አኳኀን ተጀምሮ እንዲፈጸም ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.