2010-09-04 09:39:34

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የእስራኤል ርእሰ ብሔር ተቀብለው አነጋገሩ ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ትናትና ረፋድ ላይ የእስራኤል ርእሰብሔር ሺሞን ፐረስን በካተል ጋንደልፎ ሐዋርያዊ አዳራሽ ተቀብለው አነጋግረዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲቶስ እና የእስራኤሉ ርእሰ ብሔር ሺሞን ፐረስ የቅድስት መንበር እና የእስራኤል መንግስት ግንኙነት እና በዚሁ ክልል የሚኖሩ ካቶሊካውያን ማሕበረ ሰቦች ሁኔታ በተለይ የመካከለኛው ምስራቅ ታሪካዊ ችግር ትኩረት የሰጠ ውይይት ማካሄዳቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

ቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ እና በቅድስት መንበር የውጭ ጉዳይ ዋና ተጠሪ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ በዚሁ ውይይት ተገኝተው ነበር ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና ርእሰ ብሔር ሺሞን ፐረስ የመካከለኛው ምስራቅ ህዝቦች በሰላም ለመኖር የሚያስችላቻው ብልሃት እንዲገኝ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አጽንኦት ሰጥተው ርእሰ ብሔሩን መጠየቃቸው ከግንኘቱ በኃላ የወጣ የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

ማንኛውም የዓመጽ ተግባር እንዲገታ እና ታሪካዊ የመካከለኛ ምስራቅ ዘላቂ መፍትሔ ማጝነት እንዳለበት ቅድስነታቸው እና ርእሰብሔሩ መግባባታቸው መግለጫው አክሎ አመልክተዋል።

ባለፈው ዓመት 2009 እኤአ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅድስት ሀገር ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉቡኝትም በዚሁ የትናትና ግንኙነት መዘከሩ የቅድስት መንበር እና እስራኤል የጋራ ኮሚስዮን በሚያካሄዳቸው ውይይቶ ዙርያ እና ያስመዘገበው ውጤት በተመለከተም ሁለቱ ባለስልጣናት መወያየታቸው ተገልጸዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ እና የእስራኤል ርእሰ ብሔር ሺሞን ከግንኘቱ ፍጻሜ በኃላ ስጦታዎች መለዋወጣቸውም ተዘግበዋል ።

ይሁን እና ይህ በቅድስነታቸው እና በየእስራኤሉ ርእሰ ብሔር ሺሞን ፐረስ መካከል የተካሂደው ግንኙነት ፡ በዩናይትድ ስቴትስ ዋሺንግቶን ላይ በየእስራኤል መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር በንያሚን ኔታንያሁ እና በየፍልስጢኤም ራስ ገዝ አስተዳደር መሪ ማሕሙድ ዓባስ የሰላም ድርድር ሂደት በሚካሄድበት ግዜ መከሰቱ ይታወቃል ።

የሰላም ድርድሩ እልባት እንዲኖረውም ሁለቱ ያላቸውን ተስፋ መግለጻቸው የቫቲካን መግለጫ አስገንዝበዋል ።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ የእስራኤል መንግስት እና ፍሊስጤም ባለስልጣናት እንደገና ፊት ለፊት ተገናኝተው ሲወያዩ ይህ ከሃያ ወራት በኃላ መሆኑ እንደሆነ ከዋሺንግቶ ተመልክተዋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በንያሚን ኔታንያሁ እናፕረሲዳንት ማሕሙድ ዓባስ በፕረሲዳንታ ባራክ ኦባማ ሸምጋይነት ዋሺንግቶን ላይ ለአራት ሰዓታት የተካሄደ የሰላም ድርድር ጠቃሚ እና ተስፋ ሰጪ መኖሩ በመካከለኛው ምስራቅ የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልእከተኛ ጆርጅ ሚሸል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄላሪ ሮድሃም ጠቅሰው ገልተዋል።

የሰላም ድርድሩ ረጂም እና ውጤታማ መኖሩ ጆርጅ ሚሸል በተጨማሪ መግለጣቸው ከዋሺንግቶን የደረሰ ዜና አስገንዝበዋል ።

የእስራኤል መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር በንያሚን ኔታንያሁ በእስርኤል እና ፍሊስጢኤሞች እውነተኛ ሰላም የሚገኘው ከኔ ይቅር ከኔ ይቅር ከተባባሉ እንደሆነ የሰላም ድርድሩ ሊጀመር ሲል ገልጠው ነበር።

እኔ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የእስራኤል ህዝብ ይህን ለማድረግ ዝግጁ ነን በማለት ኔታንያሁ መግለጻቸውም ይታወቃል።

ፍሊስጤማውያን የእስራኤል ህልውና እውቅና ከሰጡ እስራኤል ለነጻ ፓለስጢና እውቅና ለመስጠት እንደምትችልም ነው ኔታንያሁ አክለው የገለጹት ።



አቻቸው የፍሊስጤኤም ራስ ገዝ መሪ ማሕሙድ ዓባስ ፡ በበኩላቸው እስራኤል በአረብ ግዛቶች ላይ የምታካሄደው ሰፈራ ፍጹም እንድታቆም እና በጋዛ ሰርጥ ላይ የጣልቸው ማዕቀብ እንድታነሳው መጠየቃቸው ተገልጠዋል።

ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ የሰላም ድርድሩ የሚያበረታታ የሰላም ብልጭታ ማሰየቱ መግለጣቸው ተገልጠዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ኔታንያሁ እና ዓባስ ለሰላም ቆራጥነት ማሳየታቸው አመልክተዋል።

የእስራኤል መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር በንያሚን ኔታንያሁ እና የፍሊስጤም ራስ ገዝ መሪ ማሕሙድ ዓባስ እንደገና በዚሁ በተያዝነው መስከረም ወር አጋማሽ እንደገና እንደሚገናኙ በመካከለኛው ምስራቅ የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልእክተኛ ጆርጅ ሚሸል አስታውቀዋል ።

ከአሁን በፊት በሁለቱ ወገኖች መካከል እንዲህ ዓይነቱ የሰላም ደርድር ተካሄዶ ፍረ አልባ በመቅረቱ ይሳካል አይሳካም ከአሁኑ ለመተምበይ አስቸጋሪ እንደሆነ የፓሊቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ጋዛሰ ርጥን የሚቆጣጠር ሐማስ የፍሊስጤም ቡድን የሰላም ድርድሩ እንደሚቃወም ከወዲሁ እየገለጸ መሆኑ ሌላ ከኢየሩሳሌም የመጣ ዜና አስታውቅዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.