2010-09-01 16:48:58

የር.ሊ.ጳጳሳት ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ

እ.አ.አ በ1988 ዓም የእግዚአብሔር ኣገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የማርያም ዓመት ምክንያት በማድረግ፤ ‘ሙልየሪስ ዲግኒታተም’ በሚል ሓዋርያዊ መልእክታቸው ሴት ልጆች በቤተ ክርስትያን ሕይወት ያበረከቱትና እያበረክቱት ስላለው ወደር የሌለው ኣገግሎት ገልጸው ነበር። በመልእክቱ ቊ 31 ላይ “ቤተ ክርስትያን የሴት ልጆችን በታሪክ እንደተመዝገበ ለሰው ልጆች ሁሉና ለዓለም ኣገሮች መሃከል ስላበረከቱት ብልህ ኣገልግሎት ታመሰግናለች፤ በቤተ ክርስትያን ታሪክ ውስጥ የተለያዩ የሴት ልጆች ማኅበር በመምሥረት እውን ላደርጉት ስለ መንፈስ ቅዱስ ሥጦታዎች እንዲሁም በእርሳቸው በኩል ቤተ ክርስትያን በእምነት በተስፋ በፍቅር በመጨረሻም የዚህ ሁሉ ፍሬ የሆኑ ብዙ የሴት ልጆች ቅዱሳን በማበርከታቸው ታመስግናቸዋለች።’ ይላል።

በዘልማድ መህከለኛ ዘመን የምንላቸው የታሪክ ዘመንም ለሕይወት ቅድስናና ለትምህርት ሃብት ኣብነት የሆኑ የሴት ልጆች ብቅ ብለዋል፤ ዛሬ ከእነዚህ የሴት ልጆች ኣንድዋን በማስታወስ ለመጀመር እወዳለሁ፤ ይህች ቅዱስት የቢንገን ቅድስት ኢልደጋርዳ ናት፤ በ12ኛው ክፍለዘመን በጀርመን የኖረች ቅድስት ናት፤ በ1098 ዓም ረናንያ በበርመርሻይም በሚባል የኣልዘይ ኣውራጃ ተወለደች፤ ብዙ ጤናም ባይኖራት በ81 ዓመት ድሜዋ በ1179 ከዚህ ዓለም ከሞት ተለየች፤ ቤተ ሰቦችዋ ሃብታምና ከበርቴ ሆኖ ብዙ እኅቶችና ወንድሞች ነበርዋት፤ ወላጆችዋ ከሕጻንነትዋ ለእግዚአብሔር ኣገልግሎት ሰጥዋት። በ8 ዓመት ዕድሜዋ ሰብኣዊና ክርስትያናዊ ትምህርት ለማግኘት በቅዱስ ዲሲቦዶ የበነዲክታውያን ገዳመ ኅቡኣን ይቀመጡ ለነበሩ መምህር ጉዲታ ዘእስጳንሃይም ኣደራ ተሰጠች፡ የቅዱስ በነደቶ ሕግ በመከተል የሴት ልጆች የክላውዙራ ደናግል ማኅበር ገባች፤ ከብጹዕ ኣቡነ ኦቶነ የባንበርጋ ጳጳስ ልብሰ ድንግልና ተቀበለች፤ በ1136 ዓም የገዳሙ እመምኔት እናቴ ጉዲታ ከዚህ ዓለም በሞት በተለየችበት ግዜ ቅድስት ኢልደጋርዳ የገዳሙ ኣለቃ ሆነች የገዳሙ ደናግል ደግሞ እመምኔት እንድትሆን ጠርዋት። የገዳሙ መሪ ሆና ባገለገችበት ግዜ በጥበብ ያደገች ሴት እንዲሁም በመንፈሳዊነት ብስለት የተሞላች እንደመሆንዋ የገዳሙ ሕይወት በብቃት ኣስተዳደረችው። ከጥቂት ዓመታት በኋላ ከደናግሉ ጋር ለመቀላቀል ብዙ ወጣት ሴቶች የገዳሙን በር ስለኣንኳኩ ቅድስት ኢልደጋርዳ ሌላ ገዳም መሠረተች የቅዱስ ሩፐርቶ ገዳምም ብላ ሰየመችው ቀሪው ዘመንዋም እዛ ኣሳለፈችው። የሥልጣን ተል እኮዋን የተጠቀመችበት ኣገባብ ለማንኛውም ገዳማዊ ማኅበር ኣብነታዊ ነበር። ኣገባቡ መልካም ለማድረግ መወዳደርን የሚያነቃቃ ነበር፤ ከዘመኑ ምስክሮች እንደተመዝገበው እመምኔትዋና ደናግሉ እርስ ለእርሳቸእው ከፍ ለማድረግና ለማገልገል ይወዳደሩ ነበር።

ገና የቅዱስ ዲሲቦዶ እመምኔት በነበረችበት ጊዜ ቅዱስ ኢልደጋርዳ የተመስጦ ራእይ ታግኝ ነበር፤ በራእዩም መንፈሳዊ ምክር ታገኝ ነበር፤ በራእዩ የሚገልጡላትን ነገሮች ለቮልማር የሚባል መነኮስና እጅግ ትወዳት ለነበርችው ጸሓፊዋ እናቴ ሪቻርዲስ ዘእስትራደ በቃል ታጽፋቸው ነበር። የዚህ ዓይነት ራእይ ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከቅዠት እንዳይሆን ለማረጋገጥ ዘወትር እንደሚደረገው ቅድስት ኢልደጋርዳ የራእዮችዋ ምንጭ በደንብ ለማወቅ ሁኔታውን ጠንቅቀው በሚያውቁ ሰዎች እንድትመራ ሆነ፤ በዘመንዋ በቤተ ክርስትያን ታላቅ ታዋቂነት በነበረው በቅዱስ በርናርዶስ ዘኪያራቫለ ሥር ሆነች፤ ይህ ፍጻሜ ቅድስት ኢልደጋርዳን ኣረጋጋቶ ሰላምና ብርታት ሰጣት። ሆኖም ግን ብ1147 ዓም ኣንድ ኣስፈላጊ የራእዩ የማጽደቅ ፈቃድ ኣገኘች፤ ር.ሊ.ጳ ኤውጀንዮ 3ኛ በትረቪሪ ሲኖድ እየመሩ ከማጎንዛ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ኣቡነ ኤንሪኮ በቅድስት ኢልደጋርዳ ቃል ጽሕፈት የተጻፈውን መልእክት ካነበቡ በኋላ ራእይዋን እንድትጽፍና ለሕዝብ ስለዚሁ መንገር እንደምትችል ፍቃድ ሰጥተዋታል። ከዛ ዕለት ጀምሮ የቅድስት ኢልደጋርዳ መንፈሳዊ ክብረት እያደገ መጣ፤ የጊዜው ሰዎች እውነተኛ ነቢይት ብለው ይጠርዋት ነበሩ። የመንፈስ ቅዱስ እውነተኛ ተመኲሮ መከፈቻ ይህ ነው፤ በመንፈሳዊ ስጦታ ሃብታም የሆነ ሰው ኣይታበይም፤ ይልቅስ ለቤተ ክርስትያን በሙላት ይታዘዛል። ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ማንኛውም ጸጋ ቤተ ክርስትያይንን ለማነጽ ነው፤ ቤተ ክርስትያንም በበኲልዋ በእረኞችዋ ኣማካኝነት እውነተኛነቱን ታረጋግጣለች።

ስለዚህች ትልቅዋ ነቢይት እፊታችን ሮብ እንደግና እናገራለሁ፤ ዛሬ ለእኛም ሳይቀር በትልቅ እውነት ትናገናራለች፤ ብርታት ያለው ችሎታዋ ከግዜ ምልክቶች ባሻገር ለማወቅ ኣስችሎ ኣታል፤ ለተፍጥሮ ባላት ፍቅር፤ በሥነ ቀመም ዕውቀትዋ፤ በዘመናችን እንደገና በሚታደሰው ቅኔዋና ሙዚቃዋ ለክርስቶስና ለቤተ ክርስትያን ያላት ፍቅር፤ ያኔም በካህናትና በምእመናን ኃጢኣት ቈስላ ብዙ የተሰቃየች፤ የክርስቶስ ኣካል በሆነች ቤተ ክርስትያን እጅግ የተወደደች ቅድስት ኢልደጋርዳ ዛሬ ለእኛም በዚሁ ቋንቋ ትናገራናለች፤ እፊታችን ሮብ እንደገና እንናገራለን፤ ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.