2010-08-30 16:11:48

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የመልኣከ እግዚአብሔር ኣስተምህሮ (29.08.2010)


 “ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ በዛሬ እሁድ ወንጌል ከሉቃስ 14፡7~8 ኢየሱስ በኣንድ የፈሪሳውያን ኣለቃ ቤት ምሳ ሲበላ እንመለከታለን። በምሳ ጊዜ ኣንዳንድ ሰዎች የከበሬታ ስፍራ ሊይዙ ሲሽቀዳደሙ ባየ ጊዜ የሚከተለውን የሰርግ ግብዣ ምሳሌ ተርከላቸው፤ ‘ኣንድ ሰው ለሰርግ ግብዣ ሲጠራህ፤ ተሽቀዳድመህ በክብር ስፍራ ኣትቀመጥ፤ ምናልባት ከኣንተ የበለጠ ክብር ያለው ሰው ተጠርቶ ይሆናል፤ ታድያ ሁለታችሁንም የጋበዛችሁ ሰው፤ ወደ ኣንተ መጥቶ ‘ይህን ስፍራ ለዚህ ሰው ልቀቅለት’ ይለሃል፤ ያን ጊዜ በታላቅ ኃፍረት ወደ ዝቅተኛው ቦታ ወርደህ ትቀመጣለህ። ነገር ግን ለግብዣ ስትጠራ ሄደህ በዝቅተኛ ስፍራ ተቀመጥ፤’ ኣላቸው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምሳሌ የኑሮ ዘዴ ትምህርት ለመስጠት ወይም ስለ ሰዎች የኑሮ ደረጃ ኣይደለም የሚናገረው። ጌታ ለጥቆ የሚናገረው ስለትህትና ነው፤ በምሳሌው መጨረሽ ‘ምክንያቱም ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላልል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ግን ከፍ ይላል’ ሲል የትህትና ኣስፈላጊነት ይገልጣል። ይህ ምሳሌ ጠለቅ ባለ ትርጉሙ በእግዚአብሔር ጋር ካለን ግኑኝነት ስለእኛው የሰው ልጆች ስፍራ እንድናስብ ጥሪ ያቀርብልናል። የመጨረሻ ስፍራ የሚባለው በኃጢኣት ምክንያት ያሽቆለቆለውን የሰው ልጆች ሁኔታ ሊገልጥ ይችላል፤ ከዚህ ሁኔታ ነጻ ሊያወጣን የሚችል ከኣንድያ ልጅ ምሥጢረ ሥጋዌ ሌላ መንገድ የለም። ይህንን እውን ለማድረግ ጌታ ክርስቶስ ራሱ እጅግ ዝቅተኛ ሥፍራን ያዘ፤ ይህ ስፍራ እንደምናውቀው በዕጸ መስቀል መዋረድ ነው፤ በዚሁ ሥር ነቀል ትህትና ነው ጌታ ያደነን እንዲሁም ዘወትር የሚረዳንም በዚሁ ነው።

በምሳሌው መጨረሻ ላይ ኢየሱስ ጋባዡን ሰው እንዲህ ኣለው፤ የምሳ ወይም የራት ግብዣ በምታደርግበት ግዜ ብድራቸውን ለመመለስ በተራቸው ይጋብዙኛል ብለህ ተስፋ በማድረግ ወዳጆችህን ኣትጥራ፤ ነገር ግን ግብዣ በምታደርግበት ግዜ ድኾችን ኣካለ ስንኩሎችን ሽባዎችን ዕውሮችንም ጥራ’ ይለዋል። እውነተኛውን ወሮታ ወይም ካሣ የሚሰጠው እግዚአብሔር ነው። በደዩስ ካሪታስ ኤስት እግዚአብሔር ፍቅር ነው በሚለው ሓዋርያዊ መልእክት ቊ.35 ይህን ወሮታ ሊሰጥ የሚችለው ዓለምን የሚገዛ እግዚአብሔር ነው፤ እኛ የምናበርከተው ኣገልግሎት ከእርሱ የምንቀበለው ነው፤ ኃይል የሚሰጠን እርሱ ራሱ ነው፤’ ስንል ገልጠነዋል።

እንደገና የኢየሱስን ትህትና እንደ ኣብነት የተመለከትን እንደሆነ ከእርሱ በፈተና ግዜ ት ዕግሥት ማድረግን፤ ሌሎች በሚገፉን ግዜ በትህትና መቀበልን፤ በሥቃይ ግዜ ለእግዚአብሔር መታዘዝን፤ እርሱ ራሱ ‘ጓደኛ ና እዚህ ከፍ ባለ ቦታ ተቀመጥ’ በማለት ከሁሉ የበለጠውን ሥጦታ ማለት ከእርሱ ኣጠገብ መሆንን እስክንቀበል በትህትና መጠባበቅን ከኢየኡስ እንማራለን።

ባለፈው ሮብ በዓሉን ያስታወስነው የፈረንሳይ ንጉሥ የነበረ ቅዱስ ልዊጂ ዘጠነኛ ይህንን ሁሉ እተግባር ላይ ያዋለ በመጽሓፈ ሲራክ 3፡18 እንደ ትልቅነትህ መጠን ትህትና የተላበስክ እንደሆነ በጌታ ፊት ከፍ ትላለህ የሚለውን የተከተለ ትልቅ ቅዱስ ነው። ይህንን ቃላት በህይወቱ በመመስከሩ እንዲህ ሲል ጽፈዋል፤ ‘ለመንፈሳዊ ልጄ የሚሆን ኑዛዜ’ ጌታ ሃብት የሰጠህ እንደሆነ በትሕትና ማመስገን ብቻ ሳይሆን ክብር በመፈለግ እንዳትሳሳት ተጠንቀቅ እግዚአብሔር በሰጠህ ስጦታ በት ዕቢት እንዳታዛዝነው ጠንቀቅ በል’ ይላል።

ውድ ጓደኞቼ በዛሬው ዕለት ከኢየሱስ ነቢያት የላቀው የዮሐንስ መጥምቅ ሰማዕትነትንም እናስታውሳለን፤ ቅዱስ ዮሓንስ መጥምቅ ለመድኃኔ ዓለም ከፍ ያለ ቦታ ለመስጠት ራሱን የካደ ስለ እውነት ሲል የተሳቀየና የሞተ ነው፤ እመቤታችን ድንግል ማርያምን ለመለኮታዊ ወሮታ የተገባን እንድንሆን ወደ ትህትና መንገድ እንድትመራን እንለምናት፤” በማለት የመል ኣከ እግዚአብሔር ጸሎት ኣሳርገዋል።

ከጸሎቱ በኋላ ‘እ አ አ እፊታችን መስከረም 1 ቀን በጣልያን ጳጳሳት ጉባኤ የተዘጋጀ ተፈጥሮ የመጠበቅ ዕለት ስለሚታወስ፤ በዚሁ ዓመት የማስተላልፈው መል እክት ኣጠር ባለ መልኩ ‘ተፈጥሮን ማለት ኣከባብን በጥንቃቄ ካልያዝንክና ካላከበርክ በሰላም ለመኖር ኣይቻልም’፤ ለመጪው ኣዲስ ትውልድ በሚገባ ሊኖሩባትና ሊተብቅዋት የምትቻል መሬት እንድናስረክባቸው ግዴታ ኣለን፤ ጌታ ደግሞ ይህንን ለማድረግ ይርዳን ሲሉ ኣደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.