2010-08-23 13:47:24

የእስራኤል ፍልስጤም የሰላም ድርድር፡


የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት የእስራኤል መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር በንጃሚን ኔታናያሁ እና የፍሊስጤም ራስ ገዝ አስተዳደር መሪ ማሕሙድ ዓባስ ፊታችን መስክረም ወር ዋሺንግቶን ላይ የሰላም ድርድር ልማካሄድ ጥሪ ማቅረብዋ ይፋ መግለጫ መስጠትዋ ተመልክተዋል።

ከዋሺንግቶን እንደተገለጸው ፡ መሪዎቹ ለዓመታት እልባት ያልተገኘላቸው የክልሉ ዓበይት ችግሮች ይኽውም የድንበር ጉዳይ ፡ የኢየሩሳሌም ባለቤትነት ጉዳይ ፡ ውች የሚገኙ ፍልስጤማውያን ስድተኞች መመለስ ፡ እስራኤል በተያዙ የዓረብ ግዛቶች የምታካሄደው ሰፈራ መቆም፡ ለዚህ ሁሉ ዘላቂ መፍትሔ እንድያፈላልጉ የጠበቃሉ ።

ጠቅላይ ሚኒስትር በንጃሚን ኔታንያሁ እና ማሕሙድ ዓባስ በዩኤስ አመሪካ ባለስልጣኖች ሸምጋይነት ፊታችን መስከረም ወር ሁለት ቀን ዋሺንግቶን ላይ ሲገናኙ ፡ የግብጽ ፕረሲዳንት ሁስኒ ሙባራክ እና የዮርዳኖስ ንጉስ ዓብዱላህ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ይህ ከዋሺንግቶን የደረሰ ዜና አስገንዝበዋል።

እንዲህ ዓይነቱ የሰላም ድርድር በርካታ ግዜዎች ታካሄደው እልባት አልባ በመቅረታቸው በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም መፍትሔ ይገኛል የሚል ብሩህ ተስፋ አለ ለማለት እንደማይስደፍር የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ጠባቂ አባ ፒየር ባቲስታ ፒዛባላ መግለጣቸው ከቦታው የመጣ ዜና ያመልከታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.