2010-08-23 13:34:16

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ መልእክት ለሪሚኒ ጉባኤ፡


የሕብረት እና አርነት መንፈሳዊ ተቅዋም ሳላሳ አንደኛ አጠቃላይ ጉባኤ ባለፈው ዓርብ በሰሜናዊ ኢጣልያ ሪሚኒ ላይ በሀገረ ስብከቱ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ፍራንቸስኮ ላምቢያዚ መስዋዕተ ቅዳሴ መጀመሩ እና እየቀጠለ መሆን የሚታወስ ነው።

ይህ በየዓመቱ የሚካሄደው ጉባኤ በዓለም ህዝቦች መካከል ውዳጅነት እና ትብብር እንዲከሰት አበክሮ የሚጥር ጉባኤ እንደሆነ ይታወቃል።

ሁሉ የሰው ልጅ የሚመኘው ከልብ ይፍልቃል በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው የሕብረት እና አርነት ጉባኤ ሁሉም የአንድ ሕብረተሰብ ቅርጾች ያሳተፈ መሆኑ የማይዘነጋ ነው ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በየቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ በብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ በኩል ለሪሚኒ ጉባኤ መልእክት ማስተላለፋቸው እና መልእክትይ በተቋሙ ሊቀመንበር በኤሚልያ ጓርየሪ መደመጡ ተገልጸዋል ።

በእውነት የሰው ልብ በደስታ የሚሞላ እግዚአብሔር ብቻ መሆኑ የሰው ልጅ በራሱ በመተማመን የፈለገውን ነገር ገቢራዊ ለመድረግ የሚችለው በኃይሉ እግዚአብሔር ረዲኤት መሆኑ የቅድስነታቸው መልእክት ማመልከቱ ተገልጠዋል።

እግዚአብሔር ወዲዚህ ዓለም የመጣው የሰው ልጅ ለማዳን ከመሆኑ ባሻገር የሰው ዓበይት ምኞቶች ለማርካትም እንደሆነ የቅድሰነታቸው መልእክት መግለጹ ተመልክተዋል።

የሰው ልጆች በቀና መንፈስ እና ልብ የፈለጉትን ለእግዚአብሔር መጠየቅ እንደሚችሉ ሩሕሩሕ ፈጣሪ በአምሳሉ ለፈጠራቸው እንደሚራራ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለሪሚኒ ጉብኤ የላኩት መልእክት ማስረዳቱ ታውቆዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.