2010-08-23 14:15:51

እናትና ንግሥት የሆነች እመቤታችን ድንግል ማርያም ለዓለም ሰላም ታውርድ፤ የፍቅር ባህል እንድንገነባ ትርዳን


ይህንን ያሉት ቅዱስ ኣባታችን በነዲክቶስ ትናንትና ከዕረፍት ቦታቸው ካስተል ጋንደልፎ ሓዋርያዊ ኣደራሽ ባስተላለፉት የእኩለ ቀን የመልኣከ እግዚአብሔር ጉባኤ ኣስተምህሮ ላይ ነው። የትምህርታቸው ማእከል የነበረው ‘ሁላችን ለዓለም ሙሉ ሰላም እንድንጸልይ’ ሲሆን የዕለቱ ሥርዓተ ኣምልኮ እንደሚያስታውሰው ‘የእመቤታችን ድንግል ማርያም ንግሥነት’ ማእከል ያደረገ በመሆኑ ‘ይህን ትልቅ ሥልጣን ያስጨበጣት ትሕትና ስለተላበሰች ነው፤ እኛም ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ከእርሷ መማር ያለብን ይህ ነው፤ ትሕትና እንልበስ፤’ በማለት ስለ የዕለቱ ቃለ ወንጌል ኣስተምረኣዋል። ለነጋድያን በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታ ባቀረቡበት ወቅት በፈረሳይኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልእክት ደግሞ ‘ምእመናን እንግዶችን ኣለ ምንም የዘር መለያየት መቀበል እንዳለባቸው፤ ምክንያቱም ሁላቸው የሰው ልጅ ዘሮች ለደኅንነት የተጠሩ በመሆናችው’ ሲሉ በማመልከት፤ ባለፈው ሳምንት የፓሪስ መንግሥት በሮም በሚታወቁ የኤውሮጳ ዘላን ማኅበረሰብ የወሰዱት እርምጃ ትክክል እንዳልነበረ ኣመልክተዋል።

በዛሬው የላቲን ሥርዓተ ኣምልኮ ባለፈው ሳምንት እመቤታችን በሥጋዋና በነፍስዋ ወደ ሰማይ የመፍለስዋ ክብረ በዓል ቀጣይ ክፍል በመሆን ዛሬ ደግሞ ‘ንግሥት’ ተብላ መሰየምዋን ያስታውሳል። በትሕትና የሚገኝ ንግሥነት ስለሆነ እግዚአብሔር በትሕትንዋ እንደመረጣት የሚያመለክተው በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል በጸሎተ እግዚእትነ ማርያም የተመለከተው፤ ‘ዝቅተኛ ኣገልጋዪቱን ስለተመለከተ ነፍሴ እግዚአብሔርን ታከብራለች መንፈሴ በአምላኬ በመድኃኒቴ ትደሰታለች’ ማለትዋ እንዲሁም ‘ትዕቢተኞችንም ከነአሳባቸው በትኖኣቸዋል፤ ታላላቅ ገዢዎችን ከዙፋናቸው አውርዶኣቸዋል፤ ዝቅተኞችን ግን በክብር ከፍ አድሮጎኣቸዋል’ ያለችውን ጠቅሰው ‘እግዚአብሔር የዚህ ዓለም ትዕቢተኞችና ኃይለኞች ዝቅ ያደርጋል ትሑታንን ግን ከፍ ያደርጋል’ ብለዋል።

ቅዱስነታቸው የማርያምን ትሕትና ሲገልጹ፤ ‘ትንሽዋና ገርዋ የናዝሬት ልጃገረድ የዓለም ንግሥት ሆነች፤ ይህ የእግዚአብሔር ልብ ከሚገልጡ ኣስደናቂ ነገሮች ኣንዱ ነው፤ በታሪክ ውስጥ ይህንን የእመቤታችን ንግሥነት የሚከበሩበት ሁኔታዎች እጅግ ብዙ ናቸው፤ ኢየሱስ ይህችን ነው እንደ እናትና እንደ ንግሥት የተወልን፤’ ካሉ በኋላ ለትህትና እንዲህ ሲሉ ጸልየዋል፤ ‘በየዕለቱ ስለ ሰላም የምናቀርበውን ጸሎት ለኣማላድነትዋ እንቅርበው፤ በተለይ የዓመጽ ኣስተሳሰብ ባሳወራቸው ክፍሎች ሰላም እንዲገኝ በአጠቃላይ ሁላችን እንደወንድማሞች ኣንዱ ሌላውን እየረዳን የፍቅር ባህል ለመገንባት እንትረዳን እንዲህ በለን እንጸሊ፤ ኦ ንግሥተ ሰላም ማርያም ለምኚልን’ ሲሉ ስለ ሰላም ጸልየዋል።

ቅዱስነታቸው ስለ እመቤታችን ንግሥነት ሲገልጡ፤ ‘የእመቤታችን ማርያም ንግሥነት ክርስቶስ በመስቀል ከተዋረደ ብኋላ ከፍጥረት ሁሉ በላይ ከፍ በማለት ካሳየው ንግሥነት ጋር በሙላት የሚዛመድ ነው’ ብለዋል።

‘እመቤታችን ንጽሕት ድንግል ማርያም በጸጋ በተቃደው ዕቅድ በሙላት ከልጅዋ ምሥጢረ ሥጋዌ ጋር ኣንድ ሆነች፤ ይህ ኣንድነት ልጅዋ በናዝሬት በሥውር ባሳለፈው ምድራዊ ሕይወቱ እንዲሁም መሲሓዊ ሕይወቱ ክሱት በሆኖነበት ጊዜ በግልጽ ሲያስተምር፤ ከዛም በቀራንዮ ሕማምቱና ሞቱ በመሳተፍ በመጨረጻም ከሙታን ተለይቶ በመነሣትና ወደ ሰማይ በማረግ ሙሉ በሙሉ ተሳተፈች። በዚህም እመቤታችን ከልጅዋ ጋር የተካፈለችው ምሥጢራዊ የሆነ ሰብ አዊ ሕይወት ብቻ ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ የሆነው ምሥጢረ ሥጋዌ መለኮታዊ ፈቃድ በትህትናና በድህነት ያሳለፈችው ሕይወት ተለውጦና ከፍ ፍሎ በጠባቡ ደጅ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ኣማካኝነት ወደ ክብር ስታልፍ ማየት እጅግ ኣስደናቂ ነው። ኣዎ ትሑታን እና ቃለ እግዚአብሔር ሰምተው እተግባር የሚያውሉ ብቻ ሊያልፉት የሚቻለው ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ክርስቶስ በከፈተው መንገድ መጀመርያ ያለፈች ፍጥረት እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት።’ ካሉ በኋላ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ኣሳርገዋል።

ቅዱስነታቸው ጸሎቱን ካሳረጉ በኋላ ለነጋድያን በተለያዩ ቋንቋዎች ሰልማታ ባቀረቡበት ወቅት፤ በፈረንሳይኛ ቋንቋ ‘ሁላችን የሰው ልጆች ለደኅንነት የተጣራን ነን፤ ይህ የሚያስተምረን ነገር ካለ የተለያዩ ሰዎች በማኅበረሰባችን ውስጥ ሲገኙ ክርቶስ የዓለም ሕዝብ ኣንድ ለማድረግ እንደመጣው እኛም የተለያዩ ሰዎችን መቀበል ኣለብን፤ ወላጆች ልጆቻቸውን ለወንድማማችነትና እንግዳ የመቀበል ባህል እንዲኖራቸው እንዲያስተምሩ ኣደራ’ በማለት በተለያዩ ቋንቋዎች ኣመስግነው ሓዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት የዕለቱን ኣስተምህሮ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.