2010-08-23 13:42:20

ናይጀርያ ምርጫና ጸረ ሙስና ትግል፡


በምዕራባዊ አፍሪቃ በናይጀርያ የኢባዳን ክልል ጳጳሳት አጠቃላይ ጉባኤ መካሄዱ ከቦታው የተሰራጨ ዜና አመልክተዋል።

ከጉባኤው በኃላ የወጣ መግለጫ እንዳመለከተው፡ ጉባኤው ፊታችን ዓመት 2011 እኤአ ስለሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ሀገሪቱ ውስጥ የገነነው እና ፈውስ ያልተገኘለት ሙስና ትኩረት በመስጠት ከተወያየባቸው ነጥቦች ናቸው።

የናይጀርያ መንግስት መሪ ፕረሲዳንት ጉድላክ ዮናታን የነጻ አስመራጭ ኮሚሽን አዲስ እና ገለልተኛ የበላይ ሐላፊ መመረጣቸው አዎንታዊ መሆኑ የኢባዳን ጳጳሳት መግለጣቸው ተገልጸዋል።

ፍትሐዊ ነጻ እና ግልጽነት ያለው ብሔራዊ ምርጫ እንዲከናወን ዜጎች የዜግነት መብያቸው እንዲወጡ የኢባዳን ጳጳሳት ማመልከታቸው ተነግረዋል።

በሙስና ክስ የተመሰረታቸው ሰዎች ሁሉ ክሱ በተጨባጭ ከተረጋገጠ በተከሳሾቹ ሁነኛ ርምጃ መወሰድ እንደሚጠበቅ ጠቅሰው ሀገሪቱ በዚሁ አከፊ እና አሳፋሪ ተግባር ለበርካታ ዓመታት መሰቃየትዋ ማስገንዘባቸው ተመልክተዋል።

በህዝብ ብዛት ከአፍሪቅ ክፍለ ዓለም የላቀች ናይጀርያ ህዝብዋ ከስቃይ የሚላቀቅበት ሁኔታ መገኘት እንዳለበት የፖሊቲካ ሰዎች ሐላፍነታቸው እንዲወጡ ከጥቅማቸው ይልቅ የህዝብ ጥቅም እንዲያስቀድሙ በናጀርያ የኢባዳን ሀገረ ስብከት ጳጳሳት አጽንኦት ሰጥተው ማሳሰባቸው







All the contents on this site are copyrighted ©.