2010-08-18 17:54:33

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሐዘን ተለግራም


የሪፓብሊክ ጣልያን ኣገር ፕረሲደንት የነበሩ ክቡር ፍራንቸስኮ ኮሲጋ በ82 ዓመት ዕድምያቸው ትላንትና በሮም ሰዓት ኣንድ ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከቀትር በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ቅዱስ ኣባታችን ሐዘናቸው ለመግለጽና በጸሎት እንደሚያስብዋቸው ለመግለጥ ለጆርጆ ናፖሊታኖ የሪፓብሊክ ጣልያን ኣገር ፕረሲደንት እንዲሁም ለመዋቹ ልጆች ሁለት የተለግራም መልእክቶች እንደጻፉ ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና ኣመልክተዋል።

ለሪፓብሊክ ጣልያን ኣገር ፕረሰንት የተጻፈውን ተለግራም በር.ሊ.ጳ ስም ፊርማ ያሰፈሩበት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዝዮ በርቶነ ሲሆኑ ለመዋቹ ልጆች የተላከውን ተለግራም ግን የቅዱነታቸው ስም ሰፍሮበታል።

ከጥቂት ቀናት በፊት መዋቹ በጀመሊ ሆስፒታል ሲታከሙ ብፁዕ ኣቡነ ሪኖ ፊዚከላ ሁኔታቸውን ተከታትለው እንዲያሳውቁ በቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ስም በቅድስት መንበር ተወክለው ነበር።

የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዝዮ በርቶነ በቅዱስነታቸው ስም ለጣልያን ኣገር ፕረሲደንት ጆርጆ ናፖሊታኖ በጻፉት ተለግራም ‘በሪፓብሊክ ጣልያን ኣገር ፕረሲደንት በመሆን ለጣልያን ሕዝብ ያገለገሉ ክቡር ፍራንቸስኮ ኮሲጋ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ኃዘን ለእርስዎ ለመላው ጣልያን ኣገር ሕዝብ ይገልጣሉ፤ ለመዋቹም ጸሎት እያሳረጉ ነው’ በማለት የቅዱስነታቸው ሱታፌ ይገልጣል።

ቅዱስ ኣባታችን ወደ ጁሰፐና ኣናማርያ ኮሲጋ በላኩት ተለግራም ደግሞ ‘ወላጅ ኣባታቸውን በማጣት በኃዘን በሚገኙበት ወቅት በመንፈስ ከእናንተ ጋር በመሆን የሓዘናችሁ ተሳታፊ መሆኔን እገልጣለሁ፤ ኣባታችሁ ፍራቸስኮ ኮሲጋን ሳስታውስ ካቶሊካዊ በመንፈሳዊና በዓለማዊ ትምህርት ያሳየውን ብስለትና ያበረከተውን ኣገልግሎት የሃገሪቱና የሕዝቡ የጋራ በጎ ሥራ ለማራመድ ያሳየው ልግሥና ኣስታውሳለሁ፤ ስለ ነፍሳቸው ባሳርገው ጸሎት እግዚአብሔር ነፍሱን ይማር ዘለዓለማዊ ሰላምም ይስጣት እያልኩ ለእናንተና ለሁሉም ቤተ ዘመድ የሚያጽናና ሓዋርያዊ ቡራኬ እልክላቸዋለሁ’ ሲሉ የተሰማቸውን ጥልቅ ሓዘን ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.