2010-08-12 16:35:32

በክዩባ አዲስ ቤተ ክርስትያን ተመርቀዋል


ባለፈው ቅዳሜ ካዮ ኤስፒኖ በተባለ የክዩባ መንደር በመድኃኔ ዓለም ባያሞ ማንዛኒሎ ሰበካ ኣዲስ ቤተ ክርስትያን እንደተመረቀ ከቦታው የደረሰ ዜና ኣመልክተዋል፤ ቤተ ክርስትያኑን ለማነጽ እርዳታ የሰጡ የጀርመን ካቶሊካውያን ጳጳሳትና ምእመናን መሆናቸውም ከዜናው ጋር ኣብሮ የደረሰን መግለጫ ያመለክታል። ሁኔታውን ልዩ የሚያደርገው በሰብካውም ይሁን በመላው ክዩባ ከረዥም ዓመታት እንዲህ ዓይነት ኣጋጣሚ ስላልታየ ነው፡ የኣዲሱ ቤተ ክርስትያን ቅድስት ጠበቃ እመቤታችን የካሪዳድ ደል ኮብረ ድንግል ማርያም መሆኑም ተመልክተዋል፤ እፊታችን 2012 ዓም የዚች ድንግል ማርያም ሓውልት የተገኘበት 400ኛ ዓመት ክብረ በዓል እንዲከበር ብዝግጅት ላይ መሆኑና ተኣምራታዊት ሓውልት መሆንዋም ተገልጦኣል። ሥር ዓተ ቡራኬውን ያካሄዱና የመጀመርያውን መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የሰበካው ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኣልቫሮ በይራ ሉዋርካ መሆናቸው እንዲሁም የማንዛኒሎ ቆሞስ አባ ማንወል ጎንሳለዝ ኢሳም ከጳጳሱ ጋር ኣብረው ቀድሰዋል። ብፁዕ አቡነ በይራ ብስብከታቸው “ቤተ ክርስትያን ዘወትር የእግዚአብሔር ቤት ነው የእግዚአብሔር ቤትም የሁሉ ቤት ነው፤ በዚህም ቤት ከእግዚአብሔር ጋር መናገርን እንማራለን፤ በዚህ ቤት እንጸልያለን፤ በዚህ ቤት እናስተነትናለን፤ በዚህ ቤት መሥዋዕተ ቅዳሴ እናሳርጋለን” ብለዋል። የቤተ ክርስትያኑ ዕቅድና ሕንፀት ኣስመልክተው ደግሞ “ተኣምር ነው” ካሉ ብኋላ እውን ለሆነው ሕልም ባደረጉት እርዳታ ደግሞ ለጀርመን ካቶሊካውያን ም እመንና ጳጳሳት ኣመስግነዋል። እንዲሁም በሕንጸት ወቅት ጉልበታቸው ገንዘባቸውና እውቀታቸው ኣለምንም ገደብ በነጻ ላበረክቱ ክዩባውያንንም ኣመስግነዋል። ብፁዕነታቸው በመጨረሻ ለሁሉም የሚነካ ንግግር “እንዲሁ ዓይነት ተኣምር እውን ሊሆን ከተቻለ ለምንድር ነው ሕይወቶቻችን በጌታ ኢየሱስ የማይለወጡ፧ ይህ ጊዜ የተሰጠን እያንዳንዳችን ወደ ላይ ወደ ሰማይና ወደ ፊትም በመመልከት ልዩ በሆነ ኣመለካከት እግዚአብሔር ሕይወታችንን መለወጥ እንደሚችል እናስታውስ፤ እንደ ቤተ ሰብ እንድንኖር ጥሪ ያቀርብልናል፤ እንደ ወንድማሞች ማኅበር፤ እንደ ቤተ ክርስትያን እንኑር እርሱ እዚህ መሀከላችን በዚሁ ኣዲስ ቤተ ክርስትያን ኣለ። ሲሉ ሕንጻው ሳይሆን ቤተ ክርስትያን ም እመናን መሆናቸውን ኣብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.