2010-08-12 16:33:07

ቅዱስ ኣባታችን በካርፒነቶ ሮማኖ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ፕሮግራም ይፋ ሆነ


የቫቲካን የኅትመት ክፍል ቅዱስ ኣባታችን ር እሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ እ.አ.አ እፊታችን መስከረም 5 ቀን 2010 ዓም በካርፒነቶ ሮማኖ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ፕሮግራም ይፋ እንዳደረገ ከቅድስት መንበር የወጣ መግለጫ ኣስታውቀዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን ሐዋርያዊ ጉብኝት የሚፈጽሙበት ዋና ምክንያት የስመ ጥር ር.ሊ.ጳ ልዮን 13ኛ ልደት 200ኛ ዓመት ለማስታወስ መሆኑንም ከመግለጫው ተያይዞ የመጣ ማብራርያ ኣመልክተዋል።

ቅዱስነታቸው በተጠቀሰው ዕለት እንደ ሮማ ሰዓት ኣቆጣጠር ልክ 8፡30 በሄሊኮፕተር ከበጋ ዕረፍት ቦታቸው የካስተል ጋንደልፎ ሐዋርያዊ ኣደራሽ ይነሣሉ። 9፡15 ደግሞ በላርጎ ደይ ሞንቲ ለፒኒ የከተማዪቱ ነዋሪዎች ይቀበልዋቸዋል፡ 9፡30 መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ፡ 11፡45 የመል ኣከ እግዚአብሔር ኣስተምህሮና እንዲሰጡ እንዲሆም ጸሎት እንዲያሳርጉ በሄሊኮፕተር ወደ ካስተል ጋንደልፎ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።








All the contents on this site are copyrighted ©.