2010-08-06 11:36:33

የስደተኞች መኖር ምስዮናዊት ለሆነችው ቤተ ክርስትያን እንድትታደስ ያስገድታታል


የወርኃ ነሐሴ የር.ሊ.ጳጳሳት ጸሎት ቤተ ክርስትያንና ስደተኞችን የተመለከተ መሆኑን የስደተኞች ማእከል ዳይረክተር የሆኑ ኣባ ጃንፎማኖ ግነሰቶ ኣመልክተዋል። የጸሎተ ይዘት የሚከተል ነው። ቤተ ክርስትያን የሁሉ ቤት እንድትሆን፤ “በዘር ኣድልዎና በሃይማኖት መለያየት ምክንያት እንዲሁም ረሃብና ውግያ ኣስጨንቆኣቸው ወደ ሌሎች ኣገሮች ለሚሰደዱ በሮችዋን ለመክፈት ዝግጁ እንድትሆን እንጸሊ፤” ይላል።

“የሰው ልጆች ከቦታ ወደ ቦታ መሰደድ ለቤተ ክርስትያንና ም እመናንዋ ስለባህርያቸው ተጨባጭ ምልክት ይሰጣል፤ ቤተ ክርስትያን በዚች ምድር እንደ ንግደት ስለምታልፍ ስደተኞች ደግሞ እንደ ቤተ ክርስያን ባህርይ በጉዞ ላይ ያለ ሕዝብ በመሆኑ ቤተ ክርስትያንም በጉዞ ላይ ሕዝብ ስለሆነች የስደተኞች ጉዳይ በቀጥታ ይነካታል፤ ስለ ምንነትዋ እንድታስተነትንና ክፍት እንድትሆንም ያስገድታታል። ልክ ኣንድ ስደተኛ እግሩ በመሬት ላይ ሓሳቡ ወደሚቀበለው እፎይ ብሎ ወደሚቀመጥበት ኣገር እንደሆነ፤ ቤተ ክርስትያንም በዚች ምድር እስካለች እግርዋ በዚህ ምድር ላይ ቢቆምም ልብዋና ኣሳብዋ ወደ ሰማይና ሰማያዊ ነገሮች መሆን እንዳለበት ዘወትር ማስታወስ ኣለባት።

በየቁምስናው በየሰበካው እያንዳንዱ ክርስትያን ማሰብ ያለበት “ስደተኛ ሁል ግዜ ወንድማችን እኅታችን መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፤ ጌታ በማቴዎስ ወንጌል ስለ መጨረሻው ፍርድ ሲናገር እንግዳ ሆኜ ተቀበላችሁኛል ሲል እያንዳንዱ ስደተኛ የጌታ ኣምሳል መሆኑን በማስታወስ ለስደተኛ የምናደርገው ሁሉ ለኢየሱስ እንዳደረገው መሆኑንም መዘንጋት የለብንም። ይህ መሠረታዊ ትምህርተ ክርስቶስ በመሆኑ በኣዲስ መንፈስ እግብር ላይ መዋል ያለበት ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.