2010-08-02 18:03:45

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (01.08.2010)


ቅዱስ ኣባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና ረፋድ ላይ ለዕረፍት ከሚገኙት ካስተል ጋንደልፎ ሓዋርያዊ ኣደራሽ በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ ምእመናን በዚህ ሳምንታ ዝክረ በዓሉ ለተስታወሰው የኢየሱሳውያን ማኅበር መሥራች የልዮላ ቅዱስ ኢግናጽዮስ የተመለክተ ትምህርት ሰጥተው የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ካሳረጉ በኋላ ትላንትና ገቢራዊ ለሆነው ተፈናጣሪ ቦምብ የሚከልክል ስምምነት ኣዎንታዊነት ጠቅሰው ኣወድሰዋል።

ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በፊት ይህን ትምህርት ሰጥተዋል፡ “ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ በዚሁ ቀናት የኣንዳንድ ቅዱሳን ዝክረ ሥርዐተ ኣምልኮ ተካሂደዋል፡ ትናንትና የኢየሱሳውያን ማኅበር መሥራች የልዮላ ቅዱስ ኢግናጽዮስ በዓል ተከብረዋል፤ ቅዱስ ኢግናጽዮስ በ14ኛው ክፍለ ዘመን ኖረዋል፤ ሕይወቱን በውግያ ባጋጠመው የመቁሰል ኣደጋ በነበረው ረዥም ጊዜ የኢየሱስ ሕይወትና የቅዱሳን ሕይወት በማንበብ ለውጠዋል። በንባቡ እጅግ ስለተሳበ ኢየሱስን ለመከተል ወስነዋል። ዛሬ ደግሞ የረደንቶሪስት ማኅበር መሥራች በ18ኛ ክፍለ ዘመን የኖረ ቅዱስ ኣልፎንሶ ማርያም ደ ሊግዎሪ ይዘከራል፤ ስመ ጥርና ዝክረ ጥዑም ር.ሊ.ጳ ፕዮስ 12ኛ የንስሓ ኣባቶች ጠበቃ ብለው ሰይመውታል። እግዚአብሔር ቅዱሳን ሁሉ እንደየችሎቻቸው እንዲኖራቸው የፈለገውን ጥበብ ለቅዱስ ኣልፎንሶ ለግሦለታል። እንዲሁም በዚህ ሳምንት የሰሜን ጣልያን ኣገር ኣውራጃ የሆነችው የፕየሞንተ የመጀመርያ ጳጳስ ቅዱስ ኤውሰብዮ በዓል ይዘከራል፤ ቅዱስ ኤውዘብዮ የኢየሱስ መለኮታዊነትን ያስተማረና የተከላከለ ቅዱስ ነው። በመጨረሻም በቅርቡ ጊዜ ለተፈጸመው የካህን ዓመት በሕይወቱ ኣብነትና ምሳሌ የመራው የኣርስ ቆሞስ ቅዱስ ዮሓንስ ማርያም ቫያኒ በዚሁ ሳምንት ይዘከራል፡ በዚሁ ኣጋጣሚ የሁላቸው የቤተ ክርስትያን እረኞች ተልእኮ በእርሱ ኣማጥናለሁ።

የሁላቸው ቅዱሳን የጋራ ተልእኮ ነፍሳትን ማዳንና በተሰጣቸው ጸጋ ቤተ ክርስትያንን እያሳደሱና ሃብታም እያደረጉ እርሷን ማገልገል ነው። ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 90 ቊ 12 እንደሚለው እነኚህ ሰዎች የጥበብ ልቦና ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው መሠረት የማይበላሽ ሃብትን በመምረጥና ከጊዜ ጋር የሚለዋወጠውን ሥልጣን ምድራዊ ሃብትና ምቾትን በመመነን ድል ተቀዳጅተዋል፡ እግዚአብሔርን በመምረጥ የሚያስፈልጋቸውን ኣገኝተዋል፤ ስለዚህም ገና በዚች ምድር እያሉ ሰማያዊ ሕይወትን ኣጣጥመዋል።

በዛሬ እሁድ ወንጌል ኢየሱስ ከሕዝቡ መካከል “መምህር ሆይ! ኣባታችንን ያወረሰንን ርስት እንዲያካፍለን እባክህ ለወንድሜ ንገረው” ካለው ጥያቄ በመነሣት እውነተኛ ጥበብን የተመለከት ትምህርት ይሰጠናል። ኢየሱስ ይህንን ጥያቄ ሲመልስ የሃብታሙ ሰው ሞኝነት እንደ ምሳሌ በማቅረብ የሚሰሙትን ከምድራዊ ሃብትና የንብረት ተገዢ ከመሆን ነጻ እንዲሆኑ “የሰው ሕይወት በሃብት ብዛት ኣይደለም፤ ስለዚህ ከመጐምዠትና ከስግብግብነት ተጠበቁ ተጠንቀቁም” በማለት ያስጠነቅቃል፡ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 12 ከቊጥር 16 እስከ 21 ተጽፎ ያለው የሞኙ ሃብታም ሰውየ ታሪክ እንዲህ ነው፤ አንድ ባለ ጠጋ ሰው እርሻ እጅግ ፍሬያም ሆነችለት። እርሱም። ፍሬዬን የማከማችበት ስፍራ አጥቻለሁና ምን ላድርግ? ብሎ በልቡ አሰበ። እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጐተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፥ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤ ነፍሴንም። አንቺ ነፍሴ፥ ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ፤ ዕረፊ፥ ብዪ፥ ጠጪ፥ ደስ ይበልሽ እላታለሁ አለ። እግዚአብሔር ግን። አንተ ሰነፍ፥ በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል? አለው። ለራሱ ገንዘብ የሚያከማች፥ በእግዚአብሔር ዘንድም ባለ ጠጋ ያልሆነ እንዲህ ነው።” ይላል። በዚህ ምሳሌ የተጠቀሰው ሞኝ ሰው የዚህ ዓለም ሃብት ለዘለዓለም እንዳልሆነ ወጣትነት ኃይልና ጉልበት ምቾትና ሥልጣን ሁሉ እንደሚያልፍና ግዝያዊ መሆኑን ከሕይወት ተመኲሮ የማይማርን ሰው ሁሉ ያመለክታል። የባሰውኑ ሞኝነት ደግሞ ሕይወቱን በእነዚህ ኣላፊ ነገሮች ማስጠጋት ነው። በእግዚአብሔር የሚታመን ሰው ግን የሕይወት ጭንቅ ኣያስፈራውም የማይቀር ሞትም ኣያስደንግጠውም፤ ይህ እንደ ቅዱሳኑ ጥበበኛ ልብ የታደለ ነው።

ጸሎታችንን ወደ ቅድስት እመቤታችን ድንግል ማርያም በምናቀርብበት ባሁኑ ግዜ ሌላ ኣስፈላጊ ነገር ለማውሳት እፈልጋለሁኝ፤ ነገ የኣሲዚው ምሕረት ሥሬተ ኃጢኣት የሚታደልበት ነው፤ ይህ ሥሬተ ኃጢኣት ቅዱስ ፍራንቸስኮስ በ1216 ዓም ከር.ሊ.ጳ ኦኖርዮ 3ኛ ያገኘው ነው፡ እፊታችን ነሓሴ 5 ቀን በ431 በኤፈውሶን ጉባኤ ለእመቤታችን የተሰጠው “የእግዚአብሔር እናት” የሚለውን ቅጽል በመድገም በዓልዋን በሳንታ ማርያ ማጆረ ባሲልካ ልናከብር ነው፤ እንዲሁም ስመጥር ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ 6ኛ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩበትን ኣርብ ዕለት እናስታውሳለን፤ ነሓሴ 6 ቀን ደግሞ የበጋው ብርሃን መገማደጃ በመሆኑ የክርስቶስ ኣንጸባራቂ ገጽታ መላውን ዓለም እንዲያበራ በማመን የደብረ ታቦርን በዓል እናስታውሳለን፤ ካሉ በኋላ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ኣሳርገዋል።

ከመልኣከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ፤ ትላንትና ገቢራዊ ለሆነው ተፈናጣሪ ቦምብ የሚከልክል ስምምነት ኣዎንታዊነት ጠቅሰው በማወደስ ኣብሮዋቸው ለመጸለይና ስብከታቸውን ለመስማት ለተሰበሰቡት ምእመናንና ነጋድያን በተለያዩ ቋንቋዎች ኣመስግነው ሓዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.