2010-08-02 18:07:53

የፖርዚኡንኮላ ሥሬተ ኃጢኣት በዓል


በኣሲዚ ምሕረት የሚታወቀው የሥሬተ ኃጢኣት ጻጋ የሚገኝበት ምርጥ ግዜ ትናንትን ተጀምረዋል።

ቅዱስነታቸው በመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ትምህርት እንዳመለከቱት ከኣሲዚ ጥቂት ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው የፖርዚኡንኮላ ቤተ ክርስትያን ስም የሚታወቀው ማለት የፖርዚኡንኮላ ሥሬተ ኃጢኣት በዓል ለብዙ ምእመናን እምነታቸው እንደገና ለማሳደስ የሚጠቅም ኣጋጣሚ ነው።

የመላእክት ማርያም ጳጳሳዊ ባሲሊካ የፖርዚኡንኮላ ተግባር ኃላፊ የሆኑ የን ኡሳን ኣኃው ካፑቺኒ ኣባል ኣባ ሳውል ታምቢኒ የዚህ በዓል ትርጉም ሲገልጡ፤ “ለዘመናት እንኳ የተጓዘ ቢሆን “ምሕረት” የሚለው ቃል ዘወትር ኣዲስ ዘወትር ትርጉም ያለው ለመንፈሳዊ ሕይወት ብቻ ሳይሆን ለማኅበረሰባዊ ሕይወትም ትልቅ ዕሴት ያለው ቃል ነው፤ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ብ1216 ክ ኡምብርያ ጳጳሳት ጋር በመሆን ‘ለሁላቸው ወደ መንግሥተ ሰማያት እንድትመሩ እፈልጋለሁ’ ባለው መሠረት ኣሁንም ከሁሉም የዓለም ክፍሎች እዚህ የሚመጡ ምእመናን ከእግዚአብሔር ምሕረት ጋር የሚያያዝ መሠረታዊ ምክንያት መፈለግ ኣለባቸው። በየዓመቱ ነሓሴ 2 ቀን ለብዙዎች ልዩ ቀን ሊሆን ይችላል፤ የገዛ ራስየን ምስክርነት ለመስጠት ደስ ይለኛል፤ ከብዙ ዓመታት በፊት በዚሁ ቀን በዚሁ ፖርዚኡንኮላ መንበረ ኑዛዜ በሕይወቴ ውስጥ ትልቅ ለውጥ ተከናውነዋል፤ የዚህ ዓይነት ምስክርነት የሚሰጡ ብዙ ሰዎች ኃጢኣታቸውን ለመናዘዝ እዚህ መጥተው ሲመለሱ እውነተኛ ለውጥ የሚያገኙና የሚያደርጉ እንዳሉ ቅላቸውን ይሰጣሉ፡ ዛሬም ቢሆን ወጣቶችም ይሁኑ ኣዛውንቶች ኣለ ዕድሜ ገደብ እየጐረፉ ናቸው። በማለት የሥሬተ ኃጢኣቱ ኣዋጅ ለብዙ ምእመናን የጸጋና የንስሓ ግዜ መሆኑን ኣብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.