2010-07-30 16:37:56

ብፁዕ ካርዲናል ኢቫን ዲያስ ለቻይና ጳጳሳት እና ካህናት መልእክት ልከዋል


በቅድስት መንበር የስብከተ ቅዱስ ወንጌል ማሕበር የበላይ ሐላፊ ብፁዕ ካርዲናል ኢቫን ዲያስ ለህዝባዊት ቺና ጳጳሳት እና ካህናት መልእክት ማስተላለፋቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አመልክተዋል።

መልእክቱ የዓመተ ክህነት ፍጻሜ መሠረት ያደረገ መሆኑ የጠቆመ ፊደስ ችግር እና ስቃይ ቢኖርም የሀገሪቱ ሐዋርያዊ እረኞች ለማስተባበር እና በጋርዮሽ ለመስራት የቻይና ጳጳሳት እና ካህናት አበክረው እንዲሰሩ የሚጠይቅ መልእክት መሆኑ መግለጫው አስታውቀዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በመንፈስ ከየቻይና ጳጳሳት ካህናት እና ምእመናን መሆናቸው ሐዋርያዊ ስራቸው ስኬታማ እንዲሆን እንደሚጸልዩ መልእክቱ ማስገንዘቡ የዜና አገልግሎቱ ለጥቆ ገልጸዋል።

በርካታ የህዝባዊት ቻይና ጳጳሳት እና ካህናት ሩቅ ባልሆነ ግዜ ለካቶሊካዊ እመንታቸው እና ከሮማዊት ቤተክርስትያን ጋር ያላቸውን ትስስር ገሃድ ለማድረግ መሰቃየታቸው እውቅ መሆኑ በቅድስት መንበር የስብከተ ቅዱስ ወንጌል ማሕበር የበላይ ሐላፊ ብፁዕ ከርዲናል ኢቫን ዲያስ የላኩት መልእክት እንደሚያመልክት ተውሰተዋል።

በህዝባዊት ቻይና ዜና ሰናየ ለመዘርጋት የሀገሪቱ ጳጳሳት ካህናት እና ምእመናን በየፊናቸው የሚያካሄዱት መንፈሳዊ ጥረት የሚመስገን መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ኢቫን ዲያስ ለቻይና ጳጳሳት እና ካህናት የላኩት መልእክት መጥቀሱ ተገልጸዋል።

መልእክቱ ባለፈው ሰነ ወር የተጠቃለለው ዓመተ ካህን አስታውሶ ፡ ቅዱስ ዮሐንስ ቪያነይ ዘክሮ ካህን ሁለንትናው ለእግዚአብሔር ያደረ መሆን እንደሚጠበቅበት እና በጸሎት እና ተጋድሎ የተጠመደ እንዲሆን እንደሚጠበቅ አጽንኦት ሰጥቶ ማመልከቱ የመልእክቱ ግልባጭ ያገኘ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስገንዝበዋል።

የቻይና ጳጳሳት እና ካህናት ከ500 መቶ ዓመታት በፊት ቻይና ውስጥ ቅዱስ ወንጌል የሰበኩ እና እዚያው ሕይወታቸው ያሳለፉ የኢየሱሳዊ ካህን አባ ማተኦ ሪቺ አርአያ እንዲከተሉ መልእክቱ መጠየቁ የዜና አገልግሎቱ አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.