2010-07-28 12:18:37

የመካከለኛ ምሥራቅ ሲኖዶስ


የኢየሩሳሌም ኣርመናውያን ካቶሊካውያን ፓትርያርካዊ ኤዛርቃ የመካከለኛ ምሥራቅ ሲኖዶስ ኣስፈላጊነት ላይ ኣስምረውበታል:: እፊታችን ጥቅምት ወር በቫቲካን ሊካሄድ ተወጥኖ ያለው የመካከለኛ ምሥራቅ ሲኖዶስ ስለምሥራቃዊት ቤተክርስትያን ለማብራራት ጥሩ ኣጋጣሚ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ምሥራቃዊት ቤተ ክርስትያን የኣርመን የግሪክ ኦርቶዶክስ እና የግሪክ ካቶሊክ በመሆን በተለያዩ ቦታዎችና ባህሎች በመገኘትዋ በተለያዩና በብዙ ችግሮች ተከባ ትሮራለች።

የኢየሩሳሌም ኣርመናውያን ካቶሊካውያን ፓትርያርካዊ ኤዛርቃ ብጹዕ ኣቡነ ራፋኤል ሚናስያን ለቫቲካን ረድዮ በሰጡት ማብብራርይ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገሩ፤ “እውነት ነው፤ እነኚህ ኣገሮች ዲሞክራስያውያን ተብለው ይጠራሉ፤ ሃሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነት እንዲሁም የሃይማኖት ነጻነት ወተ ኣለ ተብሎ ይታወጃል፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ብዙ ችግር ኣለ፤ ካንዱ ኣገር በሌላው ኣገር ኣብሮ የመኖር ሽግር ኣለ፤ እንደ ክርስትያን ለመኖር ማንነትን ለመግለጥም ችግር ኣለ፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ችግሩ እየባሰ ነው ያለው፤ ሃሳብን በነጻ የመግለጥና የእምነትና የባህል ነጻነት ስለሌለም ስደትና መፈናቀል ያበቃል ብሎ መናገር ኣይቻልም፤ በተለይ እንደ ቱክ የመሳሰሉ የእስልምና ተከታዮች የበዙባቸው ኣገሮች ይህ ችግር በብዛት ኣለ፤። ዘወትር በፖሎቲካም ይሁን በኅብረተሰብ እንዲሁም በሃይማኖት በኩል በመልካም ኣይን ኣይመለከቱንም፤ በሲኖዱሱ እንድንወያይባቸውና መፍትሔ ለማግኘት የምንሻቸው ነጥቦች፤ የክርስትና እምነትን በዚሁ ኣስቸጋሪ ሁኔታ እንዴት መኖር ይቻላል፧ እንዲሁም ም እመናኖቻችን በምስራቁ ክፍል እንዴት ይኑሩ፧ በሚሉ ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ መፍትሔ ያገኛል ተብሎ ይጠበቅበታል”፤ ሲሉ የመካከለኛ ምሥራቅ ሲኖዶስን በጉጉት እንደሚጠብቁት ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.