2010-07-28 16:42:08

የሎርድ ክሪስቶፈር ፓትን መግለጫ፡




ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ፊታችን መስከረም ወር አጋማሽ ላይ ታላቅዋ ብሪታንያ ለመጐብኘት እቅድ እንዳላቸው የሚታወስ ነው ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በታላቅዋ ብሪታንያ ይፋዊ ጉብኝት ሲያደርጉ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የመጀመርያ መሆናቸው ነው ።

ይሁን እና ቅድስነታቸው ፊታችን ወራ መስከረም ከአስራ ስድስት እስከ አስራ ዘጠኝ ቀን ታላቅዋ ብሪታንያ በሚጐበኙበት ግዜ በስኮትላንድ ኤዲምበርግ ላይ በሚገኘው ሆሊሩድ ሃውስ ከንግስት ኤሊሳበጥ ዳግማዊት ጋር እንደሚገናኙ ተመልክተዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በታላቅዋ ብሪታንያ የሚያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት እንድያስተናብሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ደቪድ ካመሩን የተወከሉ ሎርድ ክሪስቶፈር ፓተን እዚህ ራድዮ ቨቲካን ውስጥ ተገኝተው ጉብኝቱ ትኩረት የሰጠ መግለጫ እና ማብራርያ ሰጥተዋል።

ሎርድ ክሪስቶፈር ፓተን እንዳመለከቱት ፡ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ታላቅዋ ብሪታንያ ይፋዊ ጉብኝት ለአማንያን ብቻ ሳይያሆን ለሀገሪቱ ሕበረተ ሰብ በሙሉ የሚመልከት አዎንታዊ እና ጠቀሜታ ያለው ነው ።

አያይዘው የቅድስነታቸው ጉብኝት ስኬታማ ለመድረግ የብሪታንያ መንግስት የኢንግሊዝ ወይልስ እና ስኮትላንድ ጳጳሳት እየተዘጋጁ መሆናቸው ሎስር ክሪስቶፈር ፓትን ገልጠዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ታላቅዋ ብሪታንያ በሚጐበኙበት ግዜ የሚደረገው ወጪ ያተኮረ ሀገሪቱ ውስጥ የተቀሰቀሰው ሙጉት በተመለከተ ሎርድ ክሪስቶፈር ሲያብራሩ

ጸጥታ ጨምሮ ከአስር እስከ አስራ ሁለት ሚልዮን ፓውንድ ወጪ እንደሚጠይቅ ጠቅሰው የቡድን ሃያ የመሪዎች ጉባኤ ላንደን ላይ በተካሄደበት ግዜ ለአንድ ቀን ብቻ ከእስራ ዘጠኝ እስከ ሃያ ፓውንድ ወጪ መደረጉ ዘክረው ችግር አለ ለማለት እንደሚያዳግት ሎርድ ክሪስቶፈር ፓትን ገልጠዋል።

የታላቅዋ ብሪታንያ ህዝብ አብዛኛው ስለ ከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር ደንታ የሌለው ሆኖ እንደሚታይ ያመልከቱት የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ የታላቅዋ ብሪታንያ ጉብኝት እንድያስተባብሩ በሀገሪቱ ጠቃላይ ሚኒስትር ደቪድ ካመሩን የተሰየሙት ሎርድ ክሪስቶፈር ፓትን ጁልያን በርንስ የተባሉ ደራሲ በእግዚአብሔር አላምንም ግን ደግሞ እሱ ይጐድለኛል የተሰየመ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ያበቁት የግድ የለሽ ህዝብ አኗኗር የሚያንጸባርቅ ይመስለኛል ማለታቸው ተመልክተዋል።

ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በትህተ ሰሃራ ሀገራት በማህበራዊ መስኮች በትምህርት እና ሕክምና የምትሰጠው ከፍተኛ እገዛ ራሱ ማሕበራዊ ፍትሕ እንዲገኝ ብሎም ሰላም ለማስፈን የምታካሄደው ጥረት አዎንታው መሆኑ ሎርድ ክሪስቶፈር ፓትን አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.