2010-07-23 15:14:23

የቤተሰብ ጉባኤ


ኢስታት በመባል የሚጠራው የኢጣልያው ተጨባጭ ሁኔታ በአኃዝ የሚተነትን ማእክል እ.ኤ.አ. በኢጣሊያ ከ 1995 ዓ.ም. የፍች ውሳኔ በእጥፍ ከፍ እያለ መምጣቱ አስታወቀ። ይህ የቤተሰብ ችግር በልጆች የሚያሳድረው ስነ RealAudioMP3 አእምሮአዊ እና ማኅበራዊ ችግር እና ከፍች በኋላ በተፋቱት ሰዎች ዘንድ የሚከሰተው የኑሮ ድኽነት እና ጥሎት የሚያልፈው ጠባሳ በተለይ ደግሞ ከፍች በኋላ ባል እና ሚስት በነበሩት መካከል የሚታየው ለተለያዩ አደጋ የሚያጋልጠው የጥላቻ ስሜት እጅግ አሳሳቢ መሆኑ ያመለክታል።

እ.ኤ.አ. በ 1995 ዓ.ም. ከሚጋቡት አንድ ሺሕ ውስጥ 80 እንደተፋቱ እና 152 እንደተለያዩ ሲገለጥ፣ እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. 286 ሲለያዩ 179 ደግሞ ተፋተዋል። ይህ ትዳር፣ መለያየት እና ፍች በሚል ርእስ ሥር ኢስታት ያካሄደው የጥናት ሰነድ እንደሚያመለክተውም፣ በአሁኑ ወቅት 84 ሺህ መለያየት እና 54 ሺህ የመፋታት ቀውስ እንዳጠቃው ለማወቅ ሲቻል፣ የአንድ ትዳር መካከለኛው የቆይታ ዕድሜ ገደብ ከ 15 እስከ 18 ዓመት መሆኑ ጥናቱ በመግለጥ፣ የተለያዩት መካከለኛው እድሜ ለባል 45 ለሚስት 41 ዓመት ሲሆን፣ የተፋታው መካከለኛው የእድሜ ገደብ ለባል 46 ለሚስት 43 ዓመት መሆኑ የኢስታት ሰነድ ያረጋገጣል።

70% የተለያዩ እና 62% የተፋቱ ውላጆች መሆናቸው ሲገለጥ፣ 78% ልጆቻቸው በማፈራረቅ እንደሚያሳድጉ ለማወቅ ሲቻል፣ 19% ግን በፍርድ ቤት ውሳኔ መሠረት ለእናት የጥበቃ እና የማሳድገድ ኃላፊነት የተሰጡ መሆናቸውም ጥናቱ ያመለክታል። የሚፋቱት ባለ ትዳሮች ከሚጋረጥማቸው ችግር አንዱ የመኖሪያ ቤት ጉዳይ እና ድኽነት መሆኑ ሲገለጥ፣ የትዳር ጉዳይ የሚከታተሉት የጠበቆች ማኅበር 25% የተፋቱት እና የተለያዩት በካሪታስ የተራድኦ ማኅበር ድጋፍ እንደሚያገኙ እና 5% የተፋቱ ሴቶች ከነልጆቻቸው ከዚህ የተራድኦ ማኅበር የተሟላ ድጋፍ እንደሚያገኙ ያመለክታል።

ኢስታት የሰጠው የጥናት መግለጫ በማስመልከት የኢጣሊያ የቤተሰብ ጉባኤ ሊቀ መንበር ፍራንቸስኮ በለቲ ከቫቲካ ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የፍች እና የመለያየት ጉዳይ እጅግ ሰብአዊ እና ማኅበራዊ ብሎም ሃይማኖታዊ ነክ የሆነ አሳሳቢ ችግር ነው፣ ሞት እስከ ሚለየን ድረስ የሚለው ቃለ ማኅላ ሊተገበር የማይቻል ሓሳብ ብቻ እየሆነ መጥተዋል። ፍች እና መለያየት ለተወለዱት ልጆች ብቻ ሳይሆን፣ የተጀመረ አንድ የታመነበት የሕይወት እቅድ ለሞት የሚዳርግ በመሆኑም ተጋብተው ለሚፋቱት ጭምር አቢይ ቀውስ ያስከትላል ብለዋል።

ችግሩ እንዲህ ሆኖ እያለ ብዙውን ጊዜ በባለ ትዳሮች መካከል የሚታየው መለያየት እና ፍች ልሙድ እይሆነ፣ ከጋብቻ በኋላ በግድ መደረስ ያለበት ደረጃ እየሆነ መጥተዋል። ስለዚህ ጋብቻ ተዋደድን ተፋቀርን በማለት ውኅደቱ በስሜት ላይ ብቻ አጽንቶ ማረጋገጡ አቢይ ስሕተት ነው፣ ለዚህም ነው ቤተ ክርስትያን ለመጋባት እቅድ ለሚወጥኑት በመከታተል ሞት እስከ ሚለየን ለሚለው ከሁለት ወደ አንድ መሆን የሚለውጠው ማንም የማይሽረ ደረጃ ከመድረሱ በፊት የተክሊል ምሥጢር በጥልቀት በማስረዳት ጋባቻ አብሮ መኖር ፍቅር መቋደስ አንድ ቤተሰብ መመሥረት ምን ማለት መሆኑ በማስተማር ለኃላፊነት በማነጽ ዓላማ የምትጠመደው። ችግር መቼም ቢሆን ይኖራል ነገር ግን ችግሩ ባጋጣመ ቁጥር በቃኝ ብሎ መፋታት ሳይሆን ችግሩን በጋራ ለመፍታት ጥረት ማድረግ፣ ፍች ለሚያፋጥኑት አቤት ማለት ሳይሆን፣ ትዳሩን ከአደጋ ለማትረፍ ጥረት ለሚያደርጉት ስለዚሁ ጉዳይ አቢይ ቅድመ ዝግጅት ላላቸው የነፍሳት አባቶች እና እንዲሁም ከተገቡት ሰዎች መንፈሳዊ እና ስነ አእምሮአዊ ድጋፍ መሻት ወሳኝ ነው። በዚሁ ጉዳይ ቤተ ክርስትያን እና ኅብረተሰብ አቢይ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸዋል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.