2010-07-23 15:17:55

ለምሥራቁ አለም የተከፈቱ በሮች


በኢጣሊያ የሚላኖ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ዲዮኒጂ ተታማንዚ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 10 ቀን እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በቫቲካን ሊካሄድ ተወስኖ ስላለው የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በማስመልከት RealAudioMP3 ፣ በሊባኖስ ዴክዋነህ ከተማ ስለ መካከለኛው ምሥራቅ በተወያየው ልዩ ስብሰባ ተገኝተው ለመካከለኛው ምሥራቅ ማኅበረ ክርስትያን ምን ዓይነት የመጪ ሕይወት ይጠብቀዋል በሚል ርእሰ ጉዳይ ሰፊ ንግግር ማሰማታቸው ተገለጠ።

ብፁዕ ካርዲናል ተታማንዚ፣ ለመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ማካሄጃ የተጠናቀረው ሰነድ፣ ስለ ክልሉ ማኅበራዊ ፖሊቲካዊ ኤኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ጉዳይ ግንዛቤ እንዲኖረን የሚያደርግ ብቻ ሳይሆን፣ በቅድሚያ ሃይማኖታዊ እና ቤተ ክርስትያናዊ ግንዛቤ እንዲኖር የሚያግዝ ነው። በምትከተለው ሥርዓት መሠረት ጥግ ፈጥሮ መኖር ለአካባቢነት እና ለተነጥሎ መኖር ለተዘጋ ሕይወት የሚያጋልጥ መሆኑ አስረድተው፣ ይህ ዓይነቱ ችግር ለኵላዊው የቤተ ክርስያን ባህርዪ የሚጻረር ነው። የቤተ ክርስትያን የምእመናን እና የካህናት የገዳማውያን ችግር ቀርቦ ማጤን በዚህ ሁሉ ሂደት የቤተ ክርስያን ኵላዊነት ገጽታው ማጉላት አስፈላጊ ነው እንዳሉ ሎሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር እለታዊ ጋዜጣ በትላንትናው ኅትመቱ አስታወቀ።

በመጨረሻም የሚላኖ ከተማ ከመካከለኛው ምሥራቅ አቢያተ ክርስትያን ጋር ያላት ቅርበት እና ግኑኝነት በመጥቀስ፣ በሚላኖ ከተማ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ንብረት የሆነው በቅዱስ አምብሮዚዮስ የሚጠራው ቤተ ንባብ በውስጡ የሚያቅፋቸው ጥንታውያን የየመን የታሪክ መጻሕፍት ቅርሶች የምስልምናው ሃይማኖት የድርሰት ቅርሶች አንዱ ምስክር መሆኑ ጠለቅ በማድረግ ማስረዳታቸው ሎሶርቫቶረ ሮማኖ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.