2010-07-19 13:31:17

አንደኛው ዓለም አቀፍ የነልሰን ማንዴላ ቀን


ዓለም አቀፍ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ነልሰን ማንዴላ የተወለዱበት ቀን ዓለም አቀፍ የነልሰን ማንደላ ቀን ተብሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲከበር ያስተላለፈው ውሳኔ መሠረት፣ ትላንትና በመላ RealAudioMP3 ዓለም ተከብሮ ውሎአል።

ዓለም አቀፍ የነልሰን ማንዴላ ቀን እንዲከበር የተባበሩት መንግሥታት የሰጠው ውሳኔ፣ በቅድሚያ ይህ ድርጅት ከዓለም ዙሪያ ዘረኝነት እንዲወገድ ለሚያደርገው ጥረት ለማበረታታት፣ በማለት እና እንዲሁም ነልሰን ማንዴላ በደቡብ አፍሪቃ የነበረው የዘረኝነት ፖለቲካ እና ሥርዓት ተወግዶ የሰው ልጅ ማእከል ያደረገ የሰው ልጅ መብት እና ፈቃድ በእኵል ደረጃ እንዲከበር ነጻነት እና ዴሞክራሲ በማነቃቃት እንዲረጋገጥ ከማድረግ አልፈውም ይህ መልካም እና የተቀደሰው ዓላማ በዓለማችን ሰላም ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት የሚያበረታታ መሆኑ በመግለጥ፣ ነልሰን ማንዴላ በደቡብ አፍሪቃ የነበረው የዘረኝነት ሥርዓት ለማጥፋት ያከናወኑት የተለያዩ እንቅስቃሴ መሠረት በ 70ዎች ዓመታት ለእስር ተዳርገው እ.ኤ.አ. በ 1990 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ማኅበረ-ሰብ ግፊት ነጻ ተለቀው፣ ካለ መታከት የደቡብ አፍሪቃው ችግር መፍትሔ የትጥቅ ትግል ሳይሆን፣ የውይይት እና የሰላም ትጥቅ መሆኑ በማመን፣ ይኸንን ዓላማ ካለ መታከት ገቢራዊ እንዲሆን በሰጡት አስተዋጽኦ መሠረት፣ በአገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሁም የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲረጋገጥ ማድረጉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በማብራራ፣ ማንዴላ በአፍሪቃ እና በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች የሚታዩት ችግሮች መፍትሔው የትጥቅ ትግል ሳይሆን የሰላም ትጥቅ ትግል መሆኑ የመሰከሩ እና ነጻነት ለማረጋገጥ ትክክለኛው መንገድ የሰላም ትጥቅ መሆኑ በቃል እና በሕይወት አብነት በመሆን የመሰከሩ፣ መሆናቸው በማብራራት የዘመናችን ቆራጥ/ጀግና በማለትም ሰይሟቸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.