2010-07-19 13:27:16

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በተባበሩት መንግሥታት አዲስ የቅድስት መንበር ቀዋሚ ታዛቢ ሾሙ


የህንድ ተወላጅ ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስ አሲዚ ቹሊካት ኒው ዮርክ በሚገኘው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሆነው እንዲያገለግሉ በቅድስቱ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 መሾማቸው RealAudioMP3 የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ብፁዕ አቡነ ቹሊካት፣ በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ በመሆን ያገለገሉት በፖላንድ የቅስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል እንዲሆኑ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. የተሾሙትን ብፁዕ አቡነ ቸለስቲኖ ሚሊዮረን የሚተኩ መሆናቸውም ለማወቅ ሲቻል፣ ብፁዕ አቡነ ቹሊካት 57ኛው የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ መሆናቸው የቅስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።

ብፁዕ አቡነ ቹሊካት እ.ኤ.አ. በ 1988 ዓ.ም. ጀምረው በቅድስት መንበር ዋና ጽሓፊ ቢሮ ሥር በሚተዳደረው የውጭ ግኑኝነት ክፍል በዲፕሎማሲያዊው ተልእኮ አገልግሎት መስጠት ጀምረው፣ በሆንዱራስ በተለያዩ በደቡብ የአፍሪቃ ክልል በሚገኙት አገሮች፣ በፊሊፒንስ እና በተለያዩ የተባቡሩት መንግሥታት ድርጅት ጽ/ቤቶች ቅድስት መንበርን በመወከል ያገለገሉ መሆናቸው ሲገለጥ። እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 29 ቀን 2006 ዓ.ም. በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ውሳኔ መሠረት የኦስትራ ተጠሪ ሊቀ ጳጳሳት እና በዮርዳኖስ ቀጥለውም በቅድስት መንበር የጠቅላላ አገልግሎት ጉዳይ ተተኪ በመሆን በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የተሾሞት ብፁዕ አቡነ ፈርናንዶ ፊሎኒን በመተካት በኢራቅ የቅድስት መንበር ሓዋርያዊ ወኪል በመሆን በማገልገል ላይ እንደነበሩ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።








All the contents on this site are copyrighted ©.