2010-07-16 15:18:58

ዴሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎ


በዴሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎ ለኡልቪራ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሪቻርድ ዶምባ በዚህች አሰቃቂው ደም አፋሳሽ ግጭት በሚፈራረቅባት አገር ሰላም ለማስፈን እና ሰላም ለማረጋገጥ ምን መደረግ አለበት ለሚለውጥ ጥያቄ ምላሽ RealAudioMP3 ለመስጠት ሰላም በሚል ርእስ ሥር ሰበካው እ.ኤ.አ. ከ ሐምሌ 12 ቀን እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2010 ባካሄደው ጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር በማስተጋባት፣ ይህ የሰበካው ጳጳሳዊ የሰላም እና የፍትህ ድርገት የእርቅ ሃብት የተሰኘው መንግሥታዊ ካልሆነው የግብረ ሰናይ ማኅበር ጋር በመተባበር ባነቃቃው ጉባኤ፣ በቅርቡ የኡጋንዳ ብፁዓን ጳጳሳት ሊቀ መንበር እንዲሆኑ የተመረጡት የጉሉ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጆን ባፕቲስት ኦዳማ፣ የዶሩማ እና ዲንጉ እንዲሁም የኢሲሮ ኣና ኒአንጋራ በሱዳን የየይ ውሉደ ክህነት አባላት መሳተፋቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በብፁዕ ካርዲናል ፊዮረንዞ አንጀሊኒ የተመራው የሻሎም እንቅስቃሴ አባላት ትላትና በኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ረፓብሊክ የሚገኘው የሻሎም እንቅስቃሴ ቅርንጫፍ፣ የፍቅር ከተማ በሚል መጠሪያ በመቆርቆር ላይ ያለው መንደር የግንባታው ሂደት ቀርቦ ለመገምገም ጉብኝት እንደሚያካሂድ ሲገለጥ፣ በዚህ በመቆርቆር ላይ ባለው መንደር አንድ ትምህርት ቤት፣ የአረጋውያን ማረፊያ ቤት፣ የተፈናቃዮች ማእከል፣ የጤና ጥበቃ አገልግሎት መስጫ ማእከል ግንባታ ያጠቃለለ ሲሆን፣ በዚህ ጉብኝት ብፁዕ አቡነ አንድረያ ፒዮ ክሪስቲኒ እና የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች በመሳተፍ ላይ መሆናቸው ተገልጠዋል።

በኮንጎ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ዜጎች የመብት እና ግዴታ ባለ ቤት እንዲሆኑ አቢይ የሕንጸት ድጋፍ ከመስጠት አልፎ፣ ሕዝብ የዜግነት ግዴታው በኃላፊነት እንዲወጣ በማነቃቃት ላይ እንደምትገኝ ሲገለጥ፣ የኮንጎ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ኒኮላስ ድጆሞ እና የአገሪቱ የኤኮኖሚ እና የገንዘብ ሃብት ጉዳይ ሚኒ. አውጉስቲን ማታታ ምፖንዮ የግብር ክፍያ ጉዳይ በተመለከተ በአገሪቱ በምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና የአገሪቱ መንግሥት መካከል ባለፈው ሐምሌ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. የጋራ የስምምነት ሰነድ መፈራረማቸው ተገልጠዋል።

የስምምነቱን ሰነድ የጠቀሱት ብፁዕ አቡነ ድጆሞ፣ በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የግብር ክፍያ የማክበር ባህል በማስደገፍ ቀጣይ ሕንጸት እንደምታቀርብ በማብራራት፣ ሙስና አድልዎ የመሳሰሉት በጠቅላላ ጸረ እድገት የሆነው ኢግብረ ገባዊ ጠንቅ በመቃወም፣ መብት እና ግዴታ የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች ናቸው የሚለው ሐሳብ መሠረት ኃላፊነት በብቃት መወጣት በሚለው ውሳኔ ሕዝብ በማነጽ ላይ እንደትገኝ አብራርተዋል።

ሚኒስተር ማታታ ምፖንዮ በበኩላቸውም በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በተለያየ መልኩ የግብር ክፍያ ኃላፊነት መወጣት በተመለከተ ከሚደረጉት ዘመቻዎች ሌላ የሕዝብ ኅሊናን በማነጹ ረገድ የምትሰጠው አገልግሎት ለአገሪቱ እድገት መሠረት ነው እንዳሉ ለማወቅ ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.