2010-07-16 15:20:45

ሴኔጋል፣ የክርስትና እና የምስልምና ሃይማኖት የጋራው ውይይት


በሴነጋል የዳካር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ተዮዶረ አድሪየን ሳር ከትላትና በስትያን በአገሪቱ የቱባ ክልል የሚገኘው እ.ኤ.አ. በሴንጋል በ 1800 ዓ.ም. ለተመሠረተው የሱፊስታ ሙስሊሞች ማኅበረሰብ ቅዱስ ሥፍራ ተብሎ RealAudioMP3 የሚነገርለት በሚሩድ ከተማ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ በክልሉ ከሚገኙት ሙስሊሞች ጋር ባካሄዱት ግኑኝነት፣ እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የሙርዲ ጠቅላይ ካሊፍ ስሪግነ ሙሃማዱ ላሚነ ባራ ምባኬ ምክንያት ለሲፊስታ ሙስሊሞች ማኅበረሰብ የሐዘን መግለጫ መልእክት አሰምተዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ሳር አክለውም አዲሱ ጠቅላይ ካሊፋ ሰሪግነ ሞዱ ማትይ ለየ እና የሳቸው የቅርብ ተባባሪዎች በእስልምናው እና በክርስትያናው ሃይማኖት መካከል የሚደረገው የጋራው ውይይት እንዲበረታቱ እና በሴነጋል በሁለቱ ሃይማኖቶች መካከል መቀራረብ እንዲኖር በሚደረገው ጥረት እጥጋቢ ውጤት ይኖረው ዘንድ አቢይ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም የአደራ ጥሪ አቅርበዋል።

ከብፁዕ ካርዲናል ሳር ጋር በሴነጋል የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ ማሪያኖ ሞንተማዮር የታይስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዣክ ሳር እና የፕሮተስታንት ቤተ ክርስትያን ተጠሪዎች አብሮአቸው በሐዋርያዊ ጉብኝቱ መሳተፋቸውም ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.