2010-07-16 15:21:57

ለጋዛው ክልል ነዋሪ ሕዝብ የሰብአዊ እርዳታ


ገዳፊ የድጋፍ ማኅበር ለጋዛው ሰርጥ ክልል ሕዝብ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት በሚል እቅድ በማስተባበር የተገኘው 2ሺሕ ቶን የሰብአዊ እርዳታ የጫነች አማልተአ የተሰየመቸው የሊቢያ መርከብ እስራኤል በፍልስእጤም ላይ RealAudioMP3 የደነገገችው ማዕቀብ በመጋፈጥ እና በመጣስ ወደ ጋዛው ሰርጥ ክልል በቀጥታ ለማድረስ ከተነሳች በኋላ በክልሉ ያለው ወጥረት ካለበት የተወሳሰበ ሁኔታ እጅግ ወደ ከፋው ሁኔታ እንዳያዘግም በሚል ሥጋት በተደረገው ድርድር መሠረት መርከቧ ትላትና አቅጣጫዋን በመቀየር ሰሜናዊ ሲናይ የባሕር በር መግባቷ ተገልጠዋል።

መንግሥታዊ ያልሆነ ቅድስት መሬት በመባል የሚጠራው የግብረ ሰናይ ማኅበር አስተዳዳሪ ቶማሶ ሳልቲኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የጋዛው ክልል ነዋሪው ሕዝብ የምግብ የመድሃኒት ችግር እንዳለበት የተረጋገጠ ቢሆንም፣ የመጪው ሕይወቱን ለመገንባታ እንዲችል ድምጹን ከፍ በማድረግ የሚያስተጋባው ቃል ነጻነት የሚል ነው፣ የምግብ እርዳታ በተለያየ ምክንያት ሲገባ ይታያል፣ ሕዝቡ የሰብአዊ ጉዳይ ችግር አለበት ስለዚህ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልገው ቢሆንም ቅሉ ሆኖም የክልሉ የተወሳሰበው ችግር የምግብ እና የመድሃኒት እርዳታ በማቅረብ ይፈታል ማለት እንደማይቻል ነው ካሉ በኋላ፣ ይህ ሁኔታ በዚሁ ክልል ገና መፍትሔ ያላገኘው የተወሳሰበ ፖለቲካዊ ችግር እንዳለ የሚያመለክት ነው ብለዋል።

እልባት ያላገኘው የክልሉ ችግር መፍትሔ እንዲያገኝ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጥረት እጅግ አስፈላጊ ነው፣ ችግሩ ለሁለቱ የውጥረቱ ተወናያን አገሮች መተው ሳይሆን የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ቆራጥ ውሳኔ በመውሰድ፣ ሰላማዊ መፍትሔ ማፈላለግ ይጠበቅበታል ካልሆነ ግን ችግሩ እየተባባሰ በአሁኑ ወቅት መፍትሔ ሊሆኑ ይችላሉ የሚባሉት ውሳኔዎች እያደከመ እና እያራቀ መፍትሔ የማፈላለጉ ጥረት እያገለለ እንደሚሄድ የታወቀ ነው ስለዚህ፣ ግዜው አሁን ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.