2010-07-15 13:07:59

የሃይማኖት ነጻነት የሰላም ጐደና ነው፡ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፊታችን ዓመት ጥር አንድ ቀን በጎርጎርዮስ ዘመን አቁጣጠ ተከብሮ ለሚውለው አዲስ የኤውሮጳውያን ዓመት ለሚያስተላልፉት አርባ አራተኛ የሰላም መልእክት የሃይማኖት ነጻነት የሰላም ጐደና የተሰየመ መልእክት መሆኑ በቅድስት መንበር የፍትሕ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ከወዲሁ አስታውቀዋል።

በቅድስት መንበር የፍትሕ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት እንዳመለከተው፡ የሐሳብ ነጻነት በተሚከበርበት የዓለም ሀገራት የእምነት ጉዳይ በተቻለ መጠን ወደ ጐን በመተው የሃይማኖት ክብር እና እሴት ሲቀነስ እና በህዝብ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንድያሳርፍ እየተደረገ መሆኑ ይስተዋላል።

የፍትሕ እና ነጻነት ጳጳሳዊ ምክር ቤት አያይዞ እንደገለጠው፡ ሐሳብ በነጻ መግለጽ በሚገድቡ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ውሁዳን ክርስትያኖች እምነታቸው ገቢራዊ ለማድረግ ፍጹም ሲከለከል ይታያል።

በቅድስት መንበር የፍትሕ እና ነጻነት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስን ጠቅሶ እንዳመልከተው፡ የሃይማኖት ነጻነት ከሰብአዊ ክብር ጋር የተሳሰረ ስለሆነ የሃይማኖት ነጻነት የነጻነት ነጻነት ተደርጎ እንደሚታይ አመልክተዋል።

ፊታችን በጎርጎርዮሳዊ ዘመን አቆጣጠር አዲስ ዓመት 2011 መባቻ ይፋ የሚሆነው የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አርባ አራተኛ የሰላም መልእክት ርእስ የሃይማኖት ነጻነት የሰላም ጐደና መሆኑ ከወዲሁ የገለጸ በቅድስት መንበር የፍትሕ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት አያይዞ እንደዘገበው ፡ የሃይማኖት ነጻነት እውነትነት በማፈላለግ እና የሰው ዘር ማንነት እና ፈልጎ ሲያሰተምር እውነተኛነቱ ያረጋግጣል ።

የሰው ክብር የማይታደጉ ሁሉ ፡ እውነተኛነት ለማፈላለግ የሚከለክሉ መሆናቸው ጳጳሳዊ ምክር ቤቱ አመልክተውል ።

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ርእሳነ ሊቃነ ጳጳሳት እንደ ኤውሮጳውያኑ ዘመን እቁጣጠር ከ1968 ዓመተ ምህረት ጀምረው አዲስ ዓመት ሲገባ ለዓለም ህዝብ የሰላም መልእክት እንደ ሚያስተላልፉ የሚታወስ ነው።

የሃይማኖት ነጻነት ግን ሲገደብ የባሰ ደግሞ በውሁዳን ክርስትያን ላይ የማሳደድ ተግባር ሲፈጸም ማየቱ አሳዛኝ መሆኑ በቅድስት መንበር የፍትሕ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት አያይዞ አመልክተዋል።

በብዛት ክርስትያን በሚኖሩባቸው ሀገራትም ቢሆን ይላል የፍትሕ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤቱ ፡ ክርስትያኖች በሀገራቱ ፖሊቲካ እና ሲቪል ሕይወት ተሳታፊ እንዳይሆኑ በነሱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሲደረግ ይታያል ብለዋል።

የፍትሕ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት የሰጠው ይፋ መግለጫ በማያያዝ እንደ ኤውሮጳያኑ ዘመን አቆጣጠር ሚያዝያ አስራ ስምንት ቀብ 2008 ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ኒውዮርክ ላይ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጠቃላይ ስብሰባ ፡ ተገኝተው፡ አማንያን ገቢራውያን ዜጎች ለመሆን የራሳቸው አካል የሆነውን እምነታቸው መቆሸብ የለባቸውም በለው ማለታቸው ምክር ቤቱ አስታውሰዋል።

በዚሁ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ንግግር በደረጉበት ግዜ አማንያን ሆነው በህዝባዊ ጉዳይ አቅማቸው የፈቀደው ሚና መጫወት መብታቸው መሆኑ

እየታወቀ ይህንን ለመድረግ አማንያን እግዚአብሔርን መካድ አለባቸው እንዴ በማለት ቅድስነታቸው ለጉባኤው መጠየቃቸው የፍትሕ እና ሰላም ምክር ቤት አመልክተዋል።

በማያያዝም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ የሰው ምሉእነት መሸራረፍ እንደማይቻል አጽንኦት ሰጥተው በመግለጽ እምነት የሰው ሕይወት መሆኑ እና እምነቱ ጠብቆ ለኅብረተ ሰብ የሚያደርገው አስተዋጽኦ መገታት እንደሌለበት ቅድስነታቸው ለድርጅቱ አባላት መግለጣቸው ምክር ቤቱ አስታውሰዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.