2010-07-14 13:44:51

ብፁዕ ካርዲናል አንቶነሊ፣ ቤተሰብ የኅብረተሰብ ሃብት ነው


የቤተሰብ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንቶነሊ በፈረንሳይ ቤተክርስትያን፣ እንተ ላእለ ኵሉ ብፅእና ያወጀችላቸው የቤተሰብ አብነት የሆኑት ባል እና ሚስት እምነትን በቃል እና በሕይወት RealAudioMP3 የኖሩትን የቅድስት ተረዛ ዘ ሕፃነ ኢየሱስ ወላጆች ብፁዓን ልዊስ እና ዘሊየ ማርቲን ሚስጢረ ተክሊል የተቀብሉበት ሓምሌ 12 ቀን 1858 ዓ.ም. ዝክረ በዓል ምክንያት በአለንኮን ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት፣ ቤተሰብ መተኪያ የሌለው የሰብአዊነት ክብር እርግጠኛ አመልካች እና የኅብረሰብ መሠረታዊ ሃብት ነው በማለት፣ የቤተሰብ ትርጉም ተንትነው በማስረዳት፣ የማርቲን ቤተሰብ የባለ ትዳሮች ፍቅር እና ውህደት እንዲሁም፣ ምንም’ኳ መሥዋዕት የሚጠይቅ አቢይ ኃላፊነት የሚያሰጥ በቃል እና በተግባር አብነት መሆን የሚጠይቅ ቢሆንም ቅሉ፣ ወላጅ መሆን ያለው እና የሚሰጠው ደስታ የመሠከሩ፣ ስለ ቤተሰብ ለሚመለከተው ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አብነት የሆኑ፣ የቤተ ክርስትያን አባልነታቸውን በሙላት የኖሩ፣ ሙያዊ እና ቤተሰብአዊ ኃላፊነታቸውን በተስተካከለ ሕይወት ያንጸባረቁ ናቸው በማለት ገልጠዋቸዋል።

ዓለማችን በአሁኑ ወቅት የዚህ ዓይነት ቤተሰብ መጠማቱንም ጠቅሰው፣ ቤተሰብ የጾታዊ ስሜት ማርኪያ እንጂ ምሥጢረ ተክሊል የማይሻር ምሥጢር መሆኑ በማመን እውነተኛው ፍቅር የሚኖርበት እንዳልሆነ ተደርጎ የግል ጉዳይ እንጂ ማኅበራዊነት ገጽታ የለለው እየሆነ ሲገለጥ እና ሲኖር እየታየ መሆኑ ገልጠው፣ ስለዚህ ቤተሰብ መብት እና ግዴታ ለበስ ሳይሆን የግለ ሰቦች ድምራዊ ስብስብ ተደርጎ ሲፈለግ የሚጸና ሲፈለግ የሚበተን ለኅብረሰብ አቢይ እና መሠረታዊ ክብር መሆኑ እየተዘነጋ፣ የግል ፍላጎት እና ምኞት የሚያቋቁመው የጋራ ሕይወት ተደርጎ እየተገለጠ፣ ለአበይት ቀውሶች ምክንያት እየሆነ ነው፣ ካሉ በኋላ ይህ ጉዳይ በትዳር፣ በወሊድ እና በሕንጸት ረግድ አቢይ ችግር እያስከተለ መሆኑ አብራርተው፣ በዚህ አይነት የትዳር አገላለጥ ምክንያት፣ ምሥጢረ ተክሊክ ከሚቀበሉት ውስጥ ግማሹ እንደሚፋታ የኤውሮጳ ህብረት የስታቲስቲክስ መግለጫ ይመሰክረዋል ብለዋል።

በምሥጢረ ተክሊል የሚጸናው ትዳር ለኅብረተሰብ ሃብት እና ዋስትና ነው፣ በማለት ብፁዕ ካርዲናል አንቶነሊ አክለው፣ በኅብረተሰብ በቁምስናዎች በመገናኛ ብዙሃን በኵል ስለ ቤተሰብ ጉዳይ በሚመለከት ርእሰ ጉዳይ፣ በቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት ላይ በማስደገፍ ውይይት አስተንትኖ እና የመደጋገፍ እቅድ መረጋገጥ ይኖርበታል። ቤተሰብ የቃለ እግዚአብሔር ማኅደር መሆን አለበት ብለዋል። ቤተ ክርስትያን የግል እና የማኅበራዊው መብት እና ግዴታ አታዘባርቅም፣ አንዱ ባንዱ ላይ የበላይነት አለው አትልም፣ ሆኖም ቤተሰብ ማለት የግለ ሰቦች ስብስብ ማለት እንዳልሆነ አጥብቃ በመቃወም ይኸንን እውነተኛው የቤተሰብ ትርጉም ታስተምራለች፣ ስለዚህ ክርስትያን ቤተሰብ ይኽ በቤተ ክርስትያን የሚገለጠው የቤተሰብ ትርጉም መሥካሪ ሆኖ መገኘት ይጠበቅበታል ብለዋል።

በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት መካከል እንጂ ተምሳይ ጾታ ባላቸው መካከል የሚጸና እንዳልሆነም አስረድተው፣ እ.ኤ.አ. በ 1981 ዓ.ም. የእዚአብሔር አገልጋይ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ስለ ቤተሰብ ጉዳይ ያቀረቡትን ምዕዳን ጠቅሰው፣ የቤተሰብ ወዳጅ የሆነ ኅብረተሰብ ማጽናት ወሳኝ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.