2010-07-14 13:46:42

ብፁዕ ካርዲናል ታውራን፣ እርቅ እና ሰላም ማነቃቃት


በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራው ውይይት የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያነቃቃው በታይላንድ ርእሰ ከተማ ብንኮክ በሚገኘው ባን ፉ ዋን የሳምፕራን የሐዋርያዊ ግብረ ኖልው ማእክል ሁሉም ሃይማኖቶች ያካተተ ጉባኤ RealAudioMP3 እየተካሄደ መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

በዚህ ከትላንትና በስትያ በተጀመረው ለአንድ ሳምንት በሚቆየው ስብሰባ በእስያ የሚገኙት የተለያዩ አሁጉራት የብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች የሚያቅፋቸው በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ውይይት የሚያነቃቁ ጳጳሳዊ ድርገቶች እየተሳተፉ መሆናቸው ሲገለጥ፣ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ውይይት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ታውራን የዚሁ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ፒየር ልውጂ ቸላታ እና ምክትል ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ኤንድሪው ዛንያ አናን እየተሳተፉ መሆናቸው ለማወቅ ሲቻል፣ የባንግላደሽ የህንድ የኢንዶነዢያ፣ የጃፓን የኮረያ የላዎስ የማሊዥያ የምያንማር፣ የኔፓል የፓኪስታን የፊሊፒንስ የታይዋን የታይላንድ፣ የስሪ ላንካ፣ እና የቪየትናም ብፁዓን ጳጳጳሳት ጭምር እየተሳተፉ መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የሚካሄደው ስብሰባ፣ በክርስትናው እና በቡድሃ ሃይማኖት መካከል የሚደረገው ውይይት፣ የክርስትናው ከታኦይስት፣ ከኮንፉቻኒ፣ ከሺንቶይስት ከሂንዱ ከሲክ ከጃይኒስቲ ከምስልምናው ሃይማኖቶች መካከል ያለው የጋራው ውይይት የሚዳስስ ጉባኤ እንደሚሆን የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

ይህ የተለያዩ ሃይማኖቶች የሚያገናኘው ስብሰባ በታይላድ ተከስቶ ላለው ቀውስ ሰላማዊ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ አቢይ ድጋፍ እንደሚሆን ፊደስ የዜና አገልግሎት በመግለጥ፣ በሕዝቦች መካከል መግባባት እና መቀራረብ እንዲሁም መተዋወቅ እንዲኖር የሚያግዝ መድረክ ብቻ ሳይሆን እርቅ እና ሰላም ላንድ ኅብረተሰብ እድገት መሠረት መሆኑ የሚያረጋግጥ ስብሰባ መሆኑ የዜናው አገልግሎት በማከል አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.