2010-07-12 16:51:33

የዓለም እግርኳስ ውድድር ተጠቃልለዋል እስጳኛ የውድድሩ አሸናፊ እና ተሸላሚ ሁናለች፡


በደቡባው አፍሪቃ ለአንድ ወር የተካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ውድድር ትናንትና ማታ በዮሐንስ በርግ ሶከር ስታድየም በእስጳኛ እና ኔዘርላንድስ መካከል በተካሄደው ውድድር እስጳኛ ኔዘርላድን አንድ ለምንም በመርታት የዓለም ዋንጫ ተሸላሚ ሁናለች።

ኔዘርላንድ የተሸነፈው ቡድኖቹ በዘጠና ደቂቃ ስላልተሸናነፉ የሳላሳ ግዜ ተጨማሪ ግዜ ተሰጥቶዋቸው ለፍጻሜ አራት ደቂቃ ሲቀር እንደሆነ ለመገንዘብ ተችለዋል።

ኔዘርላንድ ሁለት ያለቀላቸው ግቦች በመሳታቸው እንደሆነ የተመለከተ ሲሆን ውድድሩ ለምመልከት የሐንስበርግ ሶከር ስታድዮም ከሰማንያ ሺ በላይ መገኘቱ ተመልክተዋል።

የዘና ሁለት ዓመት አዛውንት አርበኛ አፍሪቃዊ ኒልሰን ማንደላ የውድሩ ሲከፈት መታዘባቸው ተዘግበዋል።ይሁን እና በአፍሪቃ ክፍለ ዓለም የዓለም ዋንጫ ውድድር ሲካሄድ ይህ ትናንትና የተገባደደው የመጀርያ እንደሆነ የማይዘነጋ ነው ።

ይህ በዚህ እንዳለ በደቡባዊ አፍሪቃ ላይ የተካሄደው የዓለም እግር ኳስ ውድድር ለሀገሪቱ እና ለክፍለ ዓለሚቱ የጨዋታ ደስታ ብቻ ሳይሆን የተስፋ ምልክት ሁነዋል በማለት የደርባን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ዊልፍሪድ ፎጽ ናፒየር ገልጸዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ዊልፍሪድ ፎክስ ናፒየር እንደገለጡት፡ በመጅመርያ ደረጃ የዓለም የእግር ኳስ ውድድር ለደቡባዊ አፍሪቃ ትተው የሚሄደው ሀገሪቱ የዓለም ኅብረተ ሰብ አካል መሆንዋን ነው ብዪ አሰባለሁኝ።

የደቡባዊ አፍሪቃ ህዝብ በተለይ ጥቁሮች የሚወዱት ስፖርት እግር ኳስ ነው ያሉት የደርባን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ዊልፍሪድ ፎክስ ናፒየር ውድድሩ ሀገራቸው ውስጥ መካሄዱ ዓቢይ ደስታ እና ፈንጠዝያ መቀስቀሱ አስታውቀዋል።

አሁን የደቡባዊ አፍሪቃ ረፓብሊክ ህዝብ አስፈላጊ የሆነ እና ዋጋ ያለው ነገር ለማድረግ ሌሎች እንድያደርጉለት ሳይጠብቅ ራሱ ማድረግ እንዳለበት በሰከነ አእምሮ መገንዘብ ይኖርበታል ሲሉ ብፅነታቸው አያይዘው ገልጸዋል።

በደቡባዊ አፍሪቃ ረፓብሊክ ብፁዕ ካርዲናል ዊልፍሪድ ፎክስ ናፒየር ሊቀ ጳጳስ ደርባን አያይዘው እንደመልከቱት ደቡባዊ አፍሪቃ የትምህርት ጤና መስኮች ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች የማዘገጀት አቅም ማሳየት ይጠበቅባታል ።

አሁን የሀገሪቱ የፖሊቲካ ሰዎች ለህዝባቸው ጠቄሜታ ያለው ሰብአዊ እና ማኅበራዊ የእድገት ውሳኝ ተግባራት መስራት እንደሚችሉ ምልክት ማሳየት የእነሱ ፈንታ መሆኑም በተጨማሪ መግለጻቸው ተነግረዋል።

አሁን በዚች ሀገር ጥቁሮች እና ነጮች አብረው በአንድ ስታድዩም ከነ ቤተሰቦቻቸው አብረው ሲቀመጡና ለአንድ በጥቆሮች ብቻ የቆመ የእግር ኳስ ቡድን ሲደግፉ ማየት ዓቢይ ርምጃ ወደ ፊት ነው ከሀያ ዓመታት በፊት ፍጹም የማይታሰብ መኖሩ ያመልከቱት ብፁዕ ካርዲናል ዊልፍሪድ ፎክስ ናፔየር ይህ ግን በዓውደ ስፖርት ብቻ ታጥሮ መቅረት የለበትም ማለታቸው ተመልከተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.