2010-07-12 16:44:38

የቅዱስ በነዲክት ዘ ኖርቺያ ክብረ በዓል እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ


ቅድስነታቸው ዛሬ የሚከበረው የኖርቺያ ቅዱስ በነዲክት የኤውሮጳ ጠባቂ እና የርእሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ቅዱስ አስታውሰው ፡ ቅዱሱ የክርስትያናዊ ጉዘአችን መብራት መሆኑ ጠቅሰው ለጥንታዊ ክፍለ ዓለም ኤውሮጳ ስልጣኔ ዓቢይ አስተዋጽኦ ያደረገ ቅዱስ መሆኑ አስገንዝበዋል።

ቅዱስ በነዲክት በአምስተኛ እና ስድስተኛ ሚእተ ዓመት መካከል ይኖር የነበረ ቅዱስ መሆኑ የማይዘነጋ ነው።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አያይዘው እንዳመልከቱት ፡ቅዱሱ በነበረበት ክፍለ ዘመን የሮማ ሥርወ መንግስት የወደቀበት እና የፖሊቲካ ትርምስ በተካሄደበት ግዜ መሆኑ ጠቅሰው ወጣት የነበረው ቅዱስ በነዲክት መንኖ ለሶስት ዓመታት በአንድ ዋሻ ውስጥ መኖሩ እና በጸለኦት እና አስተንትኖ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘቱ አመልክተዋል።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አያይዘው እንደገለጡት ቅዱስ በነዲክት በጥሞኖ ይኖርበት ከነበረ ዋሻ ወጥቶ አንድ ገዳም መስርቶ በርካታ መነኮሳን አፍርቶ መነኮሳኑ ፡ በጸሎት ጥናት እና ስራ ተጠምደው እንዲኖሩ አድርገዋል።

አለ ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት አያቻልም የሚል መርህ የተከተለ ቅዱስ በነዲክት መነኮሳኑ ከሁሉም በላይ ለጸሎት ቅድምያ እንዲሰጠቱ ማስተማሩ አመልክተዋል።

ምእመናን የቅዱስ በነዲክት የተከተለው የጸሎት መርህ እንዲከተሉ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲቶስ በማሳሰብ ለምእመናን ሐዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት ተሰናብተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.