2010-07-12 16:41:35

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በካስተል ጋንደልፎ ሐዋርያዊ አዳራሽ የበጋ ዕረፍት ለማድረግ ባለፈው ረቡዕ ወደ ካስተለ ጋንደልፎ ሐዋርያዊ መካን መዘዋወራቸው የሚታወስ ሲሆን ፡ ትናትና እኩለ ቀን ላይ በሐዋርያዊ አዳራሽ በሚገኘው ትንሽ አደባባይ ከተሰበሰቡ ምእመናን ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል።

ቅድስነታቸውበዚሁ ግዜ እንዳመልከቱት በአሁኑ የዕረፍት ግዜ ችግር ላይ ለሚገኙ ህዝቦች ትኩረት በመስጠት የርዳታ እጃችን የምንዘረጋበት ግዜ ነው ብለዋል።

መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመድገማቸው በፊት ደማቅ አቀባበል ለደረጉላቸው ምእመናን አመስግነው በዚች ውብ ከተማ የምትኖሩ ሁሉ እንደገና ከናንተ ጋር መገናኘቴ ደስ ይለናኝል ብለዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በካስተል ጋንደልፎ ሐዋርያዊ መካን መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት ግዜ ፡ አንድ የሕግ አዋቂ ለመድህን ክርስቶስ መመህር ዘለአለማዊ ሕይወት ለመግኘት ምን ማድረግ አለብኝ ብሎ ይጠቀው እና ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ጥያቄውን አዳምጦ ፡ ዘለዓለማዊ ሕይወት ለማግኘት ፡ በሙሉ ልብ ኀይል እግዚአብሔርን መውደድ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈተረውን የሰው ልጅ እንደ ራስህ መውደድ ያስፈልጋል በማለት ወልደ እግዚአብሔር መልስ ሰጠ ብለዋል።

ቅድስነታቸው እግዚአብሔር ፍቅር ነው እና እገዛ ለሚያሻቸው ሁሉ ማገዝ የፍቅር ስራ መሆኑ አስገንዝበዋል።

ፍቅር ማለት ያጋጠመህን ሰው ከተቸገረ ችግሩን ማቃለል ርህሩህ እና ለጋሽ መሆን እንደሆነም ገልጸዋል።

አንድ ክርስትያን አንድ የማየት ብቃት ያለው ልብ ባሌበት በመሆን እገዛ የሚያስፈልገው ግለ ሰብ እና ማኅበረ ሰብ ማየት እና መራዳት የርዳታ እጁ መዘርጋት ይጠበቅበታል ብለዋል።

የእመታችን ጉዞ በቅድስት ማርያም ወላዲተ አምላኽ የተሸኘ መሆን አለበት ያሉት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ቃለ እግዚአብሔር እና ርዳታ የሚያሻቸው እኅቶቻችን እና ወንድሞቻችን ከልባችን መራቅ የለባቸውም እና ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.