Home Archivio
2010-07-09 15:01:00
የእውነተኛው እምነት እውነተኛ ምስክር
በቻይን በሄ በኡ አውራጃ ለዝሄንግዲን ሰበካ ሕጋዊ ሊቀ ጳጳስ ነገር ግን ይህ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ርክስትያን ሥር የተሰጣቸው ኃላፊነት በቻይና ገና ይፋዊ እውቅና ያላገኘ፣ 75 ዓመት እድሜ ያላቸው በቻይና ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ
ክርስትያን ካህናት እና ብፁዓን ጳጳሳት አብነት የእውነተኛው እረኛ አፍቃሪ እና እርሱን በመምሰል በቻይና ያለው ሃይማኖታዊ ፖለቲካዊ እና ሰብአዊ ጉዳይ በተመለከተ አስተያየት የሚሰጡ ስለ እምነት እና ስለ ፖለቲካ ጉዳይም በተመለከተ ግልጽ የሆነ ውሳኔ ያላቸው እና ይኽንን ይፋ ከማድረግ ያልተቆጠቡ ብፁዕ አቡነ ጁሊዮ ዚያ ዚግዎ እ.ኤ.አ. መጋቢት 31 ቀን 2009 ዓ.ም. እዚህ በቅድስት መንበር በቻይና ስላለቸው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ጉዳይ በተመለከተ ይኽንን ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት ይፋዊ ስብሰባው በከፈተበት ዕለት በቻይና መንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላት እጅ ተይዘው ለእስር የተዳረጉት ከትላትና በስትያን ነጻ መለቀቃቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ብፁዕ አቡነ ጁሊዮ ዢያ ዚጉዎ እ.ኤ.አ. ግንቦት 1 ቀን 1935 ዓ.ም. የተወለዱ እ.ኤ.አ. ሰኔ 7 ቀን 1980 ዓ.ም. ማዕርገ ክህነት ተቀብለው እ.ኤ.አ. የካቲት 8 ቀን 1981 ዓ.ም. የዘንግዲንግ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ መሾማቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
All the contents on this site are copyrighted ©.