2010-07-09 15:02:08

ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና የህንድ መንግሥት


ከ 60 ሺሕ በላይ የሚገመቱ ከተለያዩ ከህንድ ግዛቶች የተወጣጡ በከፋ ድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚገኙትን ተማሪዎች ሥራ እንዲያገኙ የሚያስችላቸው እድል እንደተፈጠራላቸው ሲገለጥ፣ ይህ ዕድል በህንድ የሳሊዚያን ማኅበር RealAudioMP3 ካህናት እና የህንድ የግብርና እና የልማት ጉዳይ ሚኒ. በጋራ በመተባብር ለነዚህ ተማሪዎች ነጻ የሙያ ሥልጠና በመስጠት እራሳቸው ለሥራ ዓለም እንዲዘጋጁ ማድረግ የሚል ሲሆን፣ የመጀመሪያው የሙያው ሥልጠናው የእንግዳ ማረፊያ ቤት የስነ አስተዳደር ትምህርት፣ የመሐንዲስነትና፣ የተሽከርካሪ መኪና አገጣጠም እና የጥገና ሙያ፣ የልብስ ቅድ እና የተለያዩ የተግባረ እድ ሙያ ያካተተ እቅድ መሆኑ በካልኩታ ሐዋርያዊ አገልግሎት በመሰጠት ላይ የሚገኙት የሳሊዚያን ማኅበር አባል አባ ሮቢን ጎመዝ የሰጡትን መግለጫ የጠቀሰው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ይህ የነጻ ትምህርት ዕድል ለድኾች ተማሪዎች ማቅረብ የሚለው፣ የሳሊዚያን ማኅበር ካህናት ያቀረቡት እቅድ በተመለከተ ለሶስት ዓመት ስለ ጉዳይ ከሚመለከተው የህንድ መንግሥት አካል ምክክር ከተደረገበት በኋላ እግብር ለመዋል የበቃ መሆኑ ገልጠው፣ በህንድ ከተለያዩ 100 በሳሊዚያን ማኅበር የተቋቋሙት እና ከሚተዳደሩት የተግባረ እድ ከፍተኛ ተቋሞች እና ከተለያዩ የግብረ ሰናይ ማኅበራት በተገኘው ድጋፍ መሠረት ለማረጋገጥ የተበቃ ድጋፍ መሆኑ አባ ጎመዝ ማብራራታቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.