2010-07-09 14:59:46

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ የእረፍት ትክክለኛው ትርጉም


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከትላትና በስትያ እንደተለመደው የእለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካቀረቡ በኋላ ለበጋው ዕረፍት ሮማ አቅራቢያ ወደ ምትገኘው ከተማ ጋስተልጋንዶልፎ በሚገኘው ጳጳሳዊ ሕንፃ RealAudioMP3 መሄዳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ በመግለጥ፣ ቅዱስነታቸው በዚህ የበጋው ዕረፍት በየእሁድ እኵለ ቀን ከሚያቀርቡት ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር በስተቀረ፣ ከተለያዩ ይፋዊ መርሃ ግብሮች ነጻ በመሆን በዕረፈት በጸሎት እና ባስተንትኖ እንደምያሳልፉት ሲነገር፣ ከዓመታዊ የሥራ የተልእኮ አገልግሎት በኋላ ትንሽ ቆም ተብሎ ክንዋኔዎችን በመገምገም እራስን በማሳረፍ መንፈሳዊ ኃይል በማካበት ዳግም እራስህን ለተሰጠህ ጥሪ እና ኃላፊነት በብቃት የምታዘጋጅበት ወቅት መሆኑ ቅዱስነታቸው በተደጋጋሚ ያሉት ሀሳብ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. እያንዳንዱ እውነተኛ ክርስትያን በዓመት ዕረፍት ወቅት እራሱን በማሳረፍ በመንፍሳዊው ምግብ ለማነጽ፣ በጸሎት እና ባስተንትኖ ከክርስቶስ ጋር ያለው ግኑኝነት በበለጠ ለማጎልበት እና በእርሱ ትምህርት እራስን ለማረጋገጥ የሚያግዝ ወቅት ነው በማለት ቅዱስነታቸው ገልጠው እንደነበር ይዘከራል።

ነሐሴ 13 ቀን 2006 ዓ.ም. የበጋው ዕረፍት ለራስህ የሚሆን ጊዜ በስፋት በመታደል ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ቃለ ቅዱስ መጽሐፍ ለማስተንተን ለሰብአዊ እና ለመንፍሳዊ ሕንጸት የሚደግፍ ተገቢ መጽሓፍ በጽሞና ለማንበብ የሚያመች ጊዜ መሆኑ በማብራራት፣ በክህነት በገዳምዊ ጥሪ ለሚኖሩ እረኞች እና የቤተ ክርስትያን መሪዎች፣ ጥሪ የማኅበራዊ ጉዳይ ሥራ ማከናወኛ እና ጊዜ ማሳለፊያ ሆኖ እንዳይቀር የሚያግዝ ወቅት ነው ብለው እንደነበር የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።

ዓመታዊ የዕረፍት ወቅት በውስጣችን የሚብሰለሰለው በልባችን የታቀቡት አጣዳፊ የሆኑት፣ የእግዚአብሔር አሸራ እርሱም መልካምነት እና አሳቢበቱን የሚያመለክቱ መሠረታውያን የሕይወት ጥያቄዎች በጥልቀት ለመረዳት እና በዚህ መንፈሳዊ ሂደት የሚገለጠው የፈጣሪ ውበት እና መልካምነትን የምስጋና ጸሎት ተደርጎ የሚቀርብበት ጸጋ ነው በማለት ሐምሌ 17 ቀን 2005 ስለ ዕረፍት ጉዳይ በተመለከተ በሰጡት አስተምህሮ እንዳመለከቱም የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።

በሌላው ረገድ የዕረፍት ወቅት የአንዲት ቤተሰብ አባላት ዕለታዊ የሥራ ጥድፍያ የትምህርት ጉዳይ ወዘተርፈ ከመሳሰሉት ኃላፊነቶች ለተወሰነ ጊዜ በመቆጠብ በዚህ ጥድፍያ ሥር የሚመሠረተውን ቤተሰብአዊ ጉኑኝነት ገታ በማድረግ በኅብረት ሆነው ለሰብአዊው ግኑኝነት በማተኮር በመካከላቸው ያለው ትሥሥር ለማነጽ እንዲሁም ከጓደኞች ጋር ያለውን ግኑኝነት ለመኖር የሚያግዝ ምቹ ጊዜ ነው በማለት ነሐሴ 13 ቀን 2006 ዓ.ም. መሪ ቃል መስጠታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በዚህ አጋጣሚም ቅዱስነታችው በተለያዩ ምክንያቶች የዓመታዊው የእረፍት ጊዜ ለመጠቀም የማይችሉ፣ እንዳሉ ሐምሌ1 ቀን 2009 ዓ.ም. በሰጡት አሰተምህሮ በመጥቀስ፣ ለእነዚህ የኅብረተሰብ አባላት ትብብር ድጋፍ እና ቅርበት እንዳይለያቸው እንዲሁም ሁሉም በጸሎት ለእነርሱ ቅርብ ይሆን ዘንድ ማሳሰባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።







All the contents on this site are copyrighted ©.