2010-07-05 13:51:47

ክርስትና የሥልጣኔ አንቀሳቓሽ


ሮማ በሚገኘው በልዊጂ ስቱርዞ ተቋም የኮንራድ አደናወር ማኅበር ያዘጋጀው ክርስትና የሥልጣኔ አንቀሳቃሽ ነው በሚል ርእስ ሥር ነገ ዓውደ ጥናት እንደሚካሄድ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ። በኤውሮጳ በጠቅላላ RealAudioMP3 በዓለማችን ክርስትና የእድገት፣ የእውቀት የሥልጣኔ መሠረት መሆኑ እና በዚሁ ጉዳይ የሰጠው አቢይ አስተዋጽኦ ያበቃለት ሳይሆን ቀጣይ መሆኑ ነገ ስለ ሚካሄደው ዓውደ ጥናት በተመለከተ የተሰጠው መግለጫ የጠቀሰ ሲር የዜና አገልግሎት በማስታወቅ፣ አለ ክርስትና የሰብአዊ መብት፣ የሰብአዊ ክብር እና ፈቃድ ብሎም ሰብአዊ ግዴታዎች ለማክበር ይቅርና ለማወቅ ባልተቻለም ነበር፣ የሚለውን እወነተኛው ሀሳብ መሠረት ያደረገ ዓውደ ጥናት እንደሚሆንም የዜና አገልግሎት አክሎ በማሳወቀ፣ የክርስትናው የላቀው ትምህርት በኢጣሊያ በጀርመን እንዲሁም በሌሎች የኤውሮጳ አገሮች ለተለያዩ የፖለቲካ ሰልፎች መሠረት እንደሆነና በማኅበረሰብ ዘንድ የላቁ እሴቶች እንዲጎሉ እና መመሪያ እንዲሆኑ ያነቃቁ እና በማነቃቃት ላይ የሚገኙ የሕይወት ክብር እንዲከበር የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብሩ እንዳይጣስ መከባበር መደጋገፍ የመሳሰሉትን እሴቶች መሠረት ያደረጉ መሆናቸውም ሃይማኖት እና ዴሞክራሲ በሚል ርእሰ በሚቀርበው ሰፊ አስተምህሮ እንደሚተነተን ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.