2010-07-05 13:47:44

እሴቶች እና የሰብአዊ መብት እና ግዴታ


የኤውሮጳ ህብረት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ፍርድ ቤት በኢጣሊያ ትምህርት ቤቶች የክርስትና የላቀው የእምነት ምልክት የሆነው መስቀል እንዳይሰቀል እ.ኤ.አ. ህዳር 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ያስተላለፈው RealAudioMP3 የመጀመሪያው ውሳኔ፣ ፍርድ ቤቱ የኢጣሊያ የይግባኝ ጥያቄ እና 10 የህብረቱ አባል አገሮች ኢጣሊያን በመደገፍ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በመቃወም የሰጡት መግለጫ መሠረት፣ እ.ኤ.አ. ሰነ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ይግባኝ የማይባልበት የመጨረሻ ውሳኔ እንደሰጠበት የሚዘከር ሲሆን፣ ውሳኔው ቢያንስ በስድስት ወር ቢበዛም በአንድ አመት ውስጥ በይፋ እንደሚገለጥ ሲነገር፣ ይኸንን እግምት ውስጥ በማስገባት የካቶሊክ እምነት ተከታይ ዳኖች ማኅብር ሊቀ መንበር የሕግ ሊቀ ፕሮፈሶ ፍራንቸስኮ ዳጎስቲኖ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ፖለቲካዊ ሥልጣን በባህል በሃይማኖት ጉዳይ ላይ ሥልጣን የለውም፣ የኤወሮጳው ኅብረት ፖሊቲካዊ ሕገ ለበስ ነው፣ ህብረቱንም ለማጽናት ፖለቲካዊ ስምምነቶች እና ውሳኔዎች ተከናውነዋል፣ ይኸንን የጋራው ስምምነት መቀናቀኑ ተገቢ ኣይደለም፣ ሁሉም አባላት አግሮች ሊጠብቁት እና ሊያከብሩት ይገባል፣ ሆኖም ኅብረቱ የአባል አገሮች ባህላዊ ሃይማኖታዊ ሉኣላዊነታቸውን ሊሰርዝ ሳይሆን፣ ሊንከባከብና ሊያከብር ይገባዋል፣ ካሉ በኋላ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የሚሰጠው ፍርድ አሉታዊ እና አዎንታዊ ሊሆን ይችላል፣ ሆኖም ባህልን እና ልምድን የሚጻረር ከሆን መንግሥታት ተአዝዞተ ኅሊና ሊያከብሩ ግድ ይሆንባቸዋል፣ ሃይማኖት በግላዊ አድማስ ለማጠር በኤውሮጳ እየተስፋፋ ያለው ተዛማጅ ባህል መሠረት ብዙ ሙከራ እየተደረገ ነው፣ ስለዚህ ይህ ዓይነት አመለካከት መሠረት ያደረገ ፖለቲካ ምን እንደሚያስከትልም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሲያስረዱ፣ ልቅ መንግሥታዊነት በማለት የሰጡት አስተምህሮ ለመጥቀስ ይቻልል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.