2010-07-05 13:46:22

ቅ.አ.ር.ሊ. ጳጳሳት የቤተ ክርስትያን ውኅደት/አንድነት ምልክት


የቅድስቲ መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍሊ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ትላትና ያቀረቡት ርእሰ አንቀጽ የር.ሊ.ጳ. ተቀዳሚው ኃላፊነት የቤተ ክርስትያን አንድነት መገንባት እና መከላከል መሆኑ RealAudioMP3 የሚያረጋገጥ ጴጥሮሳዊ ኃላፊነት የሚተነትን እንደነበር ተገልጠዋል።

በተለይ ደግሞ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቃላት እና እርምጃ የሚቀናቀኑ የተለያዩ ተግባሮች እና ሁኔታዎች ተመሳቅለው በሚስተጋቡበት በአሁኑ ወቅት፣ የር.ሊ.ጳ.ተቀዳሚው ኃላፊነት የቤተ ክርስትያን አንድነት መግባባት እና ከአደጋ መከላከል መሆኑ በመግለጥ፣ ይኸ ደግሞ የር.ሊ.ጳ. ጴጥሮሳዊ ኃላፊነት ምን መሆኑ የሚያስረዳ ነው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት የቅዱስ አባታችን ውሳኔዎች እና እርምጃዎች የቤተ ክርስትያን የውኅደት/ የአንድነት ሕይወት የሚያስገነዝቡ ወሳኝ እና የላቀ ጴጥሮሳዊ ተግባር መሆኑ፣ ኣባ ሎምባርዲ በሰጡት ርእሰ አንቀጽ በመግለጥ፣ ይህ ደግሞ እ.ኤ.አ. ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ባከበረቸው ዓመታዊ የቅዱሳት ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ በዓል ወቅት እጅግ ደምቆ እና ጎልቶ መረጋገጡንም አብራርተው፣ ጴጥሮስ ወንድሞችን በእምነት ማጽናት በአንድነት እና ለአንድነት መጠበቅ የተሰጠው ኃላፊነት በተከታዮች አርእስተ ሊቃ ጳጳሳት ኅያው ሆኖ እንደሚገለጥም ኣባ ሎምባርዲ በማስረዳት፣ ዛሬ በቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ አማካኝነት እየተመሰከረ ነው ካሉ በኋላ የአማኞች ማኅብረሰብ የሚከተሉት እምነት የሚደግፍ እና ለይቶ የሚያስረዳ ሊከተሉት የሚገባቸውን መንገድ የሚያመለክት ነው በማለት፣ በዚህ አጋጣሚም ይኸንን የሚመሰክር በቅርቡ ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዓለማችን በተለይ ደግሞ በበለጸጉት አገሮች በመስፋፋት ላይ ያለው ማመን አለ ማመን ሁሉም ያው ነው፣ እሴቶች እና የእሴቶች ቅደም ተከትል ብሎ የለም የሚለው ተዛማጅ ባህል እግምት ውስጥ በማስገባት የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተል ያቋቋሙት ጳጳሳዊ ምክር ቤት አንዱ መሆኑ ገልጠዋል።

በሌላው ረገድ ቤተ ክርስያን ከውጭ ብቻ ሳይሆን በውስጥዋ ከታቀፉት አባላቶችዋ አማካኝነት ችግር እንደሚደርስባትም ቅዱስ አባታችን በቅርቡ በማብራራት፣ ይኸንን በአማኞች ዘንድ መደናገርን እና አለ መረጋጋትን የሚያስከትለው ውጥረት በመለየት፣ የቤተ ክርስትያን አንድነት እና ውኅደት በሚገባ ለማጽናት እና ለመገንባት ብሎም ካደጋ ለመከላከል እየሰጡት ያለው ጴጥሮሳዊ ምስክርነት ለማንም የተሰወረ አይደለም ብለዋል።

ባለፈው ሰኞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የብፁዓን ካርዲናላት አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል ሶዳኖ እንዲሁም የቪየና ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሾንቦርንን በመቀጠልም ባለፈው ሐሙስ የአስቡርግ ልኂቕ ጳጳሳ ብፁዕ አቡነ ዋልተር ሚክሳን በመቀብል በጠቅላላ ያከናወኑዋቸው ግኑኝነቶች መሪ ሃሳብ በመስጠት ያሳዩት ጴጥሮሳዊ ተግባር በቤተ ክርስትያን እና በውሉደ ክህነት እንዲሁም በአማኞች ዘንድ አለ መግባባት እና ወጥረት እንዳይኖር የሚያረጋገጥ እና የክርስቶስ ተከታዮች በሞት ትላይ ድል ከነሳው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያላቸው ግላዊ እና ማኅበረ ክርስትያናዊ ግኑኝነት አማካኝነት እምነታቸውን እንዲኖሩ እና እንዲመሰክሩ የሚያሳስብ ነው በማለት ርእሰ አንቀጹን ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.