2010-07-02 13:36:37

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ የቅድስና እና የብጽእና ሰነድ ውሳኔ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና የቅድስና ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅይነተ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ አንጀሎ አማቶን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት፣ ቅድስት ቤተ ክርስትያን የሚሰዋው ፍቅር አብነት RealAudioMP3 በሕይወት ዘመናቸው ገቢራዊ ያደረጉ የፍቅር ቅዱሳት ከሚባሉት ውስጥ ብፅዕ ልዊጂ ጓኔላ የሚገኙባቸው ቅድስና እንደሚታወጅላቸው በማስታወቅ፣ ሌሎች አራት ቁጥራቸው በርከት ያሉ የደም ሰማዕትነት የተቀበሉት ገዳማውያን ካህናት እና ደናግል በስፐይን የርስ በርስ ጦርነት ወቅት እንዲሁም በጀርመን የናዚው ፈልጭ ቆራጭ መንግሥት በነበረበት ዘመን የደም ሰማዕትነት የከፈሉት የሚገኙባቸው የቤተ ክርስያን ልጆች የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስያን ቅድስና እና ብፅእና የማወጅ ውሳኔ ሰነድ ፊርማቸውን በማኖር ማስረከባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ብፁዕ ኣባ ልዊጂ ጓኔላ እ.ኤ.አ. በ 1842 ዓ.ም. በኢጣሊያ ሶንድሪዮ ከተማ የተወለደ ልክ በ 24 ዓመት ዕድሜው የክህነት ማዕርግ ተቀብሎ፣ ከቅዱስ ጆቫኒ ዶንቦስኮ ጋር ተዋውቆ በዘመኑ ያንሰራፋ ለነበረው ማኅበራዊ ድኽነት ለመቅረፍ፣ የትብብር እና የፍቅር ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት በማራመድ ሕዝብ ከማህበራዊ ከሰብአዊ እና ከኤኮኖሚያዊ ድኽነት ለማላቀቅ የተሟላ አገልግሎት በመስጠት እና በማነጽ እምነትን በቃል እና በሕይወት በማስተማር ተጠሞድ ሲኖር፣ እ.ኤ.አ. በ 1881 ዓ.ም. በቤተ ክርስትያን ፈቃድ መሠረትም የሚሰዋ ፍቅር አገልጋዮች እና የቸሪቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች ማኅበር በኮሞ እንዳቋቋመ የሚነገርለትም ሲሆን፣ ይህ ማኅበር በአሁኑ ወቅት በጠቅላላ ኢጣሊያ በላቲን አሜሪካ፣ በእስያ እና በአፍሪቃ አቢይ መንፈሳዊ እና ሰብአዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝም የሚታወቅ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ 1915 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ በኋላ እ.ኤ.አ. በ 1964 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኝ ብፅእና እንዳወጁለትም የቤተ ክርስትያን የታሪክ ማኅደር ያወሳዋል።

በ 1800 እና 1900 የዓመታት ገደብ ይኖሩ ከነበሩት ውስጥ የመለኮታዊ ጥሪ ማኅበር መሥራች ኣባ ጁስቲኖ ማሪያ ሩሶሊሎ (1891-1955)፣ እናቴ ማርያ ሰራፊና (1849-1911) የመላእክት ደናግል ማኅበር መሥራች፣ የቅዱስ ደመ ክርስቶስ ማኅበር አባል እናቴ አልፎንሳ ክለሪቺ (1860-1930)፣ እ.ኤ.አ. ገና በ 18 ዓመት እድሜዋ እ.ኤ.አ. በ 1928 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው ለሶስተኛ መደበኛው የማርያም አገልጋይ ዓለማውያን ማኅበር አባል ቸቺሊይ ኤውሰፒ ብፅእና እንደሚታወጅላቸው የቅድስት መንበር መገልጫ ይጠቁማል።

በትውልድነተቸው የሃንጋሪ ዜጋ ብፁዕ አቡነ ጆቫኒ ሸፍለር (1887-1952) በሮማኒያ የሳቱ ማረ ሊቀ ጳጳስ በመሆን ያገለገሉት በወቅቱ በነበረው የኮሙኒዝም ፈላጭ ቆራጭ ሥርዓት ውሳኔ በወህኒ ቤት እያሉ ሰማዕትነት የተቀበሉ፣ ጁዜፐ ማሪያ ሩይዝ ካኖ፣ ኸሱስ አኒባለ ጎመዝ ጎመዝ፣ ቶማሶ ኮርደሮ ኮርደሮ በስፐይን የእርስ በርስ የጦርነት ዘመን የደም ሰማዕትነት የተቀበሉ እና ሌሎች 13 የንጹሕ ቅዱስ ልበ ማርያም ልኡካን ማኅበር አባላት እ.ኤ.አ. በ1936 በነበረው አማኞች የማሳደድ ውሳኔ መሠረት ሰማዕትነት የተቀበሉት ጃርነኪ ናሩታ ኒታቢ ኩባረስ እና ሌሎች ዘጠኝ የቀርመሎሳውያን ገዳማውያን ማኅበር አባላት በተመሳሳይ ውሳኔ የእምነት ሰማዕትነት የተቀበሉት እንዲሁም በጀርመን የናዚው ሥርዓት ዘመን የእምነት ሰማዕት የሆኑት የሰበካ ካህናት ኣባ ጆቫኒ ፕራሰክ በፈረንሳይ የአብዮት ወቅት የቅዱስ ቪንሰንት ዘ ፓውሊ የደናግል ማኅበር አባል የደም ሰማዕትነት የተቀበሉት እናቴ ማርገሪታ ሩታን የሚገኙባቸው የቤተ ክርስትያን ልጆች ብፅእና እንደሚታወጅላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.