2010-06-30 14:41:45

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ረቡዓዊ የትምህረተ ክርስቶስ አስተምህሮ 30/06/2010

የአበ ነፍስ አስፈላጊነት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከአሥር ሺሕ በላይ የሚገመቱት ምእመናን በተሰበሰቡበት ዛሬ ረቡዕ በ 800 ዓመታት በቶሪኖ ይኖር የነበረ ካህን ኣባ ጆቫኒ ካፋሶ ማእከል ያደረገ ትምህረተ ክርስቶስ አቅርበዋል።

በአሁኑ ወቅት ይህ ቅዱስ ካህን ከዚህ ዓለም በሞት የተለየበት በትክክል RealAudioMP3 ሰኔ 23 ቀን 1860 ዓ.ም. መሆኑ በመጥቀስ፣ ይኸው በሰማይ ቤት የተወለደበት 150ኛ ዓመት በቅርቡ መዘከሩንም አስታውሰው፣ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የክህነት ዓመት ማክበሯንም ዘክረው፣ ለቤተ ክርስትያን አስደናቂ ክንዋኔዎች እና ውጤቶች ያጎናጸፈ የጸጋ ጊዜ ነው በማለት፣ ይኸንን አስደናቂው የጸጋ ዓመት መሠረት የዛሬው ረቡዓዊ ትምህርተ ክርስቶስ ቅዱስ ካህን ኣባ ጆቫኒ ካፋሶ ላይ ያተኮረ ማድረግ ተገቢ እና ዕድል ጭምር መሆኑ ገልጠዋል።

ቅዱስ ካህን ኣባ ጆቫኒ ካፋሶ መንፈሳዊ ሰብአዊ እና በቲይሎጊያው የግብረ ገብ ጥበብ የተካነ ብሎም ለሐዋርያዊ ግብረ ኖልው ለአስፍሆተ ወንጌል ቀናተኛ እንደነበር በማስታወስ፣ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ ምሥጢረ ንስሐ በመሥራት እና የነፍሳት አባት በመሆን የሰጠው ሐዋርያዊ አገልግሎት መሠረት ለካህናት አብነት እና አርአያ ነው በማለት የሰጡት መለያ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

አክለውም ቶሪኖ አበይት ቅዱሳት የተወለዱባት ከተማ መሆኗንም ዘክረው፣ ቅዱስ ጆቫኒ ካፋሶ የተዋበ ትልቅ ክህነት በሙላት የኖረ ለክህናት ጥሪ እና ለካህን ሕይወት አብነት ነው ብለዋል። ይህ ቅዱስ ካህን የሰጠው ምስክርነትም ይሁን አብነት፣ በመጽሓፍ የተደገፈ የቃላት ጥቅሶች የሚደግም ሳይሆን፣ ከህያው የእምነት ተመክሮ የመነጨ መሆኑ አብራርተው፣ ቅዱስ ዮሓንስ ቦስኮ፣ ይህ ቅዱስ ካህን የተረጋጋ ልቦና ያለው ጥበበኛ ጥንቁቅ እና አስተዋይ በማለት እንደገለጠው በማስታወስ፣ በሕይወቱ የእግዚአብሄርን ፍቃድ ከመሻት እና እርሱን ከመከተል ያላመነታ ቅዱስ ካህን ነው ብለዋል።

ቅዱስ ጆቫኒ ካፋሶ ዛሬ ወጣቶችን በማስተማር እና በማነጽ ጥሪ ለሚኖሩ እና ለመንፈሳዊ አባቶች አብነት ነው፣ እግዚብሔር ከኛ ምን እንደሚፈልግ ለመረዳት እንድንችል የሚደግፈን ቅዱስ የቤተ ክርስትያን ልጅ ነው፣ ካሉ በኋላ በቶሪኖ ከተማ ለኅሙማን ለተናቁት በድኽንት ጫንቃ ሥር ይኖሩ ለነበሩት፣ ለእስረኞች የሞት ፍርድ ለተበየነባቸው አጽናኝ መንፈሳዊ አባት በመሆን የሰጠው አገልግሎት መቼም ቢሆን የማይረሳ ለካህናት እና ለመንፈሳዊ አባቶች አብነት ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ትላትና የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ቅዱሳት ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ማክበሯ እና ከዚህ ዓቢይ በዓል ቀጥሎ ዛሬ የሮማ ቀደምት ሰማዕታት የሚዘከሩበት እለት መሆኑ ገልጠው፣ የተከበራችሁ ወጣቶች “የእነዚህ ቀደምት የእምነት ሰማዕታት ወንጌላዊ መንፍሳዊ ገድል አብነት ተከተሉ፣ እነዚህ ክርስቶስን በመምሰል የተገቱ እና የደም ሰማዕትነት የተቀበሉትን ምሰሉ፣ በማንኛው የሕይወታቸው ሁኔታ ለክርስቶስ ታማኞች ሁኑ ካሉ በኋላ፣ ኅሙማንን በመዘከር ስቃያችሁ የቀደምት ሰማዕታት አብነትን መርህ በማድረግ ለእግዚአብሔር ፍቅር እና ለወንድሞቻችሁ መስዋዕት በማድረግ አቅርቡ፣ ቀጥለውም አዳዲስ ሙሽሮችን በመጥቀስ በሕይወታችሁ እግዚአብሔርን ለእናንተ ያለውን እቅድ ገቢራዊ በማድረግ ጥሪያችሁን ካለ ማወላወል በመከተል ፍሬያማ እና ዘላቂነት ያለው ቤተ ሰብአዊ አንድነታችሁን አጽኑ ብለው፣ ትላትና በቅዱሳት ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ በዓል ምክንያት በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ተገኝተው ከቅዱስነታቸው እጅ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መለያ ለተቀበሉት ከተለያዩ አገሮች ለተወጣጡ ብፁዓን ጳጳሳት እና ከኢጣሊያ እና ከኢጣሊያ ውጭ ለመጡት መንፈሳውያን ነጋድያን ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ ቡራኬ ሰጥተው የዕለተ ረቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ በማጠናቀቅ የተሳተፉትን ሁሉ አሰናብተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.