2010-06-30 14:44:41

እሴቶች እና የሰብአዊ መብት እና ግዴታ


የኤውሮጳ ህብረት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ፍርድ ቤት በኢጣሊያ ትምህርት ቤቶች የክርስትና የላቀው የእምነት ምልክት የሆነው መስቀል እንዳይሰቀል እ.ኤ.አ. ህዳር 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ያስተላለፈው የመጀመሪያው RealAudioMP3 ውሳኔ፣ ፍርድ ቤቱ የኢጣሊያ የይግባኝ ጥያቄ እና 10 የህብረቱ አባል አገሮች ኢጣሊያን በመደገፍ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በመቃወም የሰጡት መግለጫ መሠረት፣ ዛሬ እ.ኤ.አ. ሰነ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ዳግም ውሳኔ እንደሚሰጥበት ሲገለጥ፣ ይኸንን እግምት ውስጥ በማስገባት፣ የኢጣሊያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት እና የኢጣሊያው ክርስትያናዊ ሰብአዊነት እንቅስቃሴ በመተባበር እሴቶች እና የሰብአዊ መብት እና ግዴታ በሚል ርእስ ሥር ያነቃቁት ዓውደ ጥናት በሮማ የባህል ጉዳይ ምክር ቤት ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ መካሄዱ የሚዘከር ሲሆን፣ የኢጣሊያ መንግሥት በዚሁ የህብረቱ የበላይ ፍርድ ቤት ዘንድ ጉዳዩን ቀርበው እንዲከታተሉ ኃላፊነቱን የሰጣቸው የሮማ ሶስተኛ መንበረ ጥበብ የሥነ ሰብአዊ መብት እና ግዴታ አስተማሪ የሕግ ሊቀ ፕሮፈሶር ካሮሎ ካዲያ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በቅድሚያ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ኤውሮጳ ኅብረቷን ያጸናችባቸው መሠታውያን እሴቶች የሚጻረር ነው፣ ስለዚህ ፍርድ ቤቱ የገዛ እራሱ መዋቅራዊ መሠረቱን ነው የተጻረረው፣ የኤውሮጳው ኅብረት የአባላት አገሮች ሉአላዊነት የሚጥስ ሳይሆን በሚገባ የሚያከበር ነው፣ ሉአላዊነት ባይኖር ኖሮ ኅብረቱ ሊረጋገጥ ባልቻለ ነበር ካሉ በኋላ፣ ፍርድ ቤት ቅዱስ መስቀል የካቶሊክ ሃይማኖት የእምነት መግለጫ ምልክት ነው ሲል ገልጦታል፣ ይህ ደግሞ ስህተት ነው፣ ምክንያቱን ቅዱስ መስቀል ለክርስትናውን እምነት የሚመለከት ቅዱስ ምልክት ነው። ስለዚህ ይህ መስቀል ያለው ኵላዊ እሴታ በመወሰን ወላጆች ለልጆቻቸው የሚከተሉት እምነት የማስተማሩ ነጻነት የሚቀናቀን ውሳኔ መሆኑ አብራርተዋል። ኤውሮጳ ከማንኛውም ዓይነት እምነት ነጻ የሆነው የምትከተለው የዓለማዊነት አመለካከት ሕዝባዊ እና ጥልቅ ስሜቶች የሚጎዳ ሆኖ መገኘት የለበትም በማለት የኤውሮጳ ህብረት አገሮች ሃይማኖታዊ መለያ እና ምልክት የእያንዳንዱ አባል አገር የሉኣላዊነት ውሳኔ እንጂ የህብረቱ የበላይ ፍርድ ቤት የሚመለከት ጉዳይ አይደለም፣ ስለዚህ የስቁል ኢየሱስ ቅዱስ ምስል ለሃይማኖታውያን እሴቶችን ብቻ ሳይሆን ለኤውሮጳው ሥልጣኔም ጭምር መሠረት መሆኑ አብራርተው ቅዱስ ምስል ቅዱስ መስቀል፣ ከኢጣሊያ እንዲሁም ከኤውሮጳ የሃይማኖታዊ ስሜት ታሪክ እና ባህል ጋር በጥብቅ የተቆራኘ የማንነት መለያ እና መግለጫ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።

የሥነ መብት እና ግዴታ መምህር የሕግ ሊቅ እና የኢጣልያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሕግ አማካሪ ፕሮፈሶር ቨነራንዶ ማራኖ በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የስትራስበርግ ፍርድ ቤት የመጀመሪያው ውሳኔ የቅዱስ መስቀል ቅዱስ ምስል በትምህር ቤቶች እንዳይሰቀል በማለት የሰጠው ፍርድ፣ ማንም የጠበቀው አልነበረም፣ ሆኖም ብዙ አገሮች ቤተ ክርስትያንም ሳይቀር ይህ የሃይማኖት መግለጫ ምልክቶች በይፋ መስቀል እና ሃይማኖትን መግለጥ ባህርያዊ መብት መሆኑ ዳግም ለመገንዘብ አነቃቅተዋል፣ በሌላው ረገድም የሃይማኖት ነጻነት ዳግም በሚገባ ተጢኖ እንዲከበር ለማድረግ የሚያነቃቃ ባህላዊ አመለካከት አስፈላጊ መሆኑ የጠቆመ ውሳኔ ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.