2010-06-30 14:43:16

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ የሊጡርጊያ ሥነ መለኮታዊ ትንታኔ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ገና የቅድስቱ ጴጥሮስ ተከታዮ ሆነው ከመሾማቸው በፊት እና ከተሾሙ በኋላ ባቀረቡዋቸው ጽሑፎች እና ድርሰቶች በተለያዩ ወቅቶች በሰጡት አስተምህሮ በትክክል የሰጡት የሊጡርጊያ ሥነ መለኮታዊ ትንታኔ በማሰባሰብ ብዙ ክፍሎች ያካተተ የብዕር ምርት በቅደም ተከተል የቲሎዮጊያ እና የሊጡርጊያ ሊቅ ኣባ ኤድሞንዶ ካሯና እና ሚላኖ RealAudioMP3 በሚገኘው ቅዱስ ልብ የካቶሊክ መንበረ ጥበብ የሥነ ፖለትካ ሥነ ሀሳባዊ ታሪክ መምህር የታሪክ ሊቅ ፕሮፈሶር ፔርሉካ አዛሮ አዘጋጅነት በቫቲካን እና በሄርደር ማተሚያ ቤት በኩል ለሕትመት እንደሚበቃ ተገልጠዋል።

ይህ የቅዱስ አባታችን የሊጡርጊያ ቲዮሊግያዊ ትንታኔ፣ የክርስትናው ቅዱሳት ምሥጢራት መሠረት ያለው ህላዌ በሚል ርእስ ሥር የሚቀርበው ተከታታይ ድርሰት በማስመልከት በቀዳሚው መጽሓፍ የመግቢያውን ክፍል የጻፉት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ቀደም በማድረግ እንደገለጡት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለዘመኑ ሰው እንደ ገጸ በረከት ያቀረቡት ጥልቅ እና በሥነ ሓሳብ እጅግ ሃብታም የሆነው ጽሑፍ፣ ባላቸው የማስተማር ብቃት እና እንዲሁም የካህን ተልእኮአቸው አማካኝነት የተወሳሰበው እና ቲዮልግያዊ እና ፍልስፍናዊ ጥልቀት ያለው ሥነ ሀሳብ ሁሉም ሊረዳው በሚችለው መንገድ የሰጡት የሊጡርጊያ ቲዮሎጊያዊ አስተምህሮ ለአማኞች ብቻ ሳይሆን እንዲሁም ለኢአማኒያ የቀረበ እምነትን እና ምርምርን ያጣመረ መሆኑ አብራርተዋል።

ይህ ተከታታይ ድርሰታቸው ሥነ ቤተ ክርስትያን በቅዱስ አጎስጢኖስ ሥነ አስተሳሰብ ሥር እንዲሁም የቲዮሊጊያ ታሪክ፣ ሁለተኛው ሥነ ግልጸት/ ሥነ አስተርእዮ በቅዱስ ቦናቨንቱራ ሥነ አስተሳሰብ፣ ሦስተኛው እምነት እና ሥነ ምርምር፣ በመግቢያው ክርስትና እና ተአምኖተ ሃይማኖት ምሥጢረ ጥምቀት፣ መለወጥ የክርስቶስ ተከታይነት የክርስትና ህላዌ ፍጻሜ፣ የቲዮሎጊያ ሥነ አገባብ ትንታኔ እንዲሁም ቅዱስ አባታችን በሰጡት የቃለ መጠይቆች ምላሽ የሊጡርጊያ ጉዳይ በተመለከተ ያሉትን በስብከቶቻቸው ስለ ሊጡርጊያ የሰጡትን ሃሳብ የመሳሰሉት ያካተተ ተከታታይ መጽሓፍ መሆኑ ከወዲሁ ለማወቅ ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.